Get Mystery Box with random crypto!

Top Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja T
የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @topmereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.48K
የሰርጥ መግለጫ

-ማስታወቂያ ለማሰራት እና ለአስታየት :- @NatnaelAbreham1
የ Twitter አድራሻ : http://twitter.com/BoleMereja?t=watBbei5PnmgrUd80qQrnw&s=09
ዩቲዩብ : https://youtube.com/channel/UCXcMdhLzUAPeRAxW48JFClQ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 95

2022-07-14 12:25:46
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዋስትና ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሐምሌ 13 ቀን 2014 ከሰዓት በኋላ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በዛሬው ቀጠሮ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዋስትና ሊፈታ አይገባም ክርክር ላይ ይግባኙን አድምጧል::

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ክርክሩን ሠምቶ ወሳኔ ለመስጠት ለሐምሌ 13 ቀን 2014 ቀጠሮ መስጠቱን የጋዜጠኛው ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ አስታውቋል::

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከታሠረ 49 (አርባ ዘጠኝ) ቀናትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም በስር ፍርድ ቤት በ100 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጣ ተወስኖለት እንደነበር ይታወሳል፡፡


@TopMereja
@TopMereja
8.6K views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 19:25:06
ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘ እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ሰራተኞች ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ

በአዲስ አበባ ከተማ ከ14ኛ ዙር የ20/80 እንዲሁም ከ40/60 3ኛ ዙር እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮና የቤቶች ቢሮ የተለያየ እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ሰራተኞች ሰዎች ስም ዝርዝር

1ኛ. ዶ/ር ሙሉቀን ሃብቱ ቢሮ ሃላፊ ከሃላፊነቱ የተነሳ
በቁጥጥር ስር የዋሉ፡-
1ኛ. አብርሀም ሰርሞሎ የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ
2ኛ. መብራቱ ወልደኪዳን :_ዳይሬክተር
3ኛ. ሀብታሙ ከበደ :_ሶፍትዌር ባለሙያ
4ኛ. ዬሴፍ ሙላት :_ሶፍትዌር ባለሙያ
5ኛ. ጌታቸው በሪሁን :_ሶፍትዌር ባለሙያ
6ኛ. ቃሲም ከድር :_ሶፍትዌር ባለሙያ
7ኛ. ስጦታው ግዛቸው :_ሶፍትዌሩን ያለማ
8.ኛ. ባየልኝ እረታ ፡_ሶፍትዌር ተቆጣጣሪ
9ኛ. ሚኪያስ ቶሌራ ፡_የቤቶች ኢንፎሜሽን ና ቴክኖሎጂ ባለሙያ
10ኛ. ኩምሳ ቶላ ፡_ የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳሬክተር ሲሆኑ

በቀጣይም ሂደቱን በመከታተል መረጃዎችን እንደሚያቀርብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት አመልክቷል።


@TopMereja
@TopMereja
10.9K views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 18:18:26
10.6K views15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 15:08:29
በአዲስ አበባ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ይደረጋል ተባለ

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
የቢሮው ሃላፊ አቶ ዳዊት የሺጥላ እንዳሉት በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የአዉቶብስም፣ የታክሲም የታሪፍ ማሻሻያ ይደረጋል፡፡

የማሻሻያ ዋጋዉም የታክሲ ትንሹ የ 50 ሳንቲም ጭማሪ ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ የ2 ብር ጭማሪ ለማድረግ መዘጋጀቱን ቢሮው አስታውቋል፡፡

በነዳጅ ላይ የዋጋ ጭማሪ ከተደረገ ወዲህ በተለይም ታክሲዎች በራሳቸዉ ታሪፍ እየጨመሩ ከተሳፋሪዎች ጋር አላስፈላጊ እስጠገባ ዉስጥ ሲገቡ ይስተዋላል፡፡


@TopMereja
@TopMereja
11.2K views12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 12:02:31
11.3K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 21:58:35
በጎንደር ከተማ ኤርትራውያንን የጫነ የመከላከያ መኪና ከፍተሻ አካላት ሲያመልጥ በቁጥጥር ስር ዋለ

ከጎንደር ከተማ በቅርብ ርቀት ከምትገኘው አምባ ጊዎርጊስ ከተማ ከ 31ኛ ክፍለ ጦር እንደመጣ በመግለፅ ሶስት ኤርትራውያንን የጫነ ኮድ 06580 መ.ከ ሰሌዳ የመከላከያ ሰራዊት መኪና ለመፈተሽ ፈቃደኛ ባለመሆንና ኬላ በመጣስ ለማምለጥ ሲሞክር በቁጥጥር ስር ውሏል።

ወደ ጎንደር ከተማ እየገባ የነበረው ይህ መኪና የአካባቢው የኬላ ተቆጣጣሪዎች ሊያስቆሙት በሚሞክሩበት ጊዜ በቦታው የነበሩ እንስሳትን በመግጨት ሊያመልጥ ሙከራ አድርጓል።በማምለጥ ላይ ያለው ተሽከርካሪ ከጎንደር ከተማ በ 3 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ወለቃ ቀበሌ ላይ 3 ኤርትራዊያን የጫነው ሹፌር ከነመኪናው በመከላከያ ሰራዊት ኃይል ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ሶስት ኤርትራውያንና የመኪናው አሽከርካሪ በጎንደር ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።

ምንጭ :- አዳስ ዘይቤ

@TopMereja
@TopMereja
13.2K views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 12:21:48
አለም ዛሬ እየተነጋገረበት ያለ ጉዳይ

የስነ-ፍጥረት ሁሉ መገኛ የሆነውን ዩኒቨርስ (universe) ውስጠት በግልፅ እና በጥልቀት የሚያሳይ ምስል በታሪክ ለመጀመርያ ግዜ ዛሬ ለእይታ ቀርቧል።

በናሳ ጄምስ ዌብ ስፔስ ቴሌስኮፕ አማካኝነት የተነሳው ይህ ምስል በአሜሪካው ፕሬዝደንት አማካኝነት ለአለም ይፋ የተደረገ ሲሆን የሰው ልጅ እስካሁን ወዳልሄደባቸው የፍጥረት ጥጎች ለመሄድ የመጀመርያው ሂደት ተብሎለታል። ተጨማሪ ምስሎች በአለም ዙርያ በቀጥታ በሚተላለፉ ፕሮግራሞች ዛሬ አመሻሹን እንደሚቀርብ ተጠቁሟል።

#Share #ሼር

@TopMereja
@TopMereja
13.2K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 12:16:37
12.7K views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 07:26:58
ሰበር መረጃ

ሁለት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ አባላት አቶ ሙሉቀን እና የቤቶች ልማት ቢሮ ወ/ሮ ያስሚን በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

የህዝብ እና የመንግስት እምነት የተጣለባቸዉ አደራ ወደ ጎን ትተዉ የደሃውን ቤት ባልተገባ መንገድ ሊያጭበረብሩ ሲሉ ተጠርጥረው ማምሻውን በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

#Share

@TopMereja
@TopMereja
13.4K viewsedited  04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:20:57
በአማራ ክልል ሁለት አጎራባች ዞኖች መካከል በሚገኙ ቀበሌዎች የተቀሰቀሰው ውጊያ እስካሁን አልቆመም

ውጊያው በጅሌ ጥሙጋ እና ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጎራባች ቀበሌዎች ያጋጠመ ነው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ ቀበሌዎች ግጭት መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።

ግጭቱ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በጤ ቀበሌን እና በኤፍራታና ግድም ወረዳ አርሶ አምባ (ዘምቦ) ቀበሌን በሚያጎራብቱ አጎራባች አካባቢዎች (ጎጦች) ያጋጠመ ነው፡፡ ቀበሌዎቹ ከአዲስ አበባ ደሴ በሚያልፈው አውራ የአስፓልት መንገድ ላይ በሰንበቴ እና ጀውሃ ከተሞች መካከል የሚገኙ ናቸው፡፡ ከትናንት ምሽት ጀምሮ በአጎራባች የቀበሌዎቹ አካባቢዎች የተኩስ ልውውጥ እንዳለ የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች አሁንም የማያቋርጥ የጥይት ድምፅ እየሰሙ መሆኑን ገልፀዋል።

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አንድ የኤፍሬታ ግድም ወረዳ ነዋሪ ከትናንት ረፋድ ጀምሮ በሁለቱ ቀበሌዎች አዋሳኝ አካባቢዎች ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንዳለ ገልጸው፤ በዚህም ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል፡፡ግጭቱ አካባቢ መሆናቸውን የገለጹት አቶ አህመድ የተረጋጋ ሁኔታ እንደሌለ በመጠቆም የፌዴራልና የክልሉ የጸጥታ አካላት ለመግባትና ሁኔታዎችን ለማረጋጋት፤ ወደ ግጭቱ የሚገቡ ሰዎችንም ለማስቆም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ በበኩላቸው በተጠቀሱት ቦታዎች ግጭት መቀስቀሱን ተናግረው ግጭቱ ሳይባባስ ለማስቆም ተጨማሪ ሀይል ወደ ስፍራው መላኩን ተናግረዋል፡፡ ከሁለት ወራት በፊት በዚሁ አካባቢ በተፈጠረ ተመሳሳይ ጥቃት በኤፍራታና ግድም ወረዳ ያለች ሞላሌ የተባለች መንደር ሙሉ ለሙሉ መውደሟም የሚዘነጋ አይደለም፡፡

@topMereja
13.7K viewsedited  18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ