Get Mystery Box with random crypto!

በአንድ ወቅት ሪዮ ፈርዲናንድ፣ ከዩናይትድ ፖድካስት ጋር በነበረው ቆይታ ይህንን ተናገረ፣ እኔ ማን | የኛ-MANCHESTER-UTD 🔴

በአንድ ወቅት ሪዮ ፈርዲናንድ፣ ከዩናይትድ ፖድካስት ጋር በነበረው ቆይታ ይህንን ተናገረ፣ እኔ ማንችስተር ዩናይትድን እወደዋለሁ፣ ማንችስተር ለኔ ምንግዜም ታላቅ ነው፣ ነገር ግን ከዩናይትድ የተሰናበትኩበት መንገድ ለእኔ አይገባም ነበር ሲል መለሰ፣ ሪዮ ቀጠለና ኮንትራት ይሰጠኛል እያልኩ ስጠብቅ ነበር፣ ነገር ግን ልቀቅ የተባልኩትኳ በደብዳቤ ወይም በ ኢሜይል አልነበረም፣ ውድዋርድ ሲያልፍ ነው የነገረኝ ሲል መናገሩ ይታወሳል።

ፓትሪስ ኤቭራም እንዲሁ፣ የሪዮን ሃሳብ ተጋርቶ፣ የዩናይትድ አመራሮች ክብረቢስ ስለመሆናቸው መስክረሯል።

ዝላታን ኢብራሂሞቪች፣ ውሃ ጠምቶህ ጁስ ስትጠጣ 1 ዶላር ከደሞዝ የሚቆርጡ መሃይሞች ናቸው ሲል የተናገረ ሲሆን፣ ሁሉም በሃሳባቸው ውስጥ ዩናይትድ ታላቅነቱ እንጂ መሪወቹ ርካሽ ስለመሆናቸው በክለቡ የሚገኘው ባይሊ ሳይቀር ተናግሯል።

ዩናይትድ ያኔ የመከራ ጽዋን እየተጎናጸፈ፣ በነ ስዋንሲ ሳይቀር ከ 52 አመታት በኋላ ሲሸነፍ፣ እነ በርንሌይ ኦልድትራፎርድ ላይ ታሪካቸውን ሲያሻሽሉ፣ ዩናይትድ ከብዙ ውርደት የታደገ፣ 12 አመታትን በማይዝሉ ክንዶቹ ለታላቁ ክለብ የተዋደቀ፣ አሞራ ነው ሰው እስኪባል ድረስ የሰማይ ጭልፊት ሆኖ፣ አስራ አምስት ሙከራወችን በጨዋታ አድኖ እነ ቪንገርን ያስደመመ፣ የተጋጣሚ ተጨዋቾችን እራስ አስጨብጦ በቁጭት ሜዳ ያስደበደበ፣ ተቃራኒ ደጋፊዎች ቆመው ያጨበጨቡለት፣ ጨዋታን ብቻውን መርታት የቻለ፣ አራት ግዜ የአመቱ ኮከብ በረኝነት ክብርን በዩናይትድ ያሸነፈ፣ የብዙ ክሊንሺቶች ባለክብር ራሱን በዩናይትድ ታሪክ ማህደር በወርቅ ብዕር ያጻፈ የጆግኖች ጀግና።

ዴቭ ዩናይትድ ይልቀቅና ክለቡ በዘመናዊ በረኞች ይጀምር ከሚሉት ወገን ነኝ፣ ነገር ግን 12 አመታት ለክለቡ ክብር የተፋለመን፣ ክብር በማሳጣት ሳይሆን በክብር በመሸኘት ቢሆን ነው የሚያምረው።

ዴቭን ሰአት ቆጥረው ኮንትራቱን መቅደድ፣ ሌሎችንም ክብር መንሳት ሲሆን፣ ከክብርም በላይ ወጣቶችን ተስፋ ማሳጣት ነው።

እነሱ አቅልለው ሊሸኙት ቢሹኳ፣ በእኛ ልብ በክብር ይሸኛልና፣ የዩናይትድ ህያው ምልክት ሆኖ ያልፋል።

በዩናይትድ ከኦናና ጋር ቢፎካከር ደስታየ የትየለሌ ነው፣ ግን የሚሆን አይመስልም፣ እንደማይሆን ግልጽ ነው፣ ክለቡ ከኦናና ጋር ድርድር ላይ ነው፣ ነገር ግን የማንደራደርበትን ኮከብ ክብር ነስተው ሌላ ማምጣቱ ሴንስ አይሰጥም።

ዴቪድ ዴህያ ኩይታና፣ ይህ ሆኖ በዚህ መንገድ ብትለቅኳ፣ ለታላቁ ክለቤ ለክብሩ ተዋድቀሃልና በክብር እሸኝሃለሁ።

COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv