Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ ዜናወች በብዛት ግልፅና ጥሩ ዜናወች ይዘው አይቻለሁ እና ይህ ሊሆንም እንደሚችል አምናለሁ | የኛ-MANCHESTER-UTD 🔴

የዛሬ ዜናወች በብዛት ግልፅና ጥሩ ዜናወች ይዘው አይቻለሁ እና ይህ ሊሆንም እንደሚችል አምናለሁ

Fabrizio ስለሁለቱም ግልፅ ዜናወችነው የለጠፈ

ከአንድሬ ኦናናጋር በደምብ የሄዱበት ይመስላል ትናንት የኢንተር ባለስልጣን በእንግሊዝ ተገኝቶ አውርተውበታል ኢንተሮች የተጨዋቹ ዝውውር ሚሆን ከሆነ በፍጥነት እንዲሆን ይፈልጋሉ ያ ካልሆነግን ዝውውሩ ሙሉበሙሉ እንዲቋረጥ ይፈልጋሉ

እስከ 60ሚዮ ለዝውውሩ የሚፈልጉ ሲሆን ዩናይትድ እስከ 55ሚዮ የማቅረብ እቅድ አለው እና በነዚህ ሁለት ቀናት ነገሮችን የበለጠ ማፍጠን ይፈልጋሉ ኦናና በግል ተስማምቷል እና ኢንተሮች ጋር ነገሮች መጠናቀቁ ከሆነ በዩናይትድ ፕሪሲዝን ኦናና ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል

ሌላው የማውንት ጉዳይነው የዚህን ተጨዋች ዝውውር የመጨረሻ እልባት ለመስጠት የቼልሲና የዩናይትድ ሰወች ፊትለፊት ተገናኝተው ያወራሉ ውሳኔው የሚሰጠው ከዚህ ስብሰባ በኋላ ይሆናል

የግል ሀሳብ

የሁለቱ ተጨዋቾች ወደ ዩናይትድ መምጣት ሚቀር አይመስለኝም ቼልሲ አይኑ እያየ በነፃ አያጣውም ስለዚህ የግድ የቻሉትን ያህል አውርተው ጥሩ ቢዝነስ መስራት ይፈልጋሉ ...

የኦናናም ሚቀር አይመስለኝም አንደኛ የዳሂያ ውል ሊጠናቀቅ ሁለት ቀን ብቻነው የቀረው ዳሂያን የዩናይትድ ባለስልጣናት ክደውታል የመጀመሪያው የደሞዝ ቅነሳ ስምምነት ሁለቱንም አካሎች አግባብቶ ነበር ከዚህ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ደሞዙን እንዲቀንስ ከጠየቁት በኋላግን ዴቪድ ምንም አይነት ምላሽ አልሰጡበትም ከደቂቃዎች በፊት ቲወተርላይም ያጋራት ምስል ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ እንደምትገልፅ ለመናገር እንደፈለገነው ብዙዎች የተረዱትና ዴቪድ ወደ መውጫውም የተጠጋ ይመስላል

አስገራሚው ሌላ የዩናይትድ መረጃ ዩናይትድ በግሌዘሮችስር ያለው የዝውውር በጀት 120ሚፓ ብቻ ሲሆን የክለቡ እዳም 725ሚፓ አካባቢ እንደደረሰ ነው የዛሬው የፋይናንስ ማረጋገጫ ያስረዳውና ክለቡ በነዚህ ሰወች ምክንያት ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብቷል ።

COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv