Get Mystery Box with random crypto!

Stalin Gebreselassie

የቴሌግራም ቻናል አርማ stalingebreselasie — Stalin Gebreselassie S
የቴሌግራም ቻናል አርማ stalingebreselasie — Stalin Gebreselassie
የሰርጥ አድራሻ: @stalingebreselasie
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.29K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-03-21 10:57:59
A great loss to humanity and earth. Dr. Tewolde, May your soul rest in eternal peace.
875 views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 10:18:19 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ኃይሎች፤ በሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሼያለሁ ስትል አሜሪካ ይፋ አደረገች።

አሜሪካ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተሳተፉ ሁሉም ኃይሎች “የጦር ወንጀሎች ፈጽመዋል” የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሷን የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ተናገሩ። በምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች፤ የአማራ ኃይሎች “የዘር ማጽዳት” እና “በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል” መፈጸማቸውንም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጨምረው አስታውቀዋል።

ብሊንከን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን በተመለከተ ሀገራቸው የደረሰችበትን መደምደሚያ ያስታወቁት፤ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ሀገራት በ2022 የነበረውን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ የሰነደ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዓመታዊ ሪፖርት ዛሬ ሰኞ መጋቢት 11፤ 2015 ይፋ ሲደረግ ነው። ይህ የአሜሪካ ዓመታዊ የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ ሪፖርት፤ በስድስት ጎራ የተከፋፈሉ 198 አገሮች እና ግዛቶችን የተመለከተ ነው።

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪፖርቱ ይፋ በተደረገበት ወቅት በሰጡት ማብራሪያ በኢራን፣ አፍጋኒስታን፣ በርማ፣ ቻይና እና ኩባ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ቢጠቃቅሱም፤ ሰፊ ጊዜ የሰጡት ግን የኢትዮጵያን ጉዳይ ነበር። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ተፋላሚ ወገኖች ፈጽመውታል ያለው ድምዳሜ ላይ የደረሰው፤ “ሕጉን እና እውነታውን በጥንቃቄ ካጠና በኋላ” መሆኑን በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።

“የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ኃይሎች፤ በሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሼያለሁ” ሲሉ ብሊንከን በዚሁ መግለጫቸው ወቅት ተናግረዋል። “የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ኃይሎች፤ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር እና ሌሎች ጾታዊ ጥቃቶች እና ማሰቃየትን ጨምሮ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ፈጽመዋል” ሲሉም አክለዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በዛሬው መግለጫቸው፤ የአማራ ኃይሎች በምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች ፈጽመዋቸዋል ያሏቸውን ወንጀሎችንም በተጨማሪነት አንስተዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ የአማራ ኃይሎች በምዕራብ ትግራይ በሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ላይ “በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል፣ ማፈናቀል ወይም በግዳጅ ማዛወር እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጽመዋል።”

“የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት አውዳሚ ነበር። ወንዶች፣ ሴቶች እና ህጻናት ተገድለዋል። ሴቶች እና ልጃገረዶች ለአሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃቶች ተጋልጠዋል። በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል። ማህበረሰቦች በሙሉ በብሔራቸው ምክንያት ኢላማ ሆነዋል” ያሉት ብሊንከን፤ ድርጊቶቹ “ታቅዶ” እና “ሆን ተብሎ” የተፈጸሙ መሆናቸውንም ገልጸዋል። “አብዛኞቹ እነዚህ እርምጃዎች የዘፈቀደ ድርጊቶች ወይም የጦርነት ውጤቶች አይደሉም” ሲሉም አክለዋል።

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግስታት እንዲሁም የአማራ ሀይሎች “እነዚህን ግፎች የፈጸሙትን ተጠያቂ እንዲያደርጉ” ጥሪ አቅርበዋል። ለተፈጸሙት ግፎች እውቅና መስጠት፣ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እና እርቅ ማውረድ “ኢትዮጵያ ካልተገደበ አቅሟ እንዳትደርስ ለረዥም ጊዜ አግደው ያቆዩዋትን የብሔር እና የፖለቲካ ግጭት አዙሪት ለመስበር ቁልፍ ናቸው” ሲሉ ተደምጠዋል።

ኢትዮጵያ “ለተጎጂዎች እና ተጽዕኖ ለደረሰባቸው ማኅበረሰቦች የሚጠቅም ተአማኒ የሽግግር ፍትሕ ሒደት” ስትዘረጋ አሜሪካ አጋር እንደምትሆንም ብሊንከን ቃል ገብተዋል። አገሪቱ “ባለፉት ጊዜያት የተፈጸሙ በደሎችን ፊት ለፊት ስትጋፈጥ፣ በዜጎቿ ላይ ለተፈጸሙ ጉዳቶች ተጠያቂነትን ስታረጋግጥ እና ወደ ዘላቂ ሰላም ስትገሰግስ ከኢትዮጵያ ጋር እንቆማለን” ሲሉ ተናግረዋል።
939 views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 09:19:18
እርምጃ...ሲል ትዝ ብሎኝ ነው።
71 views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 14:54:00 የትግራይ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መግለጫ

የኢትጵያ መንግስት የዜጎች ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነቱ እንዲወጣ እና በአማራ ክልል አስተዳደር በምዕራብ፣ደቡብ እና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እና በደል ሊያስቆመው ይገባል ሲል የትግራይ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ዛሬ ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው የሰላም ሂደቱ ወደ ተሻለ አቅጣጫ ጉዞ በጀመረበት እና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የመመስረት እንቅስቃሴ እያፋጠንበት ባለንበት ጊዜ በደቡብ ትግራይ አከባቢዎች እየተካሄዱ ያሉትን ሰላማዊ ህዝቡ የማወክ እና ተከታታይ በደል የመፈጸም ተግባራት የሰላሙ ጉዞ የማደፍረስ ተግባራት በመሆናቸው የኢትዮጵያ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲያስቆማቸው የትግራይ ህዝብ ጥሪውን ያቀርባል ብሏል።

የዚህ ችግር መገለጫም ትናንት መጋቢት 10/2015 ዓ.ም ከተለያዩ የአማራ ክልል አከባቢዎች በተለይም ከጉባ-ላፍቶ፣ወልዲያ እና ራያ ቆቦ ወረዳዎች በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ አላማጣ በማጓጓዝ ተቀባይነት የሌለው ሰልፍ ተካሂዷል።በበርካታ ሰላማውያን ሰዎች ላይም አሳዛኝ በደል ሊፈጸም ችሏል ብሏል ቢሮው በመግለጫው።

በተመሳሳይ በሰሜን ምዕራብ እና ምዕራብ ትግራይም ከመጀመርያ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያልተቋረጠ የጆኖሳይድ ወንጀል እየተፈጸመ ይገኛል ያለው መግለጫው የኢትጵያ መንግስት የዜጎች ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነቱ እንዲወጣ እና በአማራ ክልል አስተዳደር በምዕራብ፣ደቡብ እና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እና በደል ሊያስቆመው ይገባል።ይህ ለማድረግም የአማራ ታጣቂዎች ከትግራይ መሬት ጠቅልለው እንዲወጡ በቆራጥነት ሊሰራ ይገባል ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

የአፍሪካ ህብረት እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በተመሳሳይ የአማራ ታጣቂዎች እና የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈጸሙት የመጡትን እና አሁንም እየፈጸሙት ያሉትን ወንጀል ማስቆም የሚያስችል ትርጉም ያለው እርምጃ እንዲወስዱ የትግራይ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ ላይ ጥሪውን አቅርቧል።

የትግራይ ህዝብ እና መንግስት ስርዓት ይከበር፣የህዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ውሳኔ መጣስ የለበትም የሚል ህዝባዊ እምነት እና አቋም በመያዘቸው ብቻ ባለፉት ዓመታት እላያቸው ላይ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ግፎች እና በደሎች እየደረሰባቸው መምጣጡን ያስታወሰው የቢሮው መግለጫ ይህን ለመመከት ከፍተኛ ትግል እያደረጉ በነበሩበት ወቅት በጥቅምት ወር መጨረሻ 2015 ዓ.ም ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል መግባታቸውን አንስቷል።

የትግራይ ህዝብ ጥያቄዎቹ በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ እያካሄደው ባለው ሰላማዊ ትግል ለሰላም ሲል ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈለ መሆኑንም ቢሮው በመግለጫው አክሏል።

በኢትዮጵያ መንግስት በኩልም ቢሆን ምንም እንኳን አሁንም የትግራይ ህዝብ ህገመንግስታዊ መብት እና ነጻነት በሚገባ ለመመለስ ከፍተኛ ስራ መስራት የሚጠበቅበት ቢሆንም በየጊዜው ተስፋ የሚሰጡ መሻሻሎች እያሳየ መምጣቱ ግን ቀጣዩ የሰላም ጉዞ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል መሆኑን ተገቢውን ምልክት እየሰጠ ነው ሲል የኮሚኒኬሽን ቢሮው በመግለጫው አትቷል።
746 views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 14:53:59 እዋናዊ መግለፂ መንግስቲ ትግራይ

ህዝብን መንግስትን ትግራይ "ስርዓት ይከበር፣ መሰል ርእሰ ውሳነ ህዝብታት ክጥሓስ የብሉን" ዝብል ህዝባዊ እምነትን መትከልን ብምሓዞም ጥራሕ ኣብ ዝሓለፉ ዓመታት ኣብ ልዕሊኦም ማእለያ ዘይብሎም በደላትን ግፍዕታትን እናበፅሖም መፂኡ እዩ። ኣብ ልዕሊኦም ዝበፅሐ ብዓይነቱ ፍሉይ ዝኾነ ሓሳረ መከራ ንምምካት እውን ብዝገርም ፅንዓትን መስተንክራዊ ጅግንነትን እናተረባረቡ ድሕሪ ምፅናሕ ኣብ መወዳእታ ወርሒ ጥቅምቲ 2015 ዓ.ም ናብ መስርሕ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ቃልሲ ኣትዮም ይርከቡ።

ህዝቢ ትግራይ ሕቶታቱ ብሰላማዊ መንገዲ ንምምላስ ኣብ ዘካይዶ ዘሎ ሰላማዊ ቃልሲ ምእንተ ሰላም ኢሉ ኩለ መዳያዊ መስዋእቲ እናኸፈለ እዩ። ብወገን መንግስቲ ኢትዮጵያ እውን እንተኾነ ዋላ እኳ ሕዚ እውን ሕገ መንግስታዊ መሰልን ነፃነትን ህዝቢ ትግራይ ብዝግባእ ንምምላስ ብዙሕ ክሰርሕ ዝግብኦ እንተኾነ በብእዋኑ ተስፋ ዝህቡ ምምሕያሻት እናርኣየ ምምፅኡ ግን ቀፃሊ ጉዕዞ ሰላም ናብ ዝሓሸ ብርኪ ክሰግር ከም ዝኽእልን ከምዝግባእን ምልክት እናሃበ እዩ።

ይኹን እምበር እዚ ከይዲ ዘተ ሰላም ናብ ዝሓሸ ኣንፈት ጉዕዞ ኣብ ዝጀመረሉን ግዝያዊ ምምሕዳር ትግራይ ናይ ምምስራት ምንቅስቓስ ኣብ እነሳልጠሉን እዋን ኣብ ከባብታት ደቡብ ትግራይ ዝካየዱ ዘለዉ ሰላማዊ ህዝቢ ናይ ምህዋኽን ዘይዛሪ በደል ናይ ምፍፃም ተግባራትን ጉዕዞ ሰላም ናይ ምዝራግ ተግባር ዝኾነ፣ መንግስቲ ኢትዮጵያ ፍሉይ ቆላሕታ ሂቡ ጠጠው ንከብሎ ህዝቢ ትግራይ ፃውዒቱ የቕርብ። ናይዚ ሕመቕ መግለፂ ድማ ትማሊ 10 መጋቢት 2015 ዓ.ም ካብ ዝተፈላለዩ ከባቢታት ክልል ኣምሓራ ብፍላይ ካብ ወረዳታት ጉባ- ላፍቶ፣ ወልድያን ራያ ቆቦን ብዙሕ ህዝቢ ብምጉዕዓዝ ኣብ ከተማ ኣላማጣ ተቐባልነት ዘይብሉ ሰልፊ ተኻይዱ ኣሎ። ኣብ ልዕሊ ብዙሓት ሰላማውያን ሰባት እውን ዘሕዝን በደል ክፍፀም ክኢሉ እዩ። ኣብ ከባቢታት ምዕራብን ሰሜን ምዕራብን ትግራይ እውን ካብ ፈለማ ጀሚሩ ክሳብ ሕዚ ዘየቋረፀ ገበን ጀኖሳይድ እናተፈፀመ መፂኡን ኣሎን።

መንግስቲ ኢትዮጵያ ድሕንነት ዜጋታት ናይ ምሕላው ሓላፍነቱ ክዋፃእን ብምምሕዳር ክልል ኣምሓራ ኣብ ልዕሊ ህዝቢ ዞባታት ምዕራብ፣ ደቡብን ሰሜን ምዕራብን ትግራይ ዝበፅሕ ዘሎ ግፍዕን በደል ጠጠው ከብልን ይግባእ። እዚ ንምግባር ድማ ዕጡቓት ኣምሓራ ካብ መሬት ትግራይ ጠቕሊሎም ንክወፅኡ ብቆራፅነት ክሰርሕ ይግባእ።

ሕብረት ኣፍሪካን ማሕበረሰብ ዓለምን እውን ብተመሳሳሊ ዕጡቓት ኣምሓራን ሰራዊት ኤርትራን ኣብ ልዕሊ ህዝቢ ትግራይ እናፈፀምዎ ዝመፀን ዘሎን ገበን ጠጠው ከብሉ ዘኽእል ትርጉም ዘለዎ ስጉምቲ ንክወስዱ ፃውዒትና ነቕርብ።

ቢሮ ርክብ ህዝብን መንግስትን ትግራይ
11 መጋቢት 2015 ዓ.ም
መቐለ
720 views11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 10:58:40 ድምፃዊ ሙሉጌታ ማሉዳ:

ናይ ኣላማጣ ኹነታት ምስ ሰማዕኹ ዝተሰመዐኒ ሕማቕ ስሚዒት ብቓላት ኣይግለፅን ። ኣነ ኣብዚ ናይ መኸተ ዝበዘሐ
ግዜ ኣብ ደቡባዊ ትግራይ ራያ እየ ኣሕሊፈዮ ። ህዝቢ ራያ ዝተፈለየ ህዝቢ እዩ ነዓይ ለባም..ሩሁሩህ..ለጋስ ...ሐዚ ግን መሬት ፀቢባቶ ቀትሪ ፀልማት ለይቲ ሲኦል ኮይናቶም ኣላ ብሰንኪ ዙ ተስፋሕፋሓይ ሓይሊ ። ምዕራብን ሰሜን ምዕራብን ትግራይ ...ጉሎሙኾዳ ...ኢሮብ...ብጠቕላላ ኣብፀላኢ ዘሎ ህዝብን ኣብታ ጫፍ ሕማቕ ትባሃል ኩነታትዩ ዘሎ ...ወዮ ፌደራል መንግስቲ እንድሕር ዝምልከቶ ከወፀኦም ግበሩ ተዘይኮይኑ ኢድናን እግርናን ሒዝኩም ኣይተቐጥቁጡና ።
824 views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 20:55:51 በኣላማጣ ትግራዋይ በሙሉ ሰልፍ እንዲወጣ እያስገደዱ እንደነበር ሰምተናል። አይሆንም ሰልፍ አንወጣም ያሉ ተጋሩ ወጣቶችም ተገድለዋል። ትግራዋይን ሰልፍ አስወጥተህ "እኔ ኣማራ ነኝ" የሚል መፈክር ማስያዝ አትችልም ምክንያቱም ተገዶ እንኳን ቢወጣ በትግርኛ "ኣነ አምሃራ እየ" ነው የሚለው ሰልፉ ላይ በል ስትለው።አማርኛ አይችልም። ማንነትን መቀየር አትችልም። ምንም ነገር ብታደርግ ስምምነቱን ልታፈርስ አትችልም። አብቅቷል። ማቅራራት ጊዜው አልፎበታል። የፌደራል መንግስቱ ድርሻውን መወጣት አለበት እሱም እንደሚሆን ቃል ገብቷል። ቃል ባይገባም ምንም የሚፈጥረው ነገር የለም ግዴታው ነው።
1.0K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 20:55:51
በሁሉም ትግራዋይ ልብ ውስጥ መቼም የምይረሳ።
1.0K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 20:55:50
ክቡር ፕሬዝደንት ወዲ ረዳ
985 views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 20:55:50
የልሙጡ እና ተለጥፎ ትግራይ የገባው ሀይል አሁናዊ ቁመና።
943 views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ