Get Mystery Box with random crypto!

ማንችስተር ዩናይትድ 640 ሚሊዮን ፓውንድ አመታዊ ገቢ አስመዝግቧል። ይህም በክለቡ ታሪክ ከፍተኛው | የኛ-MANCHESTER-UTD 🔴

ማንችስተር ዩናይትድ 640 ሚሊዮን ፓውንድ አመታዊ ገቢ አስመዝግቧል። ይህም በክለቡ ታሪክ ከፍተኛው ነው። የግሌዘር ቤተሰቦች አሁንም ጨረታውን እያጤኑበት ይገኛል።

ግሌዘሮች ከካታርና ከ ራትክሊፍ ጋር መነጋገራቸውን የቀጠሉ ሲሆን፣ የሼክ ጃሲም 5ተኛ ጨረታ በግሌዘሮች አሸናፊነቱን ይዟል።

100% የመግዛት አማራጭ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት ሼክ ጃሲም በግሌዘሮች ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው ሲሆን፣ የጨረታ ሂደቱ ግን አሁንም በንግግር ቀጥሏል።

ስካይ ስፖርት ከዩናይትድ የውስጥ ምንጮቼ አገኘሁት ባለው መረጃ፣ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ምንም አይነት የበጀት እጥረትም ሆነ ክልከላ እንደሌለና ቴን ሃግም ይህንኑ እንዳረጋገጡ ዘግቧል።

የዩናይትድ አመታዊ የትኬት ሽያጭ ሪከርድ ከ 2016/17 የውድድር ዘመን በኋላ ከፍተኛውን ሪከርድ ያስመዘገበ ሲሆን በአጠቃላይም 2 ሚሊዮን 400 ሺ ትኬቶች ተሸሰጠዋል።

የዩናይትድ አባሎችም 300 ሺ መድረሳቸው ተጠቁሟል።

የዩናይትድ አጠቃላይ ገቢም 11 በመቶ ካለፈው አመት የጨመረ ሲሆን፣ ይህም በአገር ውስጥ ውድድሮች ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረጉ እንደሆነ ተነግሯል።

ይህንን ፋይናንስ አጠቃላይ የከወኑትና ወጪ ገቢያቸውን የለዩት ግሌዘሮች ቀጣይ ውሳኔያቸው ባለቤቱን ይፋ ማድረግ እንደሆነም ተመልክቷል።

1958 የዩናይትድ ደጋፊዎች በትዊተር ተቃውሞውን ከጀመሩና የዛሬውንም ይፋ ካደረጉ በኋላ የተለያዩ ሱቆቹን ዘግቶ ማልያውን ያስተዋወቀው ዩናይትድ፣ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ብዙ መልሶችን እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

ደጋፊወቹ ተቃውሞውንም ወደ ኤሌክትሮኒክ እንደቀየሩት የተሰማ ሲሆን ይህም 1.4 ቢሊዮን ደጋፊ ላለው ክለብ ከፍተኛ ውጥረት እንደሆነና ሽያጩን እንደሚያራዝመው ተሰምቷል።

ዛሬ ስለ ዩናይትድ የወጣው መረጃ በርካታ ቢሆንም በአጭሩ አጠቃልየው ግን ይህንን ይመስላል።

COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv