Get Mystery Box with random crypto!

Top Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja T
የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @topmereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.48K
የሰርጥ መግለጫ

-ማስታወቂያ ለማሰራት እና ለአስታየት :- @NatnaelAbreham1
የ Twitter አድራሻ : http://twitter.com/BoleMereja?t=watBbei5PnmgrUd80qQrnw&s=09
ዩቲዩብ : https://youtube.com/channel/UCXcMdhLzUAPeRAxW48JFClQ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-05-29 19:43:09
የደብረምጥማቅ ፃድቃኔ ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል እና ህንፃ ቤተክርስቲያን ምርቃት ዛሬ ተከብሮ ውሏል።

በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ የምትገኘው የደብረምጥማቅ ፃድቃኔ ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል እና አስር አመታት የግንባታ ሂደትን የወሰደው ህንፃ ቤተክርስቲያን ምርቃት በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን ወረዳው አስታውቋል።

ከእስከዛሬዉ ለየት ባለ መልኩ ሰፊ ቁጥር ያለዉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መታደማቸውን የገለጹት የወረዳዉ ሠላምና ድህነት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሸዋፈረዉ ግርማ በዓሉ በድምቀት አክብረዉ ዉለዋል ሲሉ ገልጸዋል።

ኃላፊው ክብረ በዓሉም በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ ምዕመናኑ ወደ ቤታቸዉ የመሸኘቱ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።

@topMereja
14.3K viewsedited  16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 09:56:20
511 ማህተሞችን በመጠቀም ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጁ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

የጸጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ክትትል 511 ማህተሞችን በመጠቀም ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጁ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ።

አቶ አሻግሬ በለጠ አለሙ እና ግብረአበሮቹ በአራዳ ክፍለ ከተማ 511 ማህተሞችን በመጠቀም ሃሰተኛ የመንግስት ተቋማት ሰነዶችን ሲያዘጋጁ ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት።

ግለሰቦቹ ከ1 ሺህ 500 እስከ 4 ሺህ 500 ብር በማስከፈል ሃሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት የወንጀል ተግባር ሲፈፅሙ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ያዘጋጇቸው  የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ሀሰተኛ ሰነዶችም በኢግዚቢትነት መያዛቸውን ከአዲስ በባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@topMereja
15.0K views06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 09:06:08
ከአማራ እና ትግራይ ክልል ውጭ በሌሎች አንዳንድ የሀገሪቱ ክልሎች ማለትም በኦሮሚያ ፣ በሲዳማ ፣ በደቡብ ፣ለመከላከያ ሠራዊት የድጋፍ ሰልፍ እየተደረገ ነው።

@topMereja
11.3K views06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 09:10:07 የኢትዮጵያ 86ቱ ብሄር ብሄረሰቦች መጠሪያ ስም ዝርዝር
1. አማራ
2. ኦሮሞ
3. ሶማሌ
4. ትግራይ
5. አፋር
6. ሲዳማ
7. አገው
8. ዎላይታ
9. ከምባታ
10. ሀዲያ
11. ጋሞ
12. ጉራጌ
13. ኢሮብ
14. አርጎባ
15. ቱለማ
16. ስልጤ
17. ሺናሻ
18. አኝዋክ
19. ኑዌር
20. ሀመር
21. ኩናማ
22. ጉምዝ
23. በርታ
24. በና
25. አሪ
26. ሙርሲ
27. ቡሜ
28. ካሮ
29. ፀማይ
30. ኮንሶ
31. ዳሰነች
32. ቦረና
33. ጋብራ
34. አላባ
35. አርቦሬ
36. ባጫ
37. ቤንች
38. ባስኬቶ
39. ቡርጂ
40. ጫራ
41. ጋዋዳ
42. ጌዲኦ
43. ጊዶሌ
44. ጎፋ
45. አደሬ
46. ከፊቾ
47. ኮንታ
48. ኒያንጋቶም
49. ናኦ
50. ቀቤና
51. ሱርማ
52. ጠንባሮ
53. የም
54. ወርጂ
55. ዲዚ
56. ዶንጋ
57. ዳውሮ
58. ዲሜ
59. ምዓን
60. ኮሞ
61. ማረቆ
62. ሞስዬ
63. ኦይዳ
64. ቦዲ
65. ፈዳሼ
66. ኮሬ
67. ማሌ
68. ማኦ
69. መሰንጎ
70. መዠንገር
71. ቀዋማ
72. ቀጨም
73. ሸኮ
75. ዘየሴ
76. ዘልማም
77. ሽታ
78. ቤተ እስራኤል
79. ማሾላ
80. ኮጉ
81. ድራሼ
82. ገባቶ
83. ጌዲቾ
84. ብራይሌ
85. ሙርሌ
86. ኮንቶማ .... ናቸው።

@topMereja
@topMereja
10.9K viewsedited  06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 11:03:15
#NewsAlert

ቦርዱ የህወሓትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ላይ ያስተላለፈውን የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሥረዛ ፓርቲው " ይነሣልኝ " ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

ህወሓት ያቀረበው ጥያቄ ምንድነው ?

ህወሓት የፓርቲውን ህጋዊ ሰውነት ስረዛ፤ የፓርቲው ሃላፊዎች በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንደማይችሉ እና የፓርቲው ንብረት ተጠርቶ ፓርቲው ዕዳ ካለበት ለዕዳ መሸፈኛ እንዲውል፤ ቀሪው ገንዘብና ንብረት ለሥነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት እንዲውል ከዚህ በፊት በምርጫ ቦርድ የተላለፈው ውሳኔ እንዲነሳ ሲል በደብዳቤ ጠይቋል።

ለቦርዱ ውሳኔ ምክንያት የሆነው ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመፅ ተግባር አሁን ላይ ባይኖርም እንደገና ህጋዊ ሰውነቱን ለፓርቲው ለመመለስ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች በአዋጅ 1162/2011 ተደንግጎ አይገኝም ሲል ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

በዚህም የህጋዊ ሰውነት ጥያቄ የማስመለስ ጉዳይ በህግ የተደገፈ ሆኖ እንዳላገኘው ቦርዱ አመልክቷል።

ፓርቲው ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ ለመንቀሳቀስ የሚችለው በአዋጅ 1162/2011 አንቀፅ 66 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት በድጋሚ የምዝገባ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ቦርዱ ህጉን መሰረት አደርጎ ሲፈቅድ መሆኑን ቦርዱ ወስኗል።

የፓርቲው አመራሮች እና ንብረትን በተመለከተ የቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ፓርቲው ላይ የሰጠው የስረዛ ውሳኔ ውጤቶች በመሆናቸው እንደአዲስ ሊጠየቁ የሚችሉ አይደሉም ያለው ምርጫ ቦርድ በዚህ በኩልም የተጠየቀውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

(ደብዳቤው ከላይ ተያይዟል)

@topMereja
11.4K views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 11:25:55
በአዲስ አበባ ከተማ መሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራ ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል

በአዲስ አበባ ከተማ ስድስተኛ ዙር የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራ ከዛሬ ግንቦት 03/2015 ጀምሮ ባሉ ተከታታይ አምስት ወራት እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አሰታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ግፈወሰን ዴዲሳ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የይዞታ ማረጋገጡ ስራ በተመረጡ ሰባት ክፍለ ከተሞች ይካሄዳል።

ምዝገባው በቦሌ፣ በኮልፌ ቀራኒዮ፣ አዲስ ከተማ፣ ልደታ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ቂርቆስና በአራዳ ክፍለ ከተሞች ባሉ50 ቀጠናዎችና 211 ሰፈሮች እንደሚከናወን ገልጸዋል። ወጪውም መሉ በሙሉ በመንግስት እንደሚሸፈን ተናግረዋል።

የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራው በተመረጡ ቀጠናዎችና ሰፈሮች ውስጥ ብቻ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የመረጃ ልዩነት እንዳይፈጠር ምንም ዓይነት የስምና የንብረት ዝውውር እንዲቆም ይደረጋልም ብለዋል፡፡

የይዞታ ማረጋገጥ ስራ በሚከናወንባቸው ቀጠናዎችና ሰፈሮች ውስጥ የሚገኙ ባለይዞታዎች ኤጀንሲው አረጋግጦ ላልመዘገበው ይዞታ ምንም ዓይነት ህጋዊ ዋስትና እና ከለላ የማይሰጥ በመሆኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

@topMereja
7.5K views08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 20:47:52 የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከጅቡቲ ተያዘ የተባለውን የበይነ መረብ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ጨምሮ በስድስት የሽብር ወንጀል ተጠርጣሪዎች ላይ 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት መፍቀዱን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል።

ችሎቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ያደረገው፣ መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ባስተባበሩት "የሽብር ድርጊት በርካታ ንጹሃን ዜጎች እንዲሞቱና ንብረት እንዲወድም ኾኗል" በማለት ያቀረበውን አቤቱታ ግምት ውስጥ በማስገባት እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል።

@topMereja
8.9K views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 12:04:21
ልዩ መረጃ

በአዲስአበባ መሃል ከተማ ውስጥ ጉድ ታየ። የፌድራል ፖሊስ የማይታመን ነው። በቪድዮ ይመልከቱት





11.6K viewsedited  09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 17:01:09
መረጃ !

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 30 ከቀኑ 8:30 በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የቀጨኔ  መካነ መቃብር አጥር ግንብ ተደርምሶ በአጥሩ ሥር በግ ከሚነግዱ ነጋዴዎች መካከል የኹለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

‹‹ቀሪ አስከሬን ካለ›› በሚል በአሁኑ ሰዓት ፍለጋ እየተካሄደ እንደሚገኝ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ በተለይም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ቁጥራቸዉ ለጊዜዉ በውል ያልታወቁ በግና ፍየሎች ሞተዋል የተባለ ሲሆን፤ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በፍለጋ ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል።

@topMereja
13.0K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 17:13:54
ልዩ መረጃ

የኢትዮጵያ መንግስት የፀጥታና ደህንነት ግብረሃል ከሳምንት በፊት በለጠ ጋሻው እና ምህረት ወዳጆ (ምሬ ወዳጆ ) የአማራ ብልፅግና ፅ/ቤት ሀላፊ የነበሩትን የአቶ የግርማ የሽጥላን ግድያን በሚመለከት በስልክ አድርገውታል  ብሎ በድምፅ ያሰራጨው መረጃ በሃሰት የተቀነባበረ መሆኑን በአሜሪካን ሃገር በዘርፉ ከ20 ዓመት በላይ ልምድ ያለው Digi Audio and video forensic service የተሰኘው መርማሪ ተቋም አረጋግጧል።

@BoleMereja
13.5K views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ