Get Mystery Box with random crypto!

الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም

የቴሌግራም ቻናል አርማ tidar_be_islam — الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም ا
የቴሌግራም ቻናል አርማ tidar_be_islam — الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
የሰርጥ አድራሻ: @tidar_be_islam
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.49K
የሰርጥ መግለጫ

﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾
ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን
ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-01-13 06:28:52 "አስታውሱኝም አስታውሳችኃለሁና":
የነቢዩ ﷺአስተናጋጅ የነበረው አነስ ኢብን ማሊክ በዘገበው ሓዲስ የአላህ መልእክተኛﷺ እንዲህ አሉ።

☞አንድ ሰው ለራሱ የሚወደውን ነገር ለሙስሊም ወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።”
{ሓዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
عَنْ أَبِي حَمْزَةَ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ خَادِمِ رَسُولِ اللَّهِ  ﷺ
عَنْ النَّبِيِّ ﷺ قَالَ: “لَا يُؤْمِنُ أَحَدُكُمْ حَتَّى يُحِبَّ لِأَخِيهِ مَا يُحِبُّ لِنَفْسِهِ”.
{رَوَاهُ الْبُخَارِيُّ  وَمُسْلِمٌ }

      ……… ………

﷽ {إنّ اللهَ وملائكتَهُ يُصَـلُّونَ على النبي يا أيها الذين آمنوا صَلُّوا عليه وسلِّمُوا تسليما} اللهم صلِ و سلم على نبينا محمد ﷺ
               
#መልከም_ጁማኣ

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
946 views03:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 06:24:20 :::::::::::እህቴ ሆይ:::::::::::::

#ትርጉም ያለዉ ሂወት የተረጋጋ ሂወት መኖር ከፈለግሽ የሚወድሽን ሰዉ ለይተሽ ማወቅ ይኖርብሻል..

☞አንድ ወንድ በአፉ ትት ስላለሽ ማመን የለብሽም ።
ትክክል ፍቅር የያዘዉ ወንድ ከአነጋገሩ ይታወቃል ...

☞የሚወድሽ እንጂ አንች የምትወጂዉ መምረጥ የለብሽም ለትዳር አጋሪሽ፣የትዳር አጋሪሽ ላንቺ ሁለ ነገርሽ ነው።
ፈገግታሽ ሚያስፈግገው ጭንቀትሽ ሚያሳስበው ነው፣
ስለዚህ ውዷ እህቴ አንቺ ምትወጂው እሱ ልቡ ከውጭ ያማትራልና እሱ ሚወድሽ ነው ላንቺ ምርጡ

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
969 views03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 20:43:39 وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَىٰ ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا
ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ!

(ሱራ አል-ኢስራእ 32)

ዝሙትን አትስሩት ብቻ አይደለም አሏሁ ታኣላ ያለው አትቅረቡት ነው!!!

ወጣት ሆይ አስተንትን አስተንትኚ
አላህ ሁላችንንም ይጠብቀን.አሚን

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
1.0K viewsedited  17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 21:31:44
☞ከአማኞች ሁሉ ምርጡ •ስነምግባሩ ጥሩው እና •ለባለቤቱም መልካም የሆነው ነው
#ረሱልﷺ

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ❞
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ❞
1.0K viewsedited  18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 21:05:13 ☞::::ፍቅር_በኢስላም::::☜

ጋብቻ በኢስላም ልዩ ትኩረት ከተቸራቸው ማህበራዊ ጉዳዮች አንዱ ነው። ጋብቻ ኢስላም ከሰጣቸው እና ካበረታታቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው። የነብያት ፈለግም ነው።

《•ኢስላም ለትዳር ድንጋጌና ስርአትን በመዘርጋት ትኩረት ሰጥቶታል። የባለ ትዳሮች መብት መከበር የጋብቻው ግንኙነት እንዲያጎለብትና እንዲረጋ ያደርጋል። በመንፈስ የተረጋጋ፤ በእምነቱ የፀና ፣ በሁሉም የማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ይሰጣል።

《•በጋብቻ ሰንሰለት የተቆራኘ ፍቅር አንድም ለስሜት አንድም የአምልኮ ዋጋ ያለው ነው። ከወንጀልም መጠበቂያ ነው። የረሡል ﷺ ሱና ነው።

《•የአላህን ዉዴታ በመሻት በምትለግሰው ምፅዋት ምንዳ ታገኛለህ ሌላው ቀርቶ ለባለቤትህ በምታጎርሳት ጉርሻ እንኳ ምንዳ አለህ አንቺም ምንዳ አለሽ።

《•አልሃምዱሊላህ ከኢስላማዊ ድንጋጌዎች መካከል ኢስላም ለአንድ ጋብቻ ትክክለኛነት በባልም ሆነ በሚስት በኩል የግድ ሊሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን አስቀምጧል። በሀይማኖቷና በባህሪዋ ጠንካራዋን እንድንመርጥ ይመክራል።

《•ምክኒያቱም ወደፊት ለልጆችህ እናትና ተንከባካቢ፣ ለአንተ ደግሞ በመልካም ነገር ላይ የምታግዝህና የምታጠናክርህ በመሆኗ ነው።



《• ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ባለ ሀይማኖቷን (ዲን ያላትን) ምረጥ አለያ እጅህ አመድ አፋሽ ትሆናለች። (አል ቡኻሪ 4802 /ሙስሊም 1466)

《• ባለቤትህ ጥብቅና ጨዋ መሆን አለባት። በዝሙትና በእንዝላልነት የምትታወቅ ሴትን ማግባት ክልክል ነው። አላህ ﷻ እንዲህ ይላል፦ ከምእመናት ጥብቆቹም ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ (ተፈቀዱላችሁ) አል ማኢዳህ 5፡5

《•ለዘላለሙ ሊያገባቸው እርም ከተደረጉ መሀሪሞች መካከል መሆን የለባትም። አንዲት ሴትን ከእህቷ ወይም ከአክስቶቿ ማለትም ከአባቷ እህት ወይም ከእናቷ እህት ጋር በአንድ ላይ ማግባት አይፈቀድለትም።

《•በጣምራዎች መካከል ፍቅር ሳይኖር ሳይዋደዱ አይሆንም በጭራሽ ፍቅር አንዱ ህይወታችን ነው። ሁሉመ ሰው ወደርሱ ይሮጣል ምድርን በሙሉ በቀኝም በግራ ፍቅርን ይፈልጋል። የሚወደውን ሲያጣ በጣም ያዝናል። አላህ ﷻ ይወደናል ፣ ይጠብቀናል፣ ይምረናል፣ ምንም ጥላቻ የሌለበት ላጣኸው ነገር አትዘን /አትዘኝ/ አላህ ማንንም አይበድልም።

《• ረሡል ﷺ አንዲት ሴት የምታጠባው ልጅ እሳት ላይ እንዲወረወር ትፈልጋለችን?አሉ "ላ ላ ላ" ያረሡለሏህ ሲሏቸው አላህ ከዛም በላይ አዛኝ ነው። አሉ

《•የምትወዱትን ስታጡ አላህን አመስግኑ ለበጎ ነው። የሰው ልጅ ሀብታም፣ ደሃ፣ የተማረ፣ መሀይም..አለ ሁሉም ፍቅር ፈላጊ ነው።

《• ፍቅር የሰው ልጅ ሲከተለው እንደ ኳስ የሚንከባለል ይመስላል ፣ተስፋ እንቆርጣለን። ፍቅር አይንከባለልም የሚንከባለለው የሰው ልጅ ነው። የወደደ፣ ያፈቀረ፣ ጆሮው ሰምቶ ደንቆሮ ፣አይኑ አይቶ እውር ይሆናል፤ ፍቅር ሳይሆን እውሩ የሰው ልጅ ሲያፈቅር ባፈቀረው ሰው ምክኒያት የፈረደበት ደካማ ጎን ነው።

《• ምክኒያቱም፦ የሰው ልጅ ከፍተኛ ቦታ ለፍቅር ስለሚሰጥ። ወንድ ልጅ በፍቅር ምክኒያት ትንሽ ሊለዝብ ይችላል ሴት ልጅ ግን መለዘብ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ አቋሟን ለእርሡ ብላ ትለውጣለች።

《• ሴት ልጅ ትዳሯን ቤቷን እንደ ቤተ መንግስት ነው የምታየው። ሴት ልጅ ሹመት ቢሰጣት አንድ ወንድ የሚያፈቅራትን ያክል ክብርና ኩራት አይሰማትም። ሴት ልጅ እውነተኛ ፍቅር ከያዛት ከልብ የሚያፈቅራት ወንድ ካገኘች ቤተ መንግሥት ውስጥ አለምን ከሚመራው ንጉስ የበለጠ ደስታ ይሰማታል።

ወንድ ልጅ ፍቅር በአይኑ ይገባዋል። ይህ ማለት ወንድ ልጅ ባገኘው አጋጣሚ፣ የተዋበች ቆንጆ ልጅ ሊያፈቅር ይችላል። በውበትም በአልባሳትም፣ በብልጭልጭ ነገሮች ላይ ሁሉ አይኑ ያርፋል

《• ሴት ደግሞ በጆሮዋ ነው ፍቅር የሚገባት ጥሩ ነገር የሚያወራትን፣ ባገኘው አጋጣሚ ፍቅሩን የሚገልፅላትን፣ ሲያስከፋት ይቅርታ የሚጠይቃትን ስጦታ (ሲዋክ ) እንኳ ቢሆን የሚገዛላትን እና ደግሞ ስታወራው በቁም ነገር የሚያዳምጣትን፣ ባታወራው እንኳ ፊቷን አይቶ መከፋቷን የሚረዳት ችግሯን ሳታወራው የሚፈታላት ትወዳለች።

《• ወንድ ልጅ አቀባበልን ይወዳል። ከውጭ ሲመጣ #ተኳኩላ_ምግብ_ሰርታ ማታ ከሆነ ልጆቿን አስተኝታ የምትጠብቀውን ሴት ይወዳል።

《•ባል እና ሚስት ከተሳካ የሚዋደዱ ቢሆኑ ይመረጣል። ግን እንደ እድል ሆኖ ባል እና ሚስት ሁሉም ባይሆን ብዙዎቹ የሚዋደዱ (የሚፋቀሩ) አይደሉም። ነገር ግን ትዳር በራሱ የራሱ ህግ ስላለው ተከባብረው ተደማምጠው ብዙ ልጆች ወልደው አብረው አርጅተው ይሞታሉ።

《• ትዳር የብዙዎች ፍላጎት ቢሆንም ለጥቂቶች ብቻ ነው የሚሳካው። አንዲት እንግሊዎት የመንግስት ልጅ ነበረች። ከአባቷ በጣም ብዙ ንብረት ወረሰች፣ እርሷ ግን ገንዘቧን አስቀምጣ ደሃ አገባች። አንድ ድሀ የሆነ በዜግነቱ ህንዳዊ አገባች። እቤቱ ወሰዳት ግን የምትፈልገውን ፍቅር አላገኘችም ተፈታች። ከዛም በኋላ እንግሊዛዋ ዶክተር አገባች ተፈታች። ፈረንሳዊ አገባች ተፈታች። ብዙ ባል አገባች ተፈታች። #በመጨረሻ_ግን_በጣም_ጥሩ_ትዳር_አገኘች ወለደች።

《•ከዛ አንቺ እጅግ በጣም ሀብታም ነሽ ለምንድን ነበር እያገባሽ የምትፈችው በማለት ተጠየቀች። እሷም ጥሩ ህይወት እና የሚወደኝ እና የምወደው ባል ፈልጌ ነው አለች። የሚያግዘኝን የሚመቸኝን እየፈለግኩ ትዳር በገንዘብ ብዛት አይሳካም መተጋገዝን ፍቅርን ይጠይቃል።

《• ከሚወድሽ ወይም ከሚወድህ ሰው ጋር መኖር እረፍት ነው። ከደስታ ሁሉ ደስታ ከሚወዱት ጋር መኖር ነው። ለብዙዎች ባይሳካም ተስፋ አትቁረጡ ብዙ የለፉበት ነገር ትርፍ አለው።

#አንዳንድ_ሰዎች_መፍትሄውን እጃቸው ላይ አስቀምጠው እየረዱህ እንደሆነ ለማስመሰል ይጥራሉ።

#ለአንተ የሚያስፈልግህን ወሳኝ ነገር ከመስጠት ይልቅ ስትጣጣር ትንሽ ጥቅም ያለው ነገር ይመርጣሉ።

#በቀላሉ ማዳን እየቻሉ በቀላሉ ያጠፉሀል።

#ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ ውስጥ ሆነህ ስትጣጣር ከማገዝ ይልቅ "አብሽር አይዞህ" እያሉ ምንም ሳያግዙህ አቅምህን ያስጨርሡሀል።

《• በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ ስትሆን አላህን አስታውስ እርሡ አላህ በጥቁር ጨለማ፣ በጥቁር ድንጋይ ላይ የምትራመድን ጥቁር #ጉንዳን_የእርምጃዋን_ኮቴ_የሚሰማ ታላቅ ጌታ ነውና! እርሱን ለምን (ተማፀን) በእርሡም ተመካ!

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ❞
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ❞
1.3K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 12:19:15
"በዚች ምድር ላይ እንደ ረሱል ﷺ ያፈቀረ እንደሳቸውም የተፈቀረ የለም። ወደፊትም አይኖርም!
ሰሉ አለ ነቢ አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ነቢይና ሙሀመድﷺ

መልካም ጁምዓ
:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
1.5K viewsedited  09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 18:37:12 ❥...ባልሽ ካንቺ ሚፈልጋቸው ነገሮች..❥

1☞, በይፋም ሆነ በድብቅ አላህን በቅን ልቦና መታዘዝ አላህ ከሰዎች ጋር ያለንን ሁኔታ እንዲያሰተካክል እኛ ከአላህ ጋር ያለንን ሁኔታ እናስተካክል

2,☞ እሱ በሌለበት ራስሽን፣ንብረቱን፣ልጁቹንና ቤቱን ተንከባከቢ

3, ☞ሲመለከትሽ የተዋብሽ ሁኚ፣ሲያወራሽ አስተሳሰብሽን ቅን አድርጊ፣ፈገግታ ልመጂ

4,☞የትም ስትሄጂ ፍቃድ ጠይቂ፣ባደረገልሽ ነገር አመሰግኚ፣እሱን አንዳች ነገር ለመጠየቅ ስትፈልጊ አመቺ ጊዜ ምረጪ

5,☞ከቤት ስትወጪ ሂጃብሽን ጠብቂ፣በችግሮ ጊዜ ታገሺ፣በፀጋ ጊዜ አታባክኚ፣ከውሸት ተጠበቂ፣ከንዴት ብስጭት ለመራቅ ሞክሪ

6,☞ከኩራትና ራስወዳድ ከመሆን ተቆጠቢ፣እዚህች አለም ብቻ ሳይሆን በቀጣዩም አለም የማረ ህይወት እንዲገጥመሽ በኢባዳሽ በርቺ

7,☞ከአላህ ተሰፍ ማትቆርጥ ጠንካራ ሁኚ፣አንቺ ከእሱ ላይ ካለሽ ሃቅ እሱ ባንቺ ላይ ያለው ሃቅ በላጭ መሆኑን የተረዳች ሁኚ

8,☞ስህተትሽን አትካጂ፣ካጠፍሽ ይቅርታን ልመጂ፣ዚክር አብዢ፣ከእሱ በኩል ማገኘት የፈለግሺውን አቅም በፈቀደ መልኩ ጠይቂ

9☞,ባለቤትሽ አጠገብ ሌሎች ሴቶች ከማድነቅ ተቆጠቢ፣የእሱን ፍላጎት ሁሌም አስቀድሚ

10,☞በህሪውን ተረጂ፣በኢባዳ አበርቺው፣አይዞህ በይው።
#ሼር

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
1.0K views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 18:28:28 ☞  ጥሩ ሕይወትን ለመምራት☜

ጥሩ ሕይወትን ለመምራት የሚረዱ 10 መርህዎች
1 )ሰውን አትጥላ ልብህን ንፁሕ አድርግ።
2 አትጨነቅ በአላህ ተመካ
3)ቀለል ያለ ኑሮ ኑር

4) ባለህ ነገር ተደሰት በተሰጠህ ነገር አመስጋኝ ሁን።
5 )ብዙ በሰጠህ ቁጥር ብዙ ታገኛለህ።

6) ፈገግታ አብዛ ፈገግታ ሰደቃ ነው።
7) በፍቅር ኑር ለአላህ ብለህ ውደድ።
8) ዱዓን አብዛ ብዙ ዱዓ ባደርክ ቁጥር፤በረካን ታገኛለህ።

9)  እውቀትህን ለሌሎች አካፍል አንድ የቁርአን አንቀጽም እንኳን ብትሆን።
10). አላህን በብዛአስታውስ፤ልብህ እርጋታን ታገኛለች አላህ ያግራልን!!!
#ሼር_አድርጉ
:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
1.1K viewsedited  15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 20:41:37
⇨ምናልባት አንዳንድ ጊዜ የአላህ ፈቃድ
ፍላጎትህ ላይ ተቃራኒ ሊሆን ይችላል,

ነገር ግን ከታገስክ የአላህ ምርጫ ላንተ
የበለጠና የተሻለ እንደሆነ ትረዳለህ።
ስለዚህ ለማጋጥምህ ፈተና ሁሉ ሶብር
አድርግ።ኢንሻአላህ የተሻለዉን ትወፈቃለህ እና። #ሼር

::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ❞
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ❞
2.0K viewsedited  17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 20:32:07 "ሴት ልጅ ትክክለኛውን ደስታ
የምታገኘው ቤት ውስጥ ስትሆን ነው"

በኢስላም፦ ሴት ልጅ ያለ በቂ ምክንያት ከቤት እንዳትወጣ የወጣችም እንደሆነ ከባእድ ወንዶች ጋር እንዳትቀላቀል የማይፈቀድላት ወንዶችንም አትኩራ ከመመልከት ዓይኗን ሰበር ታድርግ " መባሉ
ሴትን መበደልና ነፃነቷንም መግፈፍ ነው የሚሉ አሉ!
ታድያ ጀነት ውስጥም ነፃነት የለም ማለት ነው! ?
( فِيهِنَّ قَاصِرَاتُ الطَّرْف لَمْ يَطْمِثْهُنَّ إِنْسٌ قَبْلَهُمْ وَلَا جَانٌّ )
[ጀነት ውስጥ ከባሎቻቸው በፊት ሰውም ይሁን ጂን ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን ባሎቻቸው ላይ ያሳጠሩ የገደቡ ፣ሴቶች አሉ] አርረሕማን 56
( (حُورٌ مَقْصُورَاتٌ فِي الْخِيَامِ)
[ ጀነት ውስጥ ጠባየ መልካሞች መልክ ውቦች ሴቶች አሉ ከዕንቁ በተሰሩ ድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ < የተገደቡ መውጣት የማይፈልጉ ናቸው የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣትም ደማቅ የኾኑ ናቸው] አርረሕማን 71 / 73
~ እህቴ ሆይ አትታለይ ላንቺ የሚበጀውን ከማንም በላይ አሏህ ነው የሚያውቀው አስተሳሰብሽን አስተካክይ!

::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ❞
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ❞
193 viewsedited  17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ