Get Mystery Box with random crypto!

Top Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja T
የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @topmereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.48K
የሰርጥ መግለጫ

-ማስታወቂያ ለማሰራት እና ለአስታየት :- @NatnaelAbreham1
የ Twitter አድራሻ : http://twitter.com/BoleMereja?t=watBbei5PnmgrUd80qQrnw&s=09
ዩቲዩብ : https://youtube.com/channel/UCXcMdhLzUAPeRAxW48JFClQ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-05-06 19:37:19
ሰበር

የዲቪ (DV) 2024 አሸናፊዎች ይፋ ተደረጉ።

ባሳለፍነው ጥቅምት እና ህዳር ወራት ላይ በበይነ መረብ አማካኝነት የተሞላው የ2024 ድቪ (DV) ሎተሪ ይፋ ተደርጓል።

ለዲቪ /DV/ 2024 ማመልከቻ የሞሉ በ https://dvprogram.state.gov/ESC/Default.aspx ብቻ ውጤቱን / ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።

በአ/አ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ "የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው / ኢሜይል / ቴክስት የምንልከው"  በሚል #የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁ አደራ ብሏል።

አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 50 ሺህ ሰዎችን በዲቪ (DV) ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።

@topMereja
14.0K views16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 18:26:14 ሰበር መረጃ

አሁን ነገሮች ተቀያየሩ ከጎንደር እስከ ባህርዳር  ተዘግቷል። መከላከያ በፋኖ ተሸንፎ እየሸሸ ሲሮጥ የሚያሳይ እና የሚያረጋግጥ ቪድዮ ይመልከቱ






12.6K views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 17:04:44
በአማራ ክልል በንፁሃን ዜጎች ላይ ግድያ፣ ሞት፣ ጅምላ እስርና መፈናቀል እየተፈጸመ እንደሚገኝ ኢሰመጉ አስታወቀ።

መንግሥትና የሚመለከታቸው አካላት ኹሉ በክልሉ ላሉ ውጥረቶች በቂ ትኩረት እንዲሰጡ ተጠይቋል።

@topMereja
12.0K views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 15:16:37
ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ከሃያ ሺሕ ጫማ ከፍታ በላይ መጓዝ የሚችል ሮኬት አስወነጨፈ

ቅዳሜ ሚያዚያ 28 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ለኹለተኛ ጊዜ  "አፄ ቴዎድሮስ 2015" የሚል ስያሜ የተሰጣትን ሮኬት ከሃያ ሺሕ ጫማ ከፍታ በላይ አስወንጭፎ ስኬታማ ሙከራ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በህዋ ምርምር ላይ ትኩረት በማድረግ ጋፋት የህዋ ምህንድስና ልማት ማዕከልንም አቋቁሞ የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል።

የማዕከሉ መሥራችና ሰብሳቢ በለጠ ጌታቸው፤ ሮኬት የማስወንጨፉ ሙከራ ከዚህ በፊት ከተሞከሩት የተሻለ ምርምር የተደረገበትና ለህዋ ሳይንስ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ተሸክሞ መሄድ የሚያስችል ቴክኖሎጅ የተገጠመለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ዘርፍ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ነው ያሉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው፤ በዩኒቨርሲቲው ተማሪና ተመራማሪዎች የተሠራው ሥራ ኢትዮጵያ እንደሰለጠኑት አገራት በህዋ ምርምር የበኩሏን ድርሻ እንደምትይዝ ጅምሩን ያሳየ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ ከሚካሄዱት የህዋ ሳይንስ ምርምሮች ውስጥ በሮኬት ሳይንስ ዘርፍ ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ  ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የአማራ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሉ አያሌው (ዶ.ር) እንደዚህ አይነት ሙከራዎች ኢትዮጵያ ወደፊት በዘርፉ ለምታደርገው ምርምር አጋዥ ናቸው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
__
@topmereja
13.1K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 14:43:20
ልዩ መረጃ !

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) #ኢትዮሪካ የተሰኘ አዲስ አልበም ሊለቅ ነው!

በቅርብ ቀን የሚወጣውን የተወዳጁ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ''ኢትዮሪካ '' አልበም በሰዋሰው መተግበሪያ እንደሚለቀቅ ተገልጿል።
#Ethiotelecom

@topMereja
11.2K views11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 11:31:35 #Ethiopia

ዛሬ 82ኛው ዓመት የኢትዮጵያውያን አርበኞች የድል በዓል እየተከበረ ይገኛል።

የአርበኞች የድል በዓል ለምን ይከበራል ?

ጣሊያን የዓድዋን ድል ለመበቀል በሚል በጊዜው ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤኒቶ ሙሶሎኒ አማካኝነት፥ ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም ድረስ ኢትዮጵያን ወራ ነበር።

በወቅቱ የነበሩት ኢትዮጵያውያንም ወራሪውን ሀይል ለአምስት ዓመታት በጽናት ታግለው 1933 ዓ.ም ድል ነስተውታል።

የወቅቱ አርበኞቻችን ለሀገራቸው ነጻነት የከፈሉትን መስዋዕትነት እና ያስገኙትን ድል ለማሰብም ነው በየአመቱ ሚያዚያ 27 የኢትዮጵያ አርበኞች የድል በዓል የሚከበረው።

እንኳን አደረሳችሁ !

@topMereja
12.9K views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 09:18:23 ሰበር መረጃ

በአማራ ክልል ዋና ከተማዋ ላይ በአሁኑ ሰዓት ከባድ ፍንዳታ ተከስቷል። ነገሮች በጣም ተባብሰዋል። ይህን የሚያሳይ እና የሚያረጋግጥ ቪድዮ ይመልከቱ





14.6K views06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 21:54:07
ሰበር መረጃ

የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ ዋጋን ለማረጋጋት በሚታገልበት ወቅት ባለፉት 16 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የወለድ ምጣኔን ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሳደገ።
የፌደራል ሪዘርቭ ቁልፍ የወለድ መጠኑን በ0.25 በመቶ ጨምሯል። ማዕከላዊ ባንክ ባለፈው መጋቢት ወር ከዋጋ ግሽበት ጋር መዋጋት ከጀመረ ወዲህ ይህ አሥረኛው የዋጋ ጭማሪ ነው።

ርምጃዎቹ በዓለም ትልቁ ኢኮኖሚ ያላት አሜሪካ ውስጥ የመበደር ወጪዎችን በከፍተኛ ሁኔታ አሳድገዋል፣ ይህም እንደ መኖሪያ ቤት ባሉ ዘርፎች ላይ መቀዛቀዝ እና በቅርብ ጊዜ ለሦስት የአሜሪካ ባንኮች ውድቀት ሚና ተጫውቷል። ይህ የዛሬው የወለድ ጭማሪ ለጊዜው የመጨረሻው ሊሆን እንደሚችል የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ አስታውቋል።

ከፍ ያለ የወለድ ተመኖች ቤት መግዛትን፣ ንግድን ለማስፋፋት መበደር ወይም ሌላ ዕዳ (ክሬዲት ካርድ) ለመውሰድ የበለጠ ውድ ያደርገዋል። ባለስልጣናት ወለድን መጨመር የተበዳሪዎችን የመበደር ፍላጎት እንደሚቀንስ እና ዋጋዎች እንዲቀዛቀዙ ያደርጋሉ የሚል እምነት አላቸው።

@topMereja
3.2K viewsedited  18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 18:44:34
ተከምሮ የተቀመጠ ኮንክሪት ፖል የ2 ህጻናትን ህይወት ቀጠፈ።

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 2ዐ ልዩ ቦታው እነራታ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ  በትላንትናው ዕለት የተከመረ ኮንክሪት ፖል ላይ ሲጫወቱ ከነበሩ አምስት ህፃናት ውስጥ ፖሉ ተንከባሎባቸው 2 ህፃናት ህይወት ማለፉን የከተማው ፖሊስ አስታውቋል።

ህይወታቸው ያለፈው የ15 እና16 አመት ህፃናት ሲሆኑ ሌሎች የ6 ፣የ8 እና የ1ዐ አመት የሚሆናቸው ሦስት ህፃናት ደግሞ በአካላቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸው ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የ1ኛ ፖሊስ ጣቢያ ሀላፊ ኮማንደር ጌትነት መስፍን ገልፀዋል፡፡

ፎቶ: ፋይል

@topMereja
5.5K views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 11:45:26
የ2024 ዲቪ ሎተሪ እድለኞች ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ይፋ እንደምታደርግ አሜሪካ አስታወቀች!

አሜሪካ በዓለም ላይ በየዓመቱ 50 ሺህ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ ወይም ዲቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ ሀገሯ ታስገባለች።ባሳለፍነው ጥቅምት እና ህዳር ወራት ላይ በበይነ መረብ አማካኝነት የተሞላው የ2024 ድቪ ሎተሪ አሸናፊዎች መታወቃቸው ተገልጿል።የዲቪ 2024 ማመልከቻ የሞሉ ዜጎችም መመረጣቸውን እና አለመመረጣቸውን የፊታችን ቅዳሜ ማለትም ከሚያዚያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በትዊተር ገጹ ጽፏል።

ኢምባሲው አክሎም በዲቪ ሎተሪ ድረገጽ ላይ በመግባት አመልካቾች ያመለከቱበትን ልዩ ቁጥር ወይም ኮድ በማስገባት ማወቅ ይችላሉም ብሏል።ይህ በዚህ እንዳለም የዲቪ ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁም አሳስቧል።

ለዲቪ ሎተሪ ስለማሸነፋቸው እና አለመድረሱን አመልካቾች በራሳቸው እጃቸው ላይ ባለው ሚስጢራዊ ቁጥር ማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ እንደሆነም ተገልጿል።የ2023 ዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች እስከ ቀጣዩ መስከረም 2016 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንደሚስተናገዱም ኢምባሲው በመግለጫው ላይ ጠቁሟል።የ2022 ዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መከሰቱን ተከትሎ የአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ግንኙነት በመሻከሩ ተጎድተናል ማለታቸው ይታወሳል።

@topMereja
7.5K viewsedited  08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ