Get Mystery Box with random crypto!

Top Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja T
የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @topmereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.48K
የሰርጥ መግለጫ

-ማስታወቂያ ለማሰራት እና ለአስታየት :- @NatnaelAbreham1
የ Twitter አድራሻ : http://twitter.com/BoleMereja?t=watBbei5PnmgrUd80qQrnw&s=09
ዩቲዩብ : https://youtube.com/channel/UCXcMdhLzUAPeRAxW48JFClQ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-08-25 08:53:11
የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ይሰበሰባል።የወቅቱ የክልሉ ፕሬዝደንት ዶ/ር ይልቃል ከፈለን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ትናንት ከሰዓት በኋላ ባህርዳር መግባታቸው ታውቋል።በዛሬው የምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ ሹም ሽር እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

የምክር ቤቱ ሂደት እና ውሎ በተከታዩ ቻናል ወደ እናንተ ይደርሳል። Subscribe በማድረግ ተቀላቀሉ።

https://youtube.com/c/BoleMereja
12.6K viewsedited  05:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-23 16:57:34 ሰበር ዜና ጀነራል አበባዉ ላይ ግድያ! እና ሌሎች 4 ሰበር መረጃዎች


13.8K viewsedited  13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-23 09:30:13 ሰበር መረጃ

በልዩ ሁኔታ ሰልጥነዋል የተባሉት የሪፓብሊካን ጋርድ ኮማንዶዎች ተማረኩ። ይህን የሚያሳይ እና የሚያረጋግጥ ቪድዮ ይመልከቱ






13.2K views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-21 20:13:10
የታሰሩት የምክር ቤት አባላት የት ናቸው ?

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተያዙ የም/ቤት አባላት ታስረውበት ከነበረው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የማቆያ ቦታ እንደሌሉ እና ያሉበትን ቦታ ማወቅ እንዳልቻሉ ከጠበቆቻቸው አንዱ ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንዲሁም በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ካሳ ተሻገር ዛሬ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ለቤተሰቦቻቸው ቢገለጽም፣ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።

በተጨማሪ እስካሁን ድረስ ቤተሰቦቻቸውም ይሁን ጠበቆቻቸው ሁለቱ ታሳሪዎች ያሉበትን ቦታ እንዳላወቁ ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ተናግረዋል።

ጠበቃ ሔኖክ ምን አሉ ?

" ዛሬ ፍርድ ቤት እንደሚያቀርቧቸው ከቤተሰቦቻቸው ሰምተን ፍርድ ቤት ተገኝተን ነበር፤ አልቀረቡም።

በኋላ ላይ ስናጣራ ይገኙበት በነበረው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ እንደሌሉ እና ለጊዜው ያላረገገጥነው ቦታ እንደተወሰዱ ሰምተናል።

ቤተሰቦቻቸውም ወደ እስር ቤቱ አስገብተውላቸው የነበሩ ንብረቶችን መውሰድ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል። በሐዘን እና በከፍተኛ የስሜት መሰበር ላይ ይገኛሉ።

አንዳንድ ቤተሰቦቻቸውም ሌላ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይችላል በሚል የመረበሽ ስሜት ውስጥ ናቸው።

11፡00 ሰዓት ላይ ሊነጋጋ ሲል ነው የወጡት'፣ 'ወደ አዋሽ ተወስደዋል'  ከሚል ያልተረጋገጠ ወሬ በስተቀር የት እንዳሉ አናውቅም ብለዋል።

@topMereja
15.0K views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-17 10:07:14
M-PESA፣ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንሺያል አገልግሎት ጀመረ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንሺያል አገልግሎት የሚሰጠው M-PESA ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ካገኘ ከሶስት ወራት በኋላ አገልግሎት መጀመሩን ዛሬ አስታውቋል።

ሁሉም የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞች M-PESA አገልግሎትን ለመጠቀም *733# መደወል ወይም በተዘጋጀው የሞባይል መተግበሪያ መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፥ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት በቂ ሙከራ ማድረጉንና ከተለያዩ ባንኮች ጋር የአጋርነት ስምምነት ማድረጉን እንዲሁም ወኪሎችንም መልምሎ ማሰልጠኑን በመግለጫው ጠቅሷል።

አገልግሎቱ አሁን ላይ በአንድሮይድ መተግበሪያ በአምስት ቋንቋዎች የቀረበ ሲሆን ለአይ ኦ ኤስ ተጠቃሚዎች በቅርብ ሳምንታት ውስጥ አገልግሎት ይጀምራል ተብሏል።

@topMereja
12.6K views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-15 20:00:07
በትግራይ ክልል 16 ወረዳዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ መታየቱ እና በአዝርእትና የተፈጥሮ ሀብት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ።

የትግራይ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ እንዳስታወቀው መነሻው የአፋር ክልል በረሃዎች ያደረገ የበርሃ አንበጣ መንጋ በትግራይ ሶስት ዞኖች በሚገኙ ወረዳዎች መንሰራፋት የጀመረው ካለፈው ሐምሌ 20 ጀምሮ ሲሆን እስካሁን ባለው በ79 የክልሉ የገጠር ቀበሌዎች የሚገኝ 35 ሺህ ሄክታር መሬት መሸፈኑ ተነግሯል።

@topmereja
13.7K views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 20:51:04
ሰበር ዜና ! መከላከያ ተመታ / ለአዲስ አበባ አዲስ ከንቲባ ሙሉ መረጃዉን ሊንኩን በመንካት ይመልከቱ




7.8K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 22:42:43
ሰበር ዜና!

ከምሽቱ 3:30 ጀምሮ በወልድያ ከተማ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በከተማዋ በተለይ ፒያሳ ዳቦ ቤቱ አከባቢ የተጀመረው የተኩስ ልውውጥ አድማሱን እያሰፋ በአሬሮ፣ በመናኸሪያው ጀርባ፣ በቲንፋዝ እና በማረሚያ ቤቱ አከባቢ ከባድ የሆነ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን ነው የአማራ ድምፅ ሚድያ የከተማዋ ነዋሪዎችን በማነጋገር ለማረጋገጥ የቻለው።

ምንጮቻችን አክለውም የተኩስ ልውውጡ በቡድን መሣሪያዎችም ጭምር የታገዘ ነው ያሉ ሲሆን፤ ነገር ግን ተኩሱ በማን እና በማን መካከል እንደሆነ ማረጋገጥ አልቻልንም ብለዋል።

ዘገባው የአማራ ድምፅ ሚዲያ ነው!

@topMereja
10.8K viewsedited  19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 13:11:17
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ !

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከ1 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችንም አሰመርቋል።

የምርቃት ስነ-ስርዓቱ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትርና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መላኩ አለበልን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልሉ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ ከ1ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 234 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ተብሏል።

@topMereja
11.2K views10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-17 19:00:40
ማህበራዊ ሚዲያዎች ያለ VPN መስራት ጀመሩ !

ለወራት ያህል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ተነስቷል።

#ቴሌግራም ፣ ዩትዩብ ፣ ፌስቡክ ፣ ቲክቶክ መሰል የማህበራዊ ሚዲያዎች ከወራት በፊት (የካቲት ወር 2015 ዓ/ም) በተጣለባቸው ገደብ ያለ VPN መስራት እንዳቆሙ ይታወቃል።

ዛሬ ሰኞ ከሰዓታት በፊት ግን እነዚህ የማህበራዊ ሚዲያዎች #ያለ_VPN_እየሰሩ እንደሚገኙ እና ገደቡም መነሳቱን #ማረጋገጥ ችለናል።

@topMereja
17.9K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ