Get Mystery Box with random crypto!

የኛ-MANCHESTER-UTD 🔴

የቴሌግራም ቻናል አርማ the_red_forever_mv — የኛ-MANCHESTER-UTD 🔴
የቴሌግራም ቻናል አርማ the_red_forever_mv — የኛ-MANCHESTER-UTD 🔴
የሰርጥ አድራሻ: @the_red_forever_mv
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 22.71K
የሰርጥ መግለጫ

📍WELCOME |👇እንኳን ደና መጡ📍
➲የኛ-Manchester-UTD 🔴💃
➥ የ ዩትዩብ ቻናላችን
👇SUBSCRIBER ያርጉ
https://www.youtube.com/@the_red_forever_mv
ቲክቶክ -> tiktok.com/@the_red_forever_mv

🔴Group➥ @man_united_forever
👨‍💻➥ @Sir_AbdGGMU

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-07-03 21:11:56
በጣም ነው ግን የሚገርመው፣ ቆይ ይህ አይነቱ አካሄድ ከዩናይትድ ላይ የሚነሳው መቼ ነው፣ ሁሉም ክለቦች ዩናይትድን አግልለው የተመካከሩ እስኪመስል ድረስ ዩናይትድ የጠየቀው ተጨዋች ሁሉ በዚህ ልክ እንዴት ጣሪያ ይነካል።
ይህ ተጨዋች የአታላንታው አጥቂ ዴኒሻዊዉ ሆጅሉንድ አንድ አመትኳን በቅጡ በወጥ አቋም አልተጫወተም፣ አወ ልጁ የነገ ትልቅ ተስፋ ያለው ተጨዋች ነው፣ ነገር ግን በአመት ውስጥ 20 ጎልኳን አግብቶ አያውቅም፣ ዩናይትድ ግን ልጁን አጥብቆ ፈለገው፣ እስከ 35 ሚሊዮን ዩሮ አውጥቶ ማስፈረም ቢፈልግም፣ አታላንታ ግን ለተጨዋቹ 60/70 ሚሊዮን ዩሮ ፈልጓል።


COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv
2.8K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 20:57:43 በአንድ ወቅት ሪዮ ፈርዲናንድ፣ ከዩናይትድ ፖድካስት ጋር በነበረው ቆይታ ይህንን ተናገረ፣ እኔ ማንችስተር ዩናይትድን እወደዋለሁ፣ ማንችስተር ለኔ ምንግዜም ታላቅ ነው፣ ነገር ግን ከዩናይትድ የተሰናበትኩበት መንገድ ለእኔ አይገባም ነበር ሲል መለሰ፣ ሪዮ ቀጠለና ኮንትራት ይሰጠኛል እያልኩ ስጠብቅ ነበር፣ ነገር ግን ልቀቅ የተባልኩትኳ በደብዳቤ ወይም በ ኢሜይል አልነበረም፣ ውድዋርድ ሲያልፍ ነው የነገረኝ ሲል መናገሩ ይታወሳል።

ፓትሪስ ኤቭራም እንዲሁ፣ የሪዮን ሃሳብ ተጋርቶ፣ የዩናይትድ አመራሮች ክብረቢስ ስለመሆናቸው መስክረሯል።

ዝላታን ኢብራሂሞቪች፣ ውሃ ጠምቶህ ጁስ ስትጠጣ 1 ዶላር ከደሞዝ የሚቆርጡ መሃይሞች ናቸው ሲል የተናገረ ሲሆን፣ ሁሉም በሃሳባቸው ውስጥ ዩናይትድ ታላቅነቱ እንጂ መሪወቹ ርካሽ ስለመሆናቸው በክለቡ የሚገኘው ባይሊ ሳይቀር ተናግሯል።

ዩናይትድ ያኔ የመከራ ጽዋን እየተጎናጸፈ፣ በነ ስዋንሲ ሳይቀር ከ 52 አመታት በኋላ ሲሸነፍ፣ እነ በርንሌይ ኦልድትራፎርድ ላይ ታሪካቸውን ሲያሻሽሉ፣ ዩናይትድ ከብዙ ውርደት የታደገ፣ 12 አመታትን በማይዝሉ ክንዶቹ ለታላቁ ክለብ የተዋደቀ፣ አሞራ ነው ሰው እስኪባል ድረስ የሰማይ ጭልፊት ሆኖ፣ አስራ አምስት ሙከራወችን በጨዋታ አድኖ እነ ቪንገርን ያስደመመ፣ የተጋጣሚ ተጨዋቾችን እራስ አስጨብጦ በቁጭት ሜዳ ያስደበደበ፣ ተቃራኒ ደጋፊዎች ቆመው ያጨበጨቡለት፣ ጨዋታን ብቻውን መርታት የቻለ፣ አራት ግዜ የአመቱ ኮከብ በረኝነት ክብርን በዩናይትድ ያሸነፈ፣ የብዙ ክሊንሺቶች ባለክብር ራሱን በዩናይትድ ታሪክ ማህደር በወርቅ ብዕር ያጻፈ የጆግኖች ጀግና።

ዴቭ ዩናይትድ ይልቀቅና ክለቡ በዘመናዊ በረኞች ይጀምር ከሚሉት ወገን ነኝ፣ ነገር ግን 12 አመታት ለክለቡ ክብር የተፋለመን፣ ክብር በማሳጣት ሳይሆን በክብር በመሸኘት ቢሆን ነው የሚያምረው።

ዴቭን ሰአት ቆጥረው ኮንትራቱን መቅደድ፣ ሌሎችንም ክብር መንሳት ሲሆን፣ ከክብርም በላይ ወጣቶችን ተስፋ ማሳጣት ነው።

እነሱ አቅልለው ሊሸኙት ቢሹኳ፣ በእኛ ልብ በክብር ይሸኛልና፣ የዩናይትድ ህያው ምልክት ሆኖ ያልፋል።

በዩናይትድ ከኦናና ጋር ቢፎካከር ደስታየ የትየለሌ ነው፣ ግን የሚሆን አይመስልም፣ እንደማይሆን ግልጽ ነው፣ ክለቡ ከኦናና ጋር ድርድር ላይ ነው፣ ነገር ግን የማንደራደርበትን ኮከብ ክብር ነስተው ሌላ ማምጣቱ ሴንስ አይሰጥም።

ዴቪድ ዴህያ ኩይታና፣ ይህ ሆኖ በዚህ መንገድ ብትለቅኳ፣ ለታላቁ ክለቤ ለክብሩ ተዋድቀሃልና በክብር እሸኝሃለሁ።

COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv
6.1K views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 20:57:12
5.5K views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 16:04:43 ሙሉ ስም፡ ሜሰን ቶኒ ማውንት

የትውልድ ዘመን፡ ሰኔ 10, 1999 እ.ኤ.አ

እድሜ፡ 24 አመት

የትውልድ ቦታ፡ ፖርትስማውዝ፣እንግሊዝ

ዜግነት፡ እንግሊዛዊ

ቁመት፡ 1.81 ሜ

ክብደት፡ 74 ኪ.ግ

የተጨዋችነት ሚና፡ የአጥቂ አማካኝ፣ የመሀል አማካኝ

የተጫወተባቸው ክለቦች፡- ቼልሲ (2005-2017)
ቪቴስ (2017-2018) በውሰት
ደርቢ ካውንቲ (2018-2019) በውሰት
ቼልሲ (2019-2023)

በብሄራዊ ቡድን፡-በእንግሊዝ ከ 16፣17፣18፣19፣21 አመት በታች ቡድኖች ከ 2014-2019
በዋናው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ከ 2019-እስከአሁን

ቁጥራዊ መረጃዎች በአጠቃላይ በክለብ ቆይታ (የወጣት ቡድን ቆይታን ጨምሮ)
ጨዋታዎች፡ 324
ጎሎች፡ 65
አሲስቶች፡ 62

ቁጥራዊ መረጃዎች በብሄራዊ ቡድን (ወጣት ቡድኖችን ጨምሮ)
ጨዋታዎች፡ 76
ጎሎች፡ 18

አጠቃላይ በክለብና በብሄራዊ ቡድን፡ 400 ጨዋታዎች፣ 83 ጎሎች፣ 62 አሲስቶች

የቡድን ስኬቶች፡
በቼልሲ ወጣት ቡድን
ከ 18 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን፣ ከቼልሲ 18 አመት በታች ቡድን ጋር (2016/17)
2 ጊዜ የወጣቶች FA Cup አሸናፊ (2015/16 - 2016/17)
የ UEFA ወጣቶች ቻምፒዮንስሊግ ቻምፒዮን (2015/16)

በቼልሲ ዋናው ቡድን፡
የ አውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ (2020/21)
የ አውሮፓ ሱፐር ካፕ አሸናፊ (2021)
የአለም ክለቦች ዋንጫ አሸናፊ (2021)

በእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድኖች፡
የአውሮፓ ከ 19 አመት በታች ዋንጫ አሸናፊ (2017)
የአውሮፓ ዋንጫ የፍፃሜ ተፋላሚ (የብር ሜዳሊያ)(2020)

የግል ስኬቶች፡
የቼልሲ አካዳሚ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች (2016/17)
የአውሮፓ ከ 19 አመት ዋንጫ የውድድሩ ምርጥ 11 እና የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች (2017)
የቪቴስ እንዲሁም የሆላንድ ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች የቻምፒዮንስ ሊግ ምርጥ 11 (2020/21)
ከአካዳሚ የተገኘ የፕሪሚየር ሊግ ምርጥ ተጨዋች (2020/21)

Welcome To United

COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv
6.1K viewsedited  13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 16:03:51
5.0K views13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 21:19:44 የዛሬ ዜናወች በብዛት ግልፅና ጥሩ ዜናወች ይዘው አይቻለሁ እና ይህ ሊሆንም እንደሚችል አምናለሁ

Fabrizio ስለሁለቱም ግልፅ ዜናወችነው የለጠፈ

ከአንድሬ ኦናናጋር በደምብ የሄዱበት ይመስላል ትናንት የኢንተር ባለስልጣን በእንግሊዝ ተገኝቶ አውርተውበታል ኢንተሮች የተጨዋቹ ዝውውር ሚሆን ከሆነ በፍጥነት እንዲሆን ይፈልጋሉ ያ ካልሆነግን ዝውውሩ ሙሉበሙሉ እንዲቋረጥ ይፈልጋሉ

እስከ 60ሚዮ ለዝውውሩ የሚፈልጉ ሲሆን ዩናይትድ እስከ 55ሚዮ የማቅረብ እቅድ አለው እና በነዚህ ሁለት ቀናት ነገሮችን የበለጠ ማፍጠን ይፈልጋሉ ኦናና በግል ተስማምቷል እና ኢንተሮች ጋር ነገሮች መጠናቀቁ ከሆነ በዩናይትድ ፕሪሲዝን ኦናና ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል

ሌላው የማውንት ጉዳይነው የዚህን ተጨዋች ዝውውር የመጨረሻ እልባት ለመስጠት የቼልሲና የዩናይትድ ሰወች ፊትለፊት ተገናኝተው ያወራሉ ውሳኔው የሚሰጠው ከዚህ ስብሰባ በኋላ ይሆናል

የግል ሀሳብ

የሁለቱ ተጨዋቾች ወደ ዩናይትድ መምጣት ሚቀር አይመስለኝም ቼልሲ አይኑ እያየ በነፃ አያጣውም ስለዚህ የግድ የቻሉትን ያህል አውርተው ጥሩ ቢዝነስ መስራት ይፈልጋሉ ...

የኦናናም ሚቀር አይመስለኝም አንደኛ የዳሂያ ውል ሊጠናቀቅ ሁለት ቀን ብቻነው የቀረው ዳሂያን የዩናይትድ ባለስልጣናት ክደውታል የመጀመሪያው የደሞዝ ቅነሳ ስምምነት ሁለቱንም አካሎች አግባብቶ ነበር ከዚህ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ደሞዙን እንዲቀንስ ከጠየቁት በኋላግን ዴቪድ ምንም አይነት ምላሽ አልሰጡበትም ከደቂቃዎች በፊት ቲወተርላይም ያጋራት ምስል ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ እንደምትገልፅ ለመናገር እንደፈለገነው ብዙዎች የተረዱትና ዴቪድ ወደ መውጫውም የተጠጋ ይመስላል

አስገራሚው ሌላ የዩናይትድ መረጃ ዩናይትድ በግሌዘሮችስር ያለው የዝውውር በጀት 120ሚፓ ብቻ ሲሆን የክለቡ እዳም 725ሚፓ አካባቢ እንደደረሰ ነው የዛሬው የፋይናንስ ማረጋገጫ ያስረዳውና ክለቡ በነዚህ ሰወች ምክንያት ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብቷል ።

COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv
6.2K views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 21:19:26
5.8K views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 23:18:19 ማንችስተር ዩናይትድ 640 ሚሊዮን ፓውንድ አመታዊ ገቢ አስመዝግቧል። ይህም በክለቡ ታሪክ ከፍተኛው ነው። የግሌዘር ቤተሰቦች አሁንም ጨረታውን እያጤኑበት ይገኛል።

ግሌዘሮች ከካታርና ከ ራትክሊፍ ጋር መነጋገራቸውን የቀጠሉ ሲሆን፣ የሼክ ጃሲም 5ተኛ ጨረታ በግሌዘሮች አሸናፊነቱን ይዟል።

100% የመግዛት አማራጭ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት ሼክ ጃሲም በግሌዘሮች ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው ሲሆን፣ የጨረታ ሂደቱ ግን አሁንም በንግግር ቀጥሏል።

ስካይ ስፖርት ከዩናይትድ የውስጥ ምንጮቼ አገኘሁት ባለው መረጃ፣ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ምንም አይነት የበጀት እጥረትም ሆነ ክልከላ እንደሌለና ቴን ሃግም ይህንኑ እንዳረጋገጡ ዘግቧል።

የዩናይትድ አመታዊ የትኬት ሽያጭ ሪከርድ ከ 2016/17 የውድድር ዘመን በኋላ ከፍተኛውን ሪከርድ ያስመዘገበ ሲሆን በአጠቃላይም 2 ሚሊዮን 400 ሺ ትኬቶች ተሸሰጠዋል።

የዩናይትድ አባሎችም 300 ሺ መድረሳቸው ተጠቁሟል።

የዩናይትድ አጠቃላይ ገቢም 11 በመቶ ካለፈው አመት የጨመረ ሲሆን፣ ይህም በአገር ውስጥ ውድድሮች ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረጉ እንደሆነ ተነግሯል።

ይህንን ፋይናንስ አጠቃላይ የከወኑትና ወጪ ገቢያቸውን የለዩት ግሌዘሮች ቀጣይ ውሳኔያቸው ባለቤቱን ይፋ ማድረግ እንደሆነም ተመልክቷል።

1958 የዩናይትድ ደጋፊዎች በትዊተር ተቃውሞውን ከጀመሩና የዛሬውንም ይፋ ካደረጉ በኋላ የተለያዩ ሱቆቹን ዘግቶ ማልያውን ያስተዋወቀው ዩናይትድ፣ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ብዙ መልሶችን እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

ደጋፊወቹ ተቃውሞውንም ወደ ኤሌክትሮኒክ እንደቀየሩት የተሰማ ሲሆን ይህም 1.4 ቢሊዮን ደጋፊ ላለው ክለብ ከፍተኛ ውጥረት እንደሆነና ሽያጩን እንደሚያራዝመው ተሰምቷል።

ዛሬ ስለ ዩናይትድ የወጣው መረጃ በርካታ ቢሆንም በአጭሩ አጠቃልየው ግን ይህንን ይመስላል።

COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv
6.3K views20:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 23:17:29
5.6K views20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 15:28:04
የማንችስተር ዩናይትድ ሰዎች በቼልሲ ሰዎች ስራ ደስተኛ አይደሉም

በተለይም የቼልሲ ሰዎች በቀጥታ ዩናይትድ ለማውንት ስለ አቀረበው ገንዘብ እና በቶሎ ውድቅ ስለማድረጋቸው እና ስለ ድርድሩ ሁኔታ ለሚዲያዎች ቀጥተኛ መረጃን መስጠታቸው አላስደሰታቸውም።

[MEN]

COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv
7.5K views12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ