Get Mystery Box with random crypto!

Top Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja T
የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @topmereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.48K
የሰርጥ መግለጫ

-ማስታወቂያ ለማሰራት እና ለአስታየት :- @NatnaelAbreham1
የ Twitter አድራሻ : http://twitter.com/BoleMereja?t=watBbei5PnmgrUd80qQrnw&s=09
ዩቲዩብ : https://youtube.com/channel/UCXcMdhLzUAPeRAxW48JFClQ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-07-16 12:21:40
ExitExam Result

ተመራቂ ተማሪዎች የመዉጫ ፈተና ውጤታችሁን ከአሁን ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣችሁን Username በመጠቀም በዚህ ሊንክ https://result.ethernet.edu.et በመግባት ማወቅ ትችላላችሁ።

@TopMereja
@TopMereja
25.0K viewsedited  09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-16 11:15:09
"በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ባልተጠበቀና ባልተለመደ ሁኔታ ብቅ ብቅ ሲሉ የሚታዩት ራስን በራስ የመሾም አባዜ መገታት አለባቸው:: ማንኛውም ችግር በውይይትና በምክክር የተበደለውንም በትክክል በመካስ መፈታት ይገባዋል! ከዚህ ውጭ በጥፋት ላይ ጥፋት እየተከሠተ የቤተ ክርስቲያንን ህልውና የሚፈታተን ድርጊት ማቆም አለብን።"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት።

@topMereja
14.4K views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-15 20:05:00
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተመደቡ

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሊቀ ጳጳስ የምዕራብ አርሲ (ሻሸመኔ) ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲያገለግሉ በቅዱስ ሲኖዶስ መዘዋወራቸው ተገለጸ።

ብፁዕነታቸው የምዕራብ ሸዋ ፣ የሆሮ ጉዱሩ እና ምሥራቅ ወለጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ላለፉት ዓመታት ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል።

የዝውውሩ ምክንያት ቀደም ሲል በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አዳዲስ የሚሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት የሚመደቡበት ሀገረ ስብከት ለውጥ የተደረገበት መሆኑን ተከትሎ ነው።

የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ርዕሰ ከተማ ሻሸመኔ ከዚህ ቀደም በሕገወጦቹ አካላት በተደረገ ሢመት ቁጥራቸው ከ70 በላይ የሚሆኑ ምዕመናን ሰማዕትነት መቀበላቸው እና ከ450 በላይ የሚሆኑት ምዕመናን ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ይታወሳል።

Via ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

@topMereja
13.3K viewsedited  17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-15 14:56:47
ውጤት እሁድ ከማታ ጀምራችሁ ማየት ትችላላችሁ

የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ከነገ እሁድ #ማታ ጀምሮ ውጤታቸውን ኦንላይን ማየት ይችላሉ፡፡

User Name በመጠቀም በ https://result.ethemnet.edu.et/ በመግባት ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ።

@topMereja
@topMereja
12.5K viewsedited  11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-15 07:49:31
#ExitExamResult #KotebeUniversity

ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ውጤት ሪፖርት ገልጿል። በዚህም መሠረት 69% አማካይ የተገኘ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው  ካስተፈናቸው ዲፓርትመንቶች ውስጥ ለአብነት ያህል

Urban Environmental management = 100 %

Urban land administration = 100%

Urban and regional planning = 100%

Computer science = 73%

Accounting and finance = 62%

Economics = 74%

Management = 92.6% ተማሪዎችን አሳልፈዋል።

@topMereja
@topMereja
12.4K views04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-14 21:27:13
#ExitExam_Result

ላለፋት 5 ቀናት ከሐምሌ 3/2015 ዓ/ም ጀምሮ ሲሰጥ የነበረው የቅድመ ምረቃ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት በከፊል ዛሬ ይፋ እየሆነ ይገኛል።

በዚህም መሠረት ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ

በ41 ፕሮግራሞች ካስፈተናቸው 1604 ተፈታኞች ፡-
1ኛ. በ13 ፕሮግራሞች 100%
2ኛ. በ7 ፕሮግራሞች ከ90-99%
3ኛ በ11 ፕሮግራሞች ከ80-89%
በአጠቃላይ በ31 ፕሮግራሞች 80% እንዲሁም እንደ ዩኒቨርሲቲ 81% ተማሪዎች ማለፋቸውን(50% እና ከዚያ በላይ) ዩንቨርሲቲው በፌስቡክ ገጹ አሳውቋል።

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ካስፈተናቸው 1604 ተማሪዎች 1289 ተማሪዎች ከ50% በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ጠቅሶ ላለፉ ተመራቂ ተማሪዎቹ እና ለመላው የዩንቨርሲቲው ማህበረሰብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

@topMereja
@topMereja
21.9K viewsedited  18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-14 15:09:08 መድፍ
በቆቦ ከተማ ከ8:20 ጀምሮ የመድፍ ድምፅ አየተሰማ ይገኛል። እስከ አሁን 3 ጊዜ ተተኩሷል ብለዋል።
@topmereja
12.7K views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-13 20:43:16
በአዲስ አበባ የሚገኙ 12 ትምህርት ቤቶች ተዘጉ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በአዋጅ 74/2014 በተሠጠው ተግባርና ኃላፊነት መሠረት የግል ት/ቤቶችን ለደረጃው በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ለተቋማት ፍቃድና እድሳት ይሰጣል፣ ስታንዳርዱን ያላሟሉና የህግ ጥሰት የፈጸሙ ተቋማት ላይ እርምጃ ይወስዳል፡፡

በዚህም በከተማው ውስር ያሉት ፦

1. አዲስ ተስፋ ቅድመ አንደኛ - አቃቂ
2. ዜድኤም ቅድመ አንደኛ -አቃቂ
3. ግሎው ቅድመ አንደኛ -ንፋስ ስልክ
4. ኤልሻዳይ ቅድመ አንደኛ -ንፋስ ስልክ
5. ሰቆሬብርሀን ቅድመ አንደኛ - ንፋስ ስልክ
6. ማይድሪም ላንድ ቅድመ አንደኛ -ንፋስ ስልክ
7. ቲፒፋይ ቅድመ አንደኛ -ንፋስ ስልክ
8. ሮማናት ቅድመ አንደኛ - ንፋስ ስልክ
9. አዲስ ቪዥን ቅድመ አንደኛ -ቦሌ
10. አዲስ ቪዥን የመጀመሪያ ደረጃ - ቦሌ
11. ኢልመኑር ቅድመ አንደኛ -ኮልፌ ቀራንዮ
12. ስትራይቨርስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት - ንፋስ ስልክ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለደረጃው በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ተመዝነው የሚጠበቀውን መስፈርት ማሟላት ባለመቻላቸውና ከደረጃ በታች በመሆናቸው መዘጋታቸውን አሳውቋል።

ተቋማቱ በእውቅና ፍቃድና እድሳት መመሪያ ቁጥር 02/2012 እና ከደረጃ በታች የሆኑ ተቋማትን ለማሸግ በወጣው መመሪያ 01/2014 መሰረት ነው እንዲዘጉ ውሳኔ የተላለፈባቸው።

ት/ቤቶቹ ለ2016 ዓ/ም ማስተማር የማይችሉ ሲሆን ትምህርት ቤቶቹ የተማሪዎችን ውጤት የሚገልጽ መረጃ ለተማሪዎችና እውቅና ፍቃድ ለስጣቸው አካል እንዲያስረክቡ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ይህ ሳይሆን ቀርቶ በተማሪዎችና በተማሪ ወላቾች ላይ ለሚፈጠር እንግልት ት/ቤቶቹ ተጠያቂ ይሆናሉ ተብሏል።

@topMereja
14.0K viewsedited  17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-13 11:10:42 ቆቦ ከባድ ውጊያ
ቆቦ ከተማ ውስጥ እንዲሁም ዙሪያውን በተለይ ድንኳን ተራራ በሚባል ቦታ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ነው። አሁን ወደ ከተማዋ ውስጥ ገብቷል ፈንጅም ተወርውሯል። አንድ ወጣት ተመቶ ሆስፒታል ገብቷል።
@topmereja
13.6K views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-11 18:33:48
የሜካኒካል ተማሪዎች በ Exit ፈተና ይዘት ላይ ቅሬታ አቀረቡ

#JimmaUniversity #MattuUniversity
#HawassaUniversity #HaramayaUniversity
#Debretaboruniversity

የሜካኒካል ምህንድስና ተማሪዎች በቀን 03/11/2ዐ15 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስትር የተዘጋጀውን የመውጫ ፈተና መፈተናችን ይታወቃል ።

ቢሆንም ግን የፈተናው ይዘት ከተነገረንና መመዘኛ ነው ተብሎ ከቀረበው ሀሳብ ጋር ፍፁም የማይገጥም ፣ እንዲሁም ሆን ተብሎ ተማሪን ለመጣል በሚመስል መልኩ የተዘጋጀ ፈተና ነበረ ። የፈተናው ክብደት እና ከBlue print ጋር ያለመጣጣም ብቻ ሳይሆን ለፈተናው የተሰጠን ሰዓት ከጥያቄው አንፃር እዚህ ግባ የማይባል ነው።

ስለሆነም ከስር በተዘረዘሩት ነጥቦች ላይ የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶ በማጤን አስቸኳይ መፍትሔ (ማለትም የፈተናው ውጤት ከመገለፁ በፊት) እንዲሰጠን አጥብቀን እንጠይቃለን ፤

1~የወጡ ፈተና ጥያቄዎች ተከልሶ እንዲታዩ

2–በተመሳሳይመልኩ የፈተናው ጥያቄ እና የBlueprint ይዘት እንደማይገናኝ ተመልሶ እንዲታይ

3~የፈተናው ጥያቄ እና የተሰጠን ሰዓት ፍፁም አለመጣጣም፣

4 –የፈተናው ጥያቄ ውስጥ የመጡ የሂሳባዊ ስሌቶች ( Calculations) ጥያቄዎች በተሰጠው ሰዓት ልሰራ ቀርቶ ፣ አንዱ ጥያቄ ብቻውን ከ3ዐ እና ከዚያ በላይ ደቂቃ የሚፈጅ በመሆኑ ፣

5 – የንድፈ ሀሳብ (Theory ) ጥያቄዎች ያለቅጥ በማርዘም ፣ ትክክለኛውን የጥያቄውን ሀሳብ ለማግኘት ሰዓት የሚፈጅ በመሆኑ እንድታይልን ስሉ ቅሬታ አቅርቧል።
 
            Share share
19.6K views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ