Get Mystery Box with random crypto!

Top Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja T
የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @topmereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.48K
የሰርጥ መግለጫ

-ማስታወቂያ ለማሰራት እና ለአስታየት :- @NatnaelAbreham1
የ Twitter አድራሻ : http://twitter.com/BoleMereja?t=watBbei5PnmgrUd80qQrnw&s=09
ዩቲዩብ : https://youtube.com/channel/UCXcMdhLzUAPeRAxW48JFClQ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-05-02 11:37:10
#እንድታውቁት

" ከግንቦት 1 ጀምሮ ያለ ዲጂታል መታወቂያ ሞተር ማሽከርከር አይቻልም " - የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ

በአዲስ አበባ ከተማ ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ያለ ዲጂታል መታወቂያ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር እንደማይቻል የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳሰበ፡፡

በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ የሞተር ብስክሌት ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች የመንቀሳቀሻ ፈቃዳቸውን ጂፒ ኤስ ባስገጠሙበት ተቋም የዲጂታል መታወቂያውን እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲወስዱ ተጠይቀዋል፡፡

ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሞተር ብስክሌቶች ላይ በሚደረገው ጥብቅ ቁጥጥር ያለ ዲጂታል መታወቂያ በሚንቀሳቀሱት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ሲል ኤጀንሲው አሳስቧል።

@topMereja
9.6K views08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 11:16:59
በተከታታይ በአመራሮች ላይ የሚደረገው ግድያ የአማራን ሕዝብ ስቃይ እና መከራ ለማራዘም በሚሠሩ ፅንፈኛ ኃይሎች ቀጣይነት ያለው መሆኑን ማሳያ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ።

በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ የአቶ ግርማ የሺጥላ የአስከሬን ሽኝት ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ፣ የወንድማችን ግርማ መሥዋዕትነት በተለይ ለአመራራችን የሚያስተላልፈው መልእክት ሁላችንም የያዝነውን ዓላማ ለማሳካት እስከ መሥዋዕትነት ቆርጠን ለመሄድ የግድ የሚለን መሆኑን ነው ብለዋል።

ታጋዩ፣ ታታሪው እና ቆራጡ ሲሉ የገለጹት አቶ ግርማ የሺጥላ፣ አድፍጠው መንገድ ላይ በጠበቁት ፅንፈኞች መቀጠፉ በእጅጉ እንዳሳዘናቸውም ገልጸዋል።

@topMereja
13.1K views08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 23:46:03
የአቶ ግርማ የሺጥላ አስከሬን በነገው እለት በወዳጅነት አደባባይ የክብር ሽኝት ይደረጋል።

የአማራ ክልል ብልፅግና ፅፈት ቤት ሀላፊ የነበሩትና ከሁለት ቀናት በፊት የተገደሉት የአቶ ግርማ የሺጥላ አስከሬን በወዳጅነት አደባባይ በልዩ ሁኔታ የክብር ሽኝት ለማድረግ መንግስት ተዘጋጅቷል።

የክብር ሽኝቱ በነገው እለት የሚደረግ ሲሆን ቤሰቦቹ፣ የትግል ጓዶቹ፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት ፣ ወዳጆቹ በተገኙበት የሽኝት ስርዓቱ ይፈፀማል።

ከጠዋት 12 ስዓት ጀምሮ ስርዓቱ ከቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ጀምሮ በወዳጅነት አደባባይ የሚከናወን ሲሆን የአቶ ግርማ የሺጥላ አስከሬን በተወለዱበት አካባቢ ማህል ሜዳ በክብር ያርፋል ተብሎ ይጠበቃል።

የቀብር ሽኝት ኮሚቴው

@topMereja
2.1K viewsedited  20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 21:48:36
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ዙሪያ ኤፍራታ ግድም ወረዳ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት አርሶ አደሮች ሰብላቸውን መሰብሰብ አለመቻላቸውን ገለጹ።

Via አዲስ ማለዳ

@topMereja
8.3K views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 18:33:43
" ማኅበረሰቡ ፈፃሚዎችን ሊያወግዝና ተገቢው ማጣራት ተደርጎ ፍትኅ እንዲሰፍን የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል " - አቶ ክርስቲያን ታደለ

በአማራ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈፀመው ግድያን " በማንም ለምንም ዓላማ ይፈፀም ተቀባይነት የሌለው ወንጀል " መሆኑን የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ገለፁ።

አቶ ክርስቲያን ፤ " በወንድማችን ግርማ የሽጥላ ላይ በተፈፀመው ግድያ በእጅጉ አዝኛለሁ " ብለዋል።

" ድርጊቱ በማንም ለምንም ዓላማ ይፈፀም ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ወንጀል ነው። " ያሉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ " ማኅበረሰቡ ፈፃሚዎችን ሊያወግዝና ተገቢው ማጣራት ተደርጎ ፍትኅ እንዲሰፍን የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል " ሲሉ አሳስበዋል።

አቶ ክርስቲያን፥ በሁሉም በኩል የሚደረጉ ፍረጃዎችና የሴራ ትንተናዎች ወንጀሉን በአግባቡ በመመርመር  ገዳዮችን ለፍትህ ለማቅረብ የሚደረገውን ጥረት እንዳይጎትቱ ብርቱ ጥንቃቄዎች ሊደረጉ ይገባል ብለዋል።

" የአማራ ሕዝብ ሰላሙንና አንድነቱን እንዲጠብቅ አሳስባለሁ " ያሉት አቶ ክርስቲያን ታደለ ፤ " ለመላው ለቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዶቹ ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ " ሲሉ ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

@topMereja
9.2K views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 18:57:58
NewsAlert

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በአማራ ክልል የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የኾኑት ግርማ የሺጥላ ዛሬ "በነውጠኛ ጽንፈኞች" መገደላቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ዐቢይ በዚኹ መልዕክታቸው፣ "በሐሳብ የተለየን ኹሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሳት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው" ብለዋል።

ግድያው "አስነዋሪና አሰቃቂ" መኾኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ካልተወገደ "ወደመጨራረስ እንደሚወስደን ጉልህ ማሳያ ነው" በማለትም ድርጊቱን አውግዘዋል።

ግርማ ዛሬ የተገደሉት በተወለዱበት አካባቢ መኾኑንም ዐቢይ ጨምረው ገልጸዋል።
@topmereja
11.3K views15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 11:42:02
የ35 የአማራ፣ 2 የአፋር ባለሃብቶችና ድርጅቶች የባንክ አካውንት ታገደ!

የአማራ ሕዝብ ትግልን ሊደግፉ ይችላሉ በሚል፤ የአማራ ባለሃብቶችን ለማሠርና ንብረታቸውንም ልክ እንደ ትጥቁ ለማስፈታት እንቅስቃሴ መጀመሩን ለቶፕ መረጃ የደረሰው መረጃ ያሳያል። በኦሮሚያ ብልጽግና ሰዎች የሚመራው የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዛሬ ለሁሉም ባንኮች በጻፈው ደብዳቤ የ35 የአማራ ባለሃብቶች እንዲሁም 2 የአፋር ባለሃብቶች በባንክ ያላቸው ገንዘብ እንዲታገድ ለሁሉም ባንኮች የጻፈው ደብዳቤ ይህን ይመስላል። ይህም በኦሮሚያ ብልጽግና እና በአማራ ብልጽግና መካከል ያለውን ሽኩቻ አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ የብልጽግና ምንጮች ይናገራሉ። ደብዳቤውን ተመልከቱት፤ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እመጣለን።

በነገራችን ላይ የሞቱ ሰዎችም ጭምር በ እገዳው ስማቸው ተጠቅሷል።

@topMereja
12.2K views08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 10:39:59
መንግስት "ሸኔ" ብሎ የሚጠራኝ ማንነቴን እና አላማዬን ለማጥላላት ነዉ ሲል የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አስታወቀ!!

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት "በሶስተኛ አካል በኩል ከመንግስት ጋር ድርድር መካሄድ የምደግፈው ሰላምም የሚገኘው በውይይት ብቻ ነው" ያለ ሲሆን" ሸኔ" የሚለው ቃል የእኔ መጠሪያ አይደለም ብሏል።

በትናንትናው እለት መንግስት "ሸኔ" ሲል ከሚጠራዉ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር በታንዛንያ ድርድር ሊያደርግ መሆኑን መዘገቡ ይታወሳል። ሰራዊቱ ድርድሩን አስመልክቶ ባወጣዉ መግለጫ እንዳስታወቀው ለድርድሩ ያስቀመጣቸዉ ቅድመ ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት ማግኘታቸዉን ተናግሯል።

በመግለጫው አያይዞም ፤ መንግስት "ሸኔ" ሲል የሚጠራኝ ማንነቴን እና አላማዬን ለማጥላላት ነዉ ሲል ሲል ሰራዊቱ ገልጿል። መንግስት በተለይም በኦሮሚያ ክልል እና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ለሚደርሱ ጥቃቶች "ሸኔን" ተጠያቂ ሲያደርግ ቆይቷል።

በርካታ የፖለቲካ ተንታኞችም "ሸኔ" የተሰኘ አደረጃጀት እንደሌለ ሲገልጹ መቆየታቸዉ ይታወቃል። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድሩ ግልጸኝነት እንዲኖረዉ በሶስተኛ ወገን አደራዳሪነት መከወኑ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሷል። ይህም በመንግስት ተቀባይነት ማግኘቱን እና ድርድሩ እንደሚከናወን ማረጋገጫዉን ሰጥቷል።

@topMereja
4.8K views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 18:01:13
#አሁን

በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ "ጦርነት ይብቃ ሰላምን እናፅና" የተሰኘ ፕሮግራም እየተከናወነ ይገኛል።

@topMereja
7.8K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 13:41:25
የሱዳኑ RSF ታጣቂ ቡድን መሪ ጄኔራል ሐምዳን ዳጋሎ (ሀምቲ) ከ9 ቀናት ቆይታ በኋላ በአደባባይ ታዩ።

@topMereja
623 views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ