Get Mystery Box with random crypto!

الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም

የቴሌግራም ቻናል አርማ tidar_be_islam — الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም ا
የቴሌግራም ቻናል አርማ tidar_be_islam — الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
የሰርጥ አድራሻ: @tidar_be_islam
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.49K
የሰርጥ መግለጫ

﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾
ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን
ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-05-14 20:37:20 ❥::::::::::ልዩ ናት:::::::❥

በሱና ያጌጠች በኢማን ያበበች
ከሽርክ ከቢዳአ ፈፅሞ የራቀች
በተውሒድ ታንፃ ጌታዋን ያጠራች
ሀያዕን ተላብሳ በሒጃብ፣በኒቃብ ያማረች

ለባሏ መከታ ለወንድሟ አለኝታ
ለአባቷ ክብር ለልጇ ተምሳሌት

ፈርጥ የአማኝ ሴት የዚህች
አይነት እንስት የእንቁዎች እንቁ
☞የውዶች· ልዩ ናት
:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
2.2K viewsedited  17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 20:31:20 ሴቶች በባሎቻቸው ላይ ያላቸው አምስት ሀቆች

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
2.1K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 11:13:18 ‏﷽
۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى
النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا
عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝ ﷺ

#ሰለዋት_እናብዛ ፤  እኛ በውዱ ነብያቺን ላይ 1 ሰለዋት ብናወርድ አላህ በኛላይ 10 ሶለዋት ያዋርድልናል ። صلى الله عليه وسلم

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
1.4K viewsedited  08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 18:15:52 ☞ የሴት ልጅ መስተካከልና መበላሸት።
☞ በባሏ ላይ ተፅእኖ ያሳድራሉ!!

ሀሰኑል በስሪይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ:–

“መካ ውስጥ ልብስ ሻጭ የሆነ ሰው ዘንድ ከርሱ ልብስ ለመግዛት ቆምኩኝ፣ እየማለ ልብሱን ማወደስ ጀመረ፣ ከሱ መግዛቱን ተውኩት፣ ከእንደዚህ አይነት ሰው መግዛቱም ተገቢ አይደለም አልኩና ከሌላ ሰው ገዛሁኝ፣ ከዚያም  ከሁለት አመት በኋላ (ወደዚያው) ጉብኝት  አደረግኩ፣ እርሱ ዘንደም ቆምኩኝ እየማለም እያወደሰም ሆኖ አላገኘሁትም፣ ለሱም እንዲህ አልኩት:– ያ  ከአመታት በፊት ያገኘውህ ሰው አይደለህምን? አዎ ነኝ አለ፣ ከዚህ በፊት ከነበርከበት ሁኔታ ወደ ምመለከትህ ሁኔታ ምን አወጣህ? እየማልከና እያወደሰክም ሆነህ አላይህም፣ አልኩት።

ለኔ አንዲት ሚስት ነበረችኝ፣ ትንሽ ነገር ይዤ ስገባ የምታመናጭቅና አሳንሳ የምታይ, ብዙ ይዤ ስገባ አሳንሳ ተየዋለች፣ ከዚያም አላህ አሞታት (ሞተች)።
ከሷ በኋላ ሌላ ሴት አገባሁ፣ ወደ ሱቅ መውጣት ስፈልግ ልብሴን ይዛ ከዚያም እገሌ ሆይ! አላህን ፍራ ጥሩ ነገር እንጂ አትመግበን፣ ትንሽ ብታመጣልን ብዙ አድርገን እንቆጥረዋለን/እናብዛዘዋለን፣ ምንም ይዘህ ባትመጣ እንኳን እናግዝሃለን፣ ትለኛለች።”
ምንጭ:– አል ሙጃለሰቱ ወጀዋሂር አል ዒልም 5/251
                                 ·

☞ጥያቄ ፦ በዱንያ ላይ መልካም የሆነች ሴት በአኺራ (በጀነት) ከሁረል ዐይኖች ትሆናለች ?
,
⇨መልስ ፦ በዱንያ ላይ መልካም የሆነች ሴት(ሚስት) በአኺራ ከሁረል ዐይን በላይ ትሆናለች ፣  ጠረኗም ተፈላጊነቷም ከሁረል ዐይኖች የበለጠ ይሆናል ለባለቤቷ ፤ ረሱልም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ በማለት ነግረውናል " ጀነት የሚገቡ የመጀመሪያ ጭፍራዎች ልክ እንደ ሙሉ ጨረቃ ያበራሉ " [ሼክ ሳሊሀል ዑሰይሚን(ረሂመሁላህ) ]
,
⇨ልብ በይ እህቴ ይህን ደረጃ ልታገኚ ምትቺይው በስራ እንጂ በምኞት ብቻአ  አይደለም !!!
,
#ሀያእ የሚያመጣው ጥሩን ነገር ብቻአ ነው!

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
990 views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 06:22:27
የቱንም ያህል ወንጀልህ ቢበዛ ሰይጣን ተስፋ እንዲያስቆርጥህ እድሉን አትስጠው ወደ አላህ ተመለስ ኢስቲግፋርም አብዛ።
#ጌታህ ይቅር ባይ ነውና።

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
2.1K viewsedited  03:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 06:17:00   በባህር የሰጠመችዋ  #ጀግና ሴት ልጅ

     አስገራሚ
#ታሪክ_ነው_ሼር_አድርጉ

ጥብቅ ጨዋ የሆነችው ሙስሊሟ ሴት ገላዋን በአደባባይ አታሳይም ስብእናዋን አታቆሸሽም ክብሯን አታሰደፍርም ለምን የህይወት መስዋእትነት ጭምር አያስከፍላትም በክብር አትደራደርም

#አል_ኸጣብ ዑዳለት አስሰማእ በተሰኘው መጽሐፋቸው ውስጥ እንዳሰፈሩት ከአርባ አመት በፊት በባግዳድ እንሰሳት እያረደ ሥጋ በመሸጥ የሚተዳደር አንድ ሰው ነበር ገና ሳይነጋ በፊት ወደ ሱቅ ይሄድና የሚሸጠውን በግ አርዶ በማዘጋጀት ወደ ቤቱ ይመለሳል ፀሐይ ከወጣች በኋላ ደግሞ ተመልሶ በመውጣት ሱቁን ይከፍታል ያዘጋጀውን ሥጋ ለመሸጥ  #ከዕለታት አንድ ቀን ሌሊት ላይ ሥጋውን አርዶ ሲመለስ በድቅድቅ ጨለማ በመመለስ ላይ እያለ በመንገዱ ላይ ከጨለማ ውስጥ የጨኸት ድምጽ ሰማ ባረደው የበግ ደም ልብሱ ተበላሽቶ ነበር ፈጠን ብሎ ድምፁን ወደ ሰማበት አቅጣጫ አመራ ወዲያውኑ በተደጋጋሚ በጩቤ የተወጋ አንድ ሰው ላይ ወደቀ ሰውዬው ደሙ በከፍተኛ ሁኔታ ይፈሰው ነበር ጩቤውም ሰውነቱ ላይ እንደተተከለ ነው ጩቤውን ነቅሎለት በእጁ ይዞ ሰውዬውን ለመርዳት ብሎ ሊሸከመው ተንደረደረ የስውዬው ደም ልብሱን አጠበው በዚሁ ሁኔታ ላይ እያለ ጨኸት የሰሙ ሰዎች ከያቅጣጫው ተሰባሰቡ ጩቤውን በእጁ ሲያዩና ልብሱ በደም የተጨማለቀ መሆኑን ሲመለከቱ እንዲሁም ሰውዬውም የደነገጠ መሆኑን በደም የተጨማለቀ መሆኑን ሲመለከቱ እንዲሁም ሰውዬውም የደነገጠ መሆኑን ሲያስተውሉ ሰውዬውን የገደለው እሱሰለመሆኑ እርግጠኛ ሆኑ ከዚያም እንዲገደል ወሰኑበት ግዲያው ወደሚፈፀምበት ቦታም ወሰዱት እንደሚገደል እርግጠኛ መሆኑን ባወቀ ጊዜ ድምፁንሸ ከፍ አድርጎ ጮኸ #ሰዎች_ሆይ ወላሂ ይህንን ሰውዬ እኔ አልገደልኩም ነገር ግን ከሀያ አመት በፊት ሰው ገድዬ ነበር በዚህ ወንጀል ምክንያት ዛሬ ቅጣት እየተፈፀመበኝ እንደሆነ ይገባኛል አላቸውና #ታሪኩን ማውጋት ጀመረ

ከሀያ ዓመት በፊት በባህር ላይ ጀልባ ሰዎችን የማመላልስ ወጣት ነበርኩኝ ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ሀብታም ወጣት ከእናቷ ጋር ሆነው ወደ ባህር ማዶ ለመሻገር መጡ እኔም አሻገርኳቸው በሁለተኛው ቀንም መጡና ጀልባዬ ላይ ተሳፈሩ አሻገርኳቸው ቀናት አለፉ ልቤ በዚህች ወጣት ላይ ተንጠለጠለ ወደድኳት እሷም ወደደችኝ እንዲድሩልኝ ብዬ ለአባቷ ሽማግሌ ብልክም በድህነቴ ምክንያት ጥያቄዬን ውድቅ አደረጉት ከዚህ እሷም ምን እንደገጠማት አላውቅም ብቻ ቀረች ተጠፋፋን እሷንም ሆነ እናቷን ለረጅም ጊዜ ማግኘት አልቻልኩም ልቤ ግን እንዳፈቀራት ኖረ
#ከሁለት_ወይም_ከሶስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ነበር አንድ ቀን ጀልባዬን ይዥ ተሳፋሪዎችን በመጠበቅ ላይ እያለሁ አንዲት ሴት ትንሽ ልጅ ይዛ መጣችና ወደ ዚያኛው ማዶ እንዳሻግራት ጠየቀችኝ ተሳፍራ መሃል ባህር ላይ በደረሰች ጊዜ ተመለከትኳት ያቺ አባቷ የለያየን ሴት መሆኗንም አወቅኩኝ ሰለገኘኋት ደስ አለኝ ያለፈውን ጊዜ አስታወስኳት #ፍቅር መቼስ የማይሸር እዳ ነው እሷ ግን ሰርዓት ባለው መልኩ አናገረችኝ እንዳገባችና የያዘችውም #ህፃን  መሆኑን አስረዳችኝ ቀስ በቀስ ሸይጣን በኔ ውስጥ ሥራውን ይሰራ ጀመር መጥፎ ነገርም አሳሰበኝ ተጠጋኋት ጮኸችብኝ #አላህን እንድፈራ አስታወሰችኝ ሆኖም ግን ማስጠንቀቂያዋ ምንም ግድ አልነበረኝም  እሷ የቻለችውን ያህል ትከላከል ትገፋኝ ጀመር ህፃን ልጇ ያለቅሳል ይህንን ባስተዋልኩ ጊዜ ይበልጥ እልህ ያዘኝ ልጇን ወሰድኩና ወደ ውሃው አስጠጋሁት ፈቃደኝነቷን ካልገለፀችልኝ አሰመጥዋለሁ ብዬ አስፈራራኋት አለቀሰች ለመነችኝ ተማፀነችኝ አልሰማኋትም የልጁን ጭንቅላት ይዥ ውሃ ውስጥ እየነከርኩ እየመለስኩ አስፈራራታለሁ እሷ ታለቅሳለች ትማፀናለች አልራራሁላት ልጁን አጥብቄ ውሃው ውስጥ ነከርኩት ትንሽምአቆየሁት እሷ ታያለች ክስተቱን ላለማየት #ዐይኗን ትሸፍናለች ልጁ ተንፈራፈረ ተልፈሰፈሰ ከውሃ ውስጥ ሳወጣው በድን ሆኗል #ሞቷል በድኑን ውሀሰ ውስጥ ወረወርኩት ከዚያም ተነሳሁና ወደሷ ሄድኩኝ በቻለችው ሁሉ ተከላከለችኝ ጮሃ አለቀሰች ፀጉሯን ይዠ በመጎተት ወደ ውሃ አሰጠጋኋት አየነከርኩ አስወጣታለሁ ደጋግሜ ባደርግም በእንቢተኝነቷ ፀናች በፍፁም አላደርገውም አለች እጄን ሲደክመኝ ነክሬ አቆየኋት እሷም እንደ ልጇ ሁሉ ተንፈራፈረች ከዚያም ፀጥ አለች ሞተች ውሃው ውስጥ ወረወርኳትና ተመለስኩኝ ይህንን ወንጀሌን አንድም ሰው ሳያውቅ ለዓመታት ኖርኩኝ ቢያቆይ እንጂ የማይረሳ የሆነው ጌታ ዛሬ ያለ ወንጀሌ ያዘኝ አላቸው ሰዎች ታሪኩን ሲሰሙ አለቀሱ አንገቱ ተቆርጦ እንዲገደልም አዘዙ #አላህ በዳዮች የሚፈጽሙትን ወንጀል የሚረሳ አይደለም እስቲ የዚህችን ወጣት #እናስተውል ዐይኗ እያየ ልጇ ለፊቷ ተገደለ እሷም ሞተች ይህ ሁሉ ለምን ሆነ #ክብሯን  ከማስደፈርና በዝሙት ከመዋረድ በሞት መገላገልን መረጠች ይህ ከጨዋ ሴቶች ታሪክ መጠነኛ ማሳያ ነው ብዙ ትምህርትም  እናገኝበታለን ።

#አደራ_እህት_ወንድሞቼ
እሄንን ድንቅ አስገራሚ የፀናት ታሪክ ሼር አደርጉ
     ለሙስሊም እህት ወንድሞች እናድርስ

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
3.0K views03:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 19:09:47 ::::::::መልክ::::::::

☞ ሕሊና እንጂ መልክ አያስብም፡፡
☞ አንደበት እንጂ መልክ አይናገርም፡፡:
☞ መልካምነት እንጂ መልክ ከሰው አያኖርም፡፡:
☞ ስነ ምግባር እንጂ መልክ አያስከብርም፡፡:
☞ እምነትና ፍቅር እንጂ መልክ ሞትን አያሻግርም፡፡:
☞ መልክ የላይ ማንነትን እንጂየውስጥ ሰብእናን አይገልጥም፡፡:
☞ ፊት ቀልቶ ውስጥ ሊጠቁር፣ውጪ አጊጦ ልብ ሊቆሽሽ ይችላል፡፡
እውነተኛ ፍቅር በአይን ሳይሆን በልብ ነው። እዉነተኛ ፍቅር ያለዉ
#በትዳር_ዉስጥ_ነዉ
አላህ መልካሙን ትዳር ይወፍቀን አሚን
#ከተመቸዎት_ሼር_ያድርጉ

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
3.5K views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 19:08:04 «በዲንሽ ላይ በሚደርስብሽ ስቃይና መከራ #ሶብር አድርጊ።»

በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
3.2K views16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 10:45:51 ❥☞ወንድሜ ጥሩ #ትዳር ትፈልጋለህ ❥☜ በዉስጥ መስመር ከመጃጃልህ በፊት እሄንን ፁሁፍ አንብበዉ

☞ ከፈለክ ኢማም አህመድ ኢብን ሀንበል (አላህ ይዘንላቸው) ልጃቸው
ሲያገባ የለገሱት ምክር ለኔ ብለህ ስማ
☞ ልጄ ሆይ እነዚህን አስር ነገሮች ለባለቤትህ መፈጸም ካልቻልክ
#በትዳር ህይወትህ ደስተኛ መሆን ስለማትችል ምክሬን ጠበቅ አድርገህ ለመያዝ ሞክር

1- )☞☞ሴት ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን ነገር ሳትሰስት አጋራት

2-)☞☞ ሴት ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች። (ባገኘከው አጋጣሚ) ፍቅርህን ከመግለጽ ወደኋላ አትበል

3- )☞☞ሴቶች ግትር ወንዶችን ይጠላሉ። ደካማ ወንዶችን ደግሞ ይንቃሉ አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር ለመሆን ሞክር።
4- )☞☞ሴቶችን መልካም ንግግር፡ ውብ ገጽታ፡ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ስለሚማርካቸው ሁሌም እነዚህ ነገሮች እንዲኖሩህ ጥረት አድርግ

5-)☞☞ ለሴት ቤቷ የቤተ መንግስት ያህል ክብር የምትሰጠው ስፍራ ነው። ቤቷ ስትሆን ዙፋኗ ላይ በክብር የተቀመጠች ንግስት ያህል ክብር ይሰማታል። በምንም ተአምር ይህን ቤተ መንግስቷን የሚያፈርስባትን ነገር እንዳትፈጽም።ከንግስና ዙፋኗ ላይ ልታወርዳትም አትሞክር። ይህን ካደረክ ንግስናዋን እንደመቃወም ይቆጠራል። ለንጉስ ንግስናውን ከመቀናቀን የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለምና ጥንቃቄ አድርግ።

6)-☞☞ ሴት የቱን ያህል ብትወድህም ቤተሰቧን ማጣት አትፈልግም። አንተን ከቤተሰቦቿ በላይ እንድትወድህ ለማድረግ አትጣር። ይህን
ማድረግ ፍጻሜው የማያምር ጠላትነትን ሊያመጣብህ ይችላል።

7)- ☞☞ ሴት ከጎንህ (ጠማማ አጥንት) መፈጠሯን አትዘንጋ። ይህ አፈጣጠሯ
የውበቷ ሚስጥር መሆኑን እወቅ። ትንሽ ስህተት ባየህ ቁጥር አቃናታለሁ
እያልክ እንዳትሰብራት ተጠንቀቅ። ስብራቷ ፍቺ ነው። ላቃናት ከሞከርኩ ትሰበራለች በማለትም የባሰ እንድትጠም መንገድ አትክፈትላት። መካከለኛ ሰው ሁንላት።

8- ☞☞ሴት አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች።(ስትናደድ)
ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል። ነገር ግን እንዲህ አደረገች
በማለት ብቻ እንዳትጠላት። ይህን ባህሪዋን ባትወድላት ሌሎች የሚስቡህ
ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት አትዘንጋ።

9-☞☞ ሴት አካላዊ ድካምና ስነልቦናዊ ጫና ሊያርፍባት ይችላል። በዚህን ወቅት አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) የግዴታ አምልኮዎችን
(ሰላትና
ጾም )
ሳይቀር ውድቅ አድርጎላታል። በዚህን ጊዜ እዘንላት። ትእዛዝ አታብዛባት።

10- ☞☞ሴት አንተ ዘንድ ያለች (የፍቅር) ምርኮኛህ መሆኗን አትዘንጋ።
ምርኮኛህን በጥሩ ሁኔታ ያዛት፡ እዘንላት በድክመቷ
(የምትፈጽመውን
ስህተት) እለፋት። ምርጥ የሂዎት አጋርህ ትሆናለች።”

ወንድሜ ደግመህ አንብበው!!

:::::::ቴሌግራችን::::::::

@Tidar_Be_Islam
@Tidar_Be_Islam
1.1K views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 06:38:37 ሴት ልጅ የማትፈልገውን እንድታገባ ማስገደድ

ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል።

የትኛዋም ሴት የማትፈልገውን ሰው እንድታገባ ከተገደደች ኒካሁ ውድቅ (ተቀባይነት የሌለው) ነው። ያስገደዳት አካል ወንድሟም ይሁን አጎቷ፣ አባቷም ይሁን አያቷ ያው ነው። ማንኛውም ሰው አንድን ሴት የማትፈልገውን አካል እንድታገባ ማስገደድ አይችልም። ልክ እንደዚሁ አቻዋ የሆነና የምትፈልገው ሰው ከመጣ ወልዮቿ መከልከል እንደማይችሉ ሁሉ "የማትፈልገውን እንድታገባ" ማስገደድም አይችሉም።

(فتاوى اللقاء الشهري [20] /فتاوى المرأة)

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
3.0K views03:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ