Get Mystery Box with random crypto!

الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም

የቴሌግራም ቻናል አርማ tidar_be_islam — الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም ا
የቴሌግራም ቻናል አርማ tidar_be_islam — الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
የሰርጥ አድራሻ: @tidar_be_islam
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.49K
የሰርጥ መግለጫ

﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾
ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን
ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-02-01 00:17:34 ☞እርሷ እንኳን ጀነት ውስጥ ናት!☜

ኻሊድ ኢብኑ ሰፍዋን በበስራ መስጂድ ውስጥ የተሰበሰቡ ሰዎችን በማግኘት ለምን ጉዳይ እንደተሰበሰቡ ይጠይቃል።በአንዲት ሴት በኩል ትዳር የሚፈልጉ በርካታ ሴቶች ወደ መስጂድ መምጣታቸውን ነገሩት።ይህንን የሰማው ኻሊድ ወደ ሴቲቱ ይቀርብና ከሴቶቹ አንዳን ማግባት እንደሚፈልግ ሲነግራት ምን አይነት ሴት ማግባት እንደሚፈልግ ጠየቀችው።

ኻሊድ የምፈልጋት ሴት "ድንግል የሆነች፣ ግን ደግሞ እንደባለትዳር ሴት ብልህ የሆነች ወይም አግብታ የነበረ ግን እንደልጃገረድ የዋህ ጭምቅ የሆነች፣አጠገቧ ሲሆኑ ጣፋጭ ሲርቋት የምትናፈቅ፣ቀደም ብላ በድሎት ትኖር የነበረ ቡሀላ ድህነት የቀመሰች በዚህም ምክንያት ሀብታምም ሆነ ደሀም ባህሪ ያላት ፣ሀብታም ስንሆን የምድራዊ ሰዎች ገፅታ የሚኖራት ስንደሀይ ደግሞ የጀነት ሰዎች ስነ ምግባር የሚኖራት" አላት።

ሴቲቷ መስፈርቱን ካዳመጠች በሃላ "ላንተ የምትሆን እንዲህ አይነት ሴት አውቃለሁ" አለችው። እሱም በጉጉት "የት አለች ታዲያ?" ሲላት እሷም "እርሷ እንኳን ጀነት ውስጥ ነው የምትገኘው።ስለዚህ እንዳታመልጥህ በርታ" በማለት መለሰችለት።

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
279 viewsedited  21:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 10:46:38 :::::::::ሙሲባ:::::::::

ኡሙ ሰለማ አላህ ስራዋን ይውደድላትና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ሲሉ ሰማሁ አለች:

☞ሙሲባ ሲደርስበት

إنا لله وإنا إليه راجعون
اللهم آجرني في مصيبتي
واخلف لي خيرا منها

"እኛ የአላህ ነን! ወደእርሱም ተመላሾች ነን!
አላህ ሆይ በደረሰብኝ ነገር ምንዳን ፃፍልኝ!  ከእርሱ የተሻለም ተካልኝ"
ያለ ሰው አላህ ደግሞ በደረሰበት ነገር ምንዳን ፅፎለትና ከእርሱ የተሻለም ቢተካለት እንጂ አይተወውም አሉ።

☞አስከትላም ኡሙ ሰለማ እንዲህ ትላለች:
አቡ ሰለማ (ባለቤቴ) በሞተ ግዜ " ወደመልክተኛው ﷺ በመጀመሪያ የተሰደደው ቤት ሆኖ ሳለ ከአቡ ሰለማ የተሻለ ከሙስሊሞች ማን አለና (አላህ ማንን ይተካልኛል?) " አልኩ!

አላህ ደግሞ ከእርሱ (አቡ ሰለማ)  የተሻለ የአላህ መልክተኛን ﷺ ተካልኝ።"

ሙስሊም፣ አቡ ዳውድ እና ነሲ ኢ ዘግበውታል
:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
3.2K views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 22:21:49 ☞::::ሙስሊም ሴት::::☜

ሙስሊሟ ሴት ከጋብቻ ትስስር በኃላ
1) መታዘዝ ፡- አማኟ ሴት የአላህን ትእዛዝ በመጣስ ላይ እስካልሆነ ድርስ ለባሏ ታዛዥና እርሱንም ተንከባካቢ ነች።
በርግጥም ደግሞ ባል በሚስቱ ላይ ያለው መብት ከምንም በላይ ነው። ከወላጆቿም ጭምር!
እናም... አማኟ ሴት ይህን በወጉ ተገንዝባ የባሏን መብት አቅሟ በፈቀደው ሁሉ የምትፈጽም ነች።
ይህን ከሚያስረዱ በርካታ መረጃዎች መካከል የሚከተለው
አቡ ሁረይራ ያስተላለፉት የረሱል (ﷺ) ሀዲስ ይገኝበታል።
እንዲህ ብለዋል ፡-
«አንድ ሰው ለሌላ አካል እንዲሰግድ ባዝ ኖሮ ሴትን ልጅ ለባሏ እንድትሰግድ አዝ ነበር»
(ቲርሚዚይ ዘግበውታል)
አዎ! አማኟ ሴት ባሏን ስትታዘዝ ለአላህና ለመልዕክተኛው ስትል እንደሆነ ጠንቅቃ ታውቃለች። እናም በዚህ ጉዞ ላይ መሰናክሎች ቢፈጠሩባት እንኴን ሙሉ በሙሉ ግን ከታዛዥነት አታፈነግጥም። እንዲያውም ትክክለኛ ታዛዥነቷ
የሚረጋገጠው በዚህ ቀውጢ ወቅት ነው። በተለይም፤ ኖሮት ሲያደርግላት፣ አግኝቶ ሲያቀማጥላት፣ ሳይመፃደቅ የፈለገችውን ሁሉ ሲያደርግላት የሚኖር ባል ከሆነ ደግሞ ብዙ ማድረግ ይጠበቅባታል። ሌላው ቢቀር ይህ ውለታው ራሱ ተግባራዊ ምስጋናን ይፈልጋልና።
መብቷን ሲያጎድል ታግሳ፤ እጅ ሲያጥረው አይዞህ ብላ፤ ሲቸግረው ያልፋል ብላ ተብቃቅታ መኖሯ፤ ብሎም ታዛዥነትን መተግበሯ በትክክል ለአላህ ብላ ኢኽላስንም መሰረት አድርጋ እንደምትኖር አነላካች ነው። ለዚህ ምሳሌ ከሚሆኑት እጹብ ድንቅ እንስቶች ውስጥ ፋጢማ ቢንት ሙሀመድ ( ﷺ ) በቀዳሚነት ትጠቀሳለች፡፡
ከእለታት አንድ ቀን ለውድ ባለቤቷ አሊይ ቢን አቢጣሊብ (ረድየላሁ ዐንሁ) እህል በምትፈጭበት ሰአት በእጇ ላይ የሚደርሰውን ህመም አጫወተችው። የባለቤቱን መብት ጠባቂ ተንከባካቢና አፍቃሪ የነበረው ውድ ባሏም አሊይ (ረድየላሁ ዐንሁ) ወደ አባቷ ሄዳ የምታግዛት ሰራተኛ እንዲሰጧት እንድትጠይቅ አመላከታት። እርሷም ሄደች። ነገር ግን ለመጠየቅ እፍረት ይዟት ተመለሰች። ከዚያም አሊ (ረድየላሁ ዐንሁ) እራሱ በመሄድ ጠየቃቸው። ነገር ግን የአላህ መልክተኛው ( ﷺ ) የጠየቁትን አልሰጧቸውም።
ግና ወደ እነርሱ በመምጣት እንዲህ አሏቸው ፡- «ከጠየቃችሁት የበለጠ ነገር ላስተምራችሁን? በመኝታችሁ ላይ ስትሆኑ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ሱብሀነላህ፣ አልሀምዱሊላህ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላሁ አክበር ሰላሳ አራት ጊዜ በሉ። ይህ ለእናንተ ከአገልጋይ የበለጠ ነው!»
አዎ! ልክ እንደዚሁ ነው አማኟ ሴት ደስታንም ሃዘንንም ከውድ ባሏ ጎን በመቆም የምታሳልፈው። ታዛዥነት ሲባል ከላይ እንደተጠቀሰው ጠቅልል ባለ መልኩ ሲሆን የተወሰኑ ነጥቦችን ብቻ በዚህ ዙሪያ እንመልከት፦
==> እርሱ ያልፈለገውን ሰው ቤቱ አታስገባም
==> እርሱም ባለበት ግዴታ ያልሆኑ ጾሞችን አትጾምም::
ማስረጃ የሚከተለው አቡ ሁረይራ ያወሩት ሃዲስ ነው የአላህ መላክተኛ ( ﷺ ) እንዲህ ብለዋል ፡- «ለአንዲት ሴት ባሏ ባለበት (ሱና) ልትጾም አይፈቀድም።


:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
6.2K views19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 22:21:03 ፍቅረኛ መያዝ ከሚያመጡብን መዘዞች

ክፍል ስድስት

ቦይ-ፍሬንድ እና ገርልፍሬንድ ግንኙነት ሴቶችን ወደ ወሲባዊ ዕቃነትና እና የስሜት ማራገፊያ ሸቀጥነት ለመለወጥ ታስቦ የተወጠነ ሴራ ነው፡፡ በተፈጥሮ አንድ ወንድ አንዲትን ሴት በቀጥታ ለዝሙት ቢጠይቃት እርሷ በተፈጥሯዊ ስብዕናዋ ላይ ከሆነች እሺ አትለውም፡፡ ግና አሁን በተዘረጋው ሰይጣናዊ መረብ እርሷ የወደፊት ትዳሬን በዚህ አጋጣሚ እውን አደርገዋለሁ በሚል ምኞት ለገርልፍሬንድነት ስትጠየቅ እሺ ትላለች፡፡ በዚህ ዓይነት አካሄድም ቦይ-ገርልፍሬንድ ግንኙነት ሴቷን ለወንዱ የስሜት ማራገፊያ ያደርጋታል፡፡
      
Please ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
    ቢያንስ ለ10 ጓደኞቻችሁ ፎርዋርድ አድርጉ

ከዚህ ለመውጣት ከአለሰህ በታች እገዛ ለሚያስፈክጋችሁ ወይም በዚህ ጉዳይ ጥያቄ ካላችሁ መመካከር እ  ችላለን ሚስጥራችሁ የተጠበቀ ነው።
@jezakellah 
         
 የዝሙት ሌላኛው ስሙ የሃራም ፍቅር ነው!!
በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል
ይቀላቀሉን


https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
4.9K views19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 06:33:21 ::::ባለቤትህን አትጉዳት:::

በምታጠፋ ጊዜ በፍቅር ቀርበ ህ በሰራችው ስራ እዳዘንክና  ደግማ እንዳት ፈፅምው  ምክር ስጣት ለጥፍትዋም ይቅርታን ለግሳት፤

አንተ ቁጡ እና በትንሽ ፣ በትልቁ የምትነዘንዛት ከሆነ አንዳንዴ አሰደስትሀለሁ ብላ ልታስከፍ ትችላለችና ውስጥዋ በምን ይቆጣ ይሆን እያለች እንድትጨናነቅ አታድርጋት በትንሽ ነገር ደስተኛ ሆነ ለመገኝት መክር።

በተወሰኑ ነገሮች ላይ የሃሳብ ልዩነት ሊፈጠር ይችላል ያኔ አንተም የራስህ ሃሳብ እዲሆን ትሻለህ እስዋም እንደዛው  በዚህ መካከል ንትርክ ፣  ጭቅጭቅ ብቅ ሳይል ነገሮችን ለማብረድ ሞክር።

አንዳንድ ወንዶች በጣም አግራሞትን ይፈጥራሉ ሴቶች ላይ እጅ የሚያነሱ ባለቤቱን የሚመታ ባሌ አላህን ሊፈራ ይገባል ሴት ልጅ   የሚመታ አካል የላትም

መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ በልዋል አንድ ወንድ ሚስቱን እንደ ግመል ከተማታ በኋላ እንዴት አቅፏት ይተኛል።

አሊይ (ረድየላሁ አንሁ )እንዲህ ብሉዋል
"ሴቶች የወንዶች ስጦታዎች ናቸው ይሁን እንጂ የሁሉም ነገር ወሳኛቸው አይደሉም የአላህ አደራ ናቸው ስለሆነም አትጉዷቸው ፣ ህይወትን አስቸጋሪ አታድርጉባቸው።

አንድ ባል ምስቱ ላይ የተወሰኖ መብቶች ቢኖሮትም አቅም በሌላት ነገር እና በሚጎዳት ነገር አታስገድዳት ሴት ልጅ የፍቅር የእዝነት ማዓከል  ናት እና ተንከባከባትጎ!!!

በትዳር ላይ ያላቸው ወድ የኢስላም ልጆች አላህ እስከጀነት ያዝልቃቹ
ትዳርን ለምትናፍቁ አላህ ሷሊህ የሆነውን
#ትዳር ይወፍቃቸው።

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
172 views03:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 06:22:43   ፍቅረኛ መያዝ ከሚያመጡብን መዘዞች

ክፍል አምስት

ቦይ- ገርል ፍሬንድ ወደ ዝሙት መግቢያ ሲሆን በተለይም ታዳጊ ሴቶችን ጨምሮ ወደ ዝሙት ለማምጣት የተቀመረ ሴራ ነው፡፡ ወንዱ የሴቶችን የትዳር ወዳድነትን ተፈጥሯዊ ባህሪያቸውን ስለሚያውቅ በቀላሉ ለታዳጊዋ ሴት «እኔ ለወደፊት ለትዳር ስለምፈልግሽ እንጠናና ወይም ገርል-ፍሬንዴ ሁኚ» ይላታል፡፡ በዚህ በኩል ይግባቡና ብዙም ሳይቆዩ ዚና ያደርጋሉ፡፡ ከዚህ በኋላ የልጅቷ ሕይወት ምስቅልቅሉ ይወጣል፡፡ ሴት ልጅ ደግሞ አንዴ ሕጓን ከኒካሕ ውጭ ካጣችው ለወደፊቱ ከባድ የሆነን መዘዞች እንደሚያስከፍላት ማወቅ አለባት።
 
     
Please ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
    ቢያንስ ለ10 ጓደኞቻችሁ ፎርዋርድ አድርጉ


Join us on telegram
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
218 views03:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 06:17:56
ወንድ ልጅ ምሉዕ የሆነችን ሴት ይመኛል ሴት ልጅም ምሉዕ የሆነን ወንድ ትመኛለች ፈጣሪ አንዱ አንዱን አንዲሞላ አድርጎ እንደፈጠራቸው ግን አያውቁም
           :::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam ❞  
994 viewsedited  03:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 06:16:53   ፍቅረኛ መያዝ ከሚያመጡብን መዘዞች

ክፍል አራት


ብዙውን ጊዜ በተቃራኒ ፆታዎች መካከል የሚኖረው ፍቅር በአማካይ ከሁለት ዓመታት በላይ አይዘልቅም፡፡ ስለዚህ ወንዱና ሴቱ በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የመለያየት ዕድላቸው ሰፊ ነው፤ ምክንያቱም በሰዎች መካከል ፍቅርን የሚያደረገው አላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)እንጂ ፍቅር በራሱ ጊዜ አይመጣምና፡፡ ማንኛውም ምድራዊ ኃይልም ሆነ በዓለም ላይ ያለውን ሀብት ብናፈስ በሁለት ሰዎች መካከል ፍቅርን ማኖርን አንችልም፡፡ እውነተኛ ፍቅር ሙሉ በሙሉ አምላካዊ ጸጋ ነው፡፡ አላህ ደግሞ ትክክለኛ መዋደድን የሚዲያደርገው በትዳር ውስጥ ብቻ ነው።

   
 Please ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
    ቢያንስ ለ10 ጓደኞቻችሁ ፎርዋርድ አድርጉ

ከዚህ ለመውጣት ከአለሰህ በታች እገዛ ለሚያስፈክጋችሁ ወይም በዚህ ጉዳይ ጥያቄ ካላችሁ መመካከር እ  ችላለን ሚስጥራችሁ የተጠበቀ ነው።
@jezakellah 

Join us on telegram
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
984 views03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 21:13:11
።እህቴ  ሆይ ።

ሰላት የማይሰግድን
ሰው ለ ትዳርሽ
አጋር እንዲሆን አትፍቀጂ።

ጌታውን ችላ እንዳለ ሁሉ
አንቺንም  ይተውሻል እና።
 

:::::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
950 viewsedited  18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 21:07:09   ፍቅረኛ መያዝ ከሚያመጡብን መዘዞች

ክፍል ሦስት


የቦይ-ገርል-ፍሬንድ ግንኙነት ሲስፋፋ የሰዎች ውጤታማነት ይቀንሳል፡፡ ለምሳሌ ተማሪዎችን ብንወስድ ይህንኑ ጎጂ ባህል እንደ ሁለተኛ ትምህርታቸው ስለሚወስዱት በትምህርታቸው ላይ የሚጠበቀውን ውጤት ማስመዝገብ አይችሉም፡፡ በርካታ ተማሪዎች ፍቅረኛ ከመያዛቸው በፊት ተቃራኒ ፆታን ለመሳብ ሲሉ በራሳቸው ላይ ብዙ ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ፡፡ ለስታይላቸው፣ ለአለባበሳቸው፣ ለአረማመዳቸው፣ ለአነጋገቸውና ይጨናነቃሉ፡፡ ከዚህም የተነሳ ትምህርት ይበደላል፡፡ ቦይፍሬንድ ወይም ገርልፍሬንድ ከያዙ በኋላም ቢሆን የተመኙትን ነገር ለማግኘት ስለሚጎመዡ ለትምህርታቸው ብዙም ትኩረት አይሰጡም፡፡ አንዴ ወደ ወሲባዊ ግንኑኘት ከገቡ ደግሞ ደስታ ባይሰጣቸውም ደጋግመው ማድረግን ይፈልጋሉ፡፡ በዚሁ ዓይነት ሁኔታም ሱሰኛ ይሆናሉ፡፡ ከዚያም ለወሲብ ማሟሟቂያ በሚል ጫትና ሺሻ ይጀመራል፡፡ ተማሪው ከትምህርቱ ይልቅ በሱስ ተጠምዶ ይውላል፡፡ ይህ ሁሉ ነገርም በተግባር እየታየ ነው፡   
  
 search
@latekrebu_zina
    ፕሮፋይል በማድረግ ግዴታችንን እንወጣ

ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር

Comment
@jezakellah

Please ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
    ቢያንስ ለ10 ጓደኞቻችሁ ፎርዋርድ አድርጉ

ከዚህ ለመውጣት ከአለሰህ በታች እገዛ ለሚያስፈክጋችሁ ወይም በዚህ ጉዳይ ጥያቄ ካላችሁ መመካከር እ  ችላለን ሚስጥራችሁ የተጠበቀ ነው።
@jezakellah 

Join us on telegram
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
993 views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ