Get Mystery Box with random crypto!

VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ shewapress — VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹 V
የቴሌግራም ቻናል አርማ shewapress — VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @shewapress
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.95K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ፈጣን እና እውነተኛ መረጃወች ይተላለፉበታል።
መረጃ ፣ ሀሳብ ፣ አስተያዬት ለመስጠት @melkah
የyoutube አድራሻች👉👉
https://youtube.com/channel/UC05y0-96PuPy2yRN0Sk4a3A

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 95

2022-05-11 13:15:12
የጀግናው የእሸቴ ሞገስ ባለቤት፣ የጀግናው የይታገሱ ሞገስ እናት ወይዘሮ ወለላ ይመኑ በዛሬው የባህርዳር ከተማ የጀግና ሜዳሊያ ተሸልመዋል!

@shewapress
12.4K views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 11:10:48 የ አማራ ህዝባዊ ሰራዊት ለ አንድየ እና ለመጨረሻ ግዜ አማራን ከባርነት እና ከተደቀነበት ፈተና ነፃ ሊያወጣ ቆርጦ ተነስቷል።

አማራነኝ ኢትዮጲያን እወዳለሁ የሚል ሁሉ ይሄን ሀይል በቻልነው መጠን ልናግዘው እና አብረነው ልንሰለፍ ይገባል።

#vidoን ሊንኩን ተጮነው ይመልከቱት ዩቲቭ ቻናላችንን #subscribe ማድረግ እንዳይረሱ።

Watch "አስገራሚው ጀግናው ፋኖ ኮማንዶ ።" on YouTube


12.6K views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 09:13:31
የክልል ርእሳነ መሥተዳድሮችና ሚኒስትሮች ባሕር ዳር ገቡ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ የክልል ርእሳነ መሥተዳድሮችና ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የአማራ ክልል መንግሥት ባዘጋጀው በሕግ ማስከበርና በኅልውና ዘመቻ ለተሳተፉ የጸጥታ አካላት የዕውቅና መርኃ ግብር ላይ ለመሳተፍ ባሕር ዳር ገብተዋል።

ለርእሳነ መሥተዳድሮችና ሚኒስትሮች÷ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ጌታቸው ጀምበርና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በባሕር ዳር በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሀገር ለማፍረስ የከፈተውን ጦርነት ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን በማጠናከር የጥፋት መንገዱን አክሽፈዋል።

የአማራ ክልል መንግሥት ባዘጋጀው የምሥጋናና የእውቅና መርኃ ግብር ለጸጥታ አካላት፣ ግለሰቦችና ተቋማት የዕውቅና መርኃ ግብሩ ትናንት መጀመሩ ይታወሳል፡፡

ዛሬም በሕግ ማስከበርና በኅልውና ዘመቻ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መከላከያ፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ ፖሊስ፣ ፋኖ፣ ሚሊሻና የክተት ጥሪ ተሳታፊ የሕዝብ ኀይል ዕውቅና ይሰጣል ነው የተባለው።

ከሽብርተኛው የህወሓት ቡድን ጋር ሲፋለሙ በጀግንነት የተሰውትም ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት በክብር ዕውቅና ይሰጣቸዋል ተብሏል።

በዘመቻው የተሳተፉ ተቋማት፣ ባለሐብቶች፣ የብዙኀን መገናኛዎችና ሌሎች አደረጃጀቶችም ዕውቅና ይሰጣቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የክልል ርእሳነ መሥተዳድሮችም ኢትዮጵያን ለማዳን በተደረገው ዘመቻ ላደረጉት አስተዋጽኦ ዕውቅና ይሰጣቸዋል መባሉን አሚኮ ዘግቧል።

Amc

@Shewapress
13.4K views06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 17:55:27 ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ተይዞ ስለቆየበት ሁኔታ በዝርዝር ተናገረ
.
ከአንድ ሳምንት በላይ ደብዛው ጠፍቶ የነበረው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፤ ከመኖሪያ ቤቱ 'የተደራጀ የሕገ-ወጥ ቡድን' በሚመስል አካል ከተያዘ በኋላ ጦር ኃይሎች አካባቢ ባለ 'የድሮ ቤት' ውስጥ ሳያቆዩኝ አይቀርም አለ። ከአንድ ሳምንት ቆይታ በኋላ ትናንት ግንቦት 01/2014 ዓ.ም. ወደ መኖሪያ ቤቱ የተመለሰው ጋዜጠኛ ጎበዜ፤ ተይዞ ወደቆየበት 'የድሮ ቤት' እስኪደርስ ድረስ እንዲሁም ጥያቄ ሲቀርብለት ዓይኑ በጨርቅ ታስሮ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግሯል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ተይዞ የቆየው ጦር ኃይሎች አካባቢ ባለ ቤት መሆኑን ያወቀው የያዙት ሰዎች ወደ ሥፍራው ለመሄድ አቅጣጫ ሲነጋገሩ ከሰማ በኋላ መሆኑን አስረድቷል።
ጋዜጠኛ ጎበዜ እንዴት ተያዘ?

"የያዙኝ የኢድ በዓል ዋዜማ ዕለት እሁድ ዕለት ረፋድ 4 ሰዓት አካባቢ ነበር" ይላል። 7 ወይም 8 የሚሆኑ ሲቪል የለበሱ እና የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የማይመስሉ ግለሰቦች አያት አካባቢ ወደሚኖርበት ግቢ ዘለው መግባታቸውን ጎበዜ ያስረዳል።

"የፀጥታ ኃይል ናቸው ለማለት ይከብዳል። ድርጊታቸው የመንግሥት የፀጥታ ኃይል አይመስልም። ግቢ ውስጥ ገብተው ሲጯጯሁ ሰው አምልጧቸው የሚፈልጉ እንጂ እኔን ሊይዙ የመጡ አልመሰለኝም ነበር። 'አንተን ነው የምንፈልገው' አሉኝ" ይላል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ የግለሰቦቹን ማንነት ቢጠይቅም ወዲያው ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ እንዳልነበሩ ይናገራል።

"መሳሪያ ይዘዋል። ማናችሁ ብዬ መታወቂያ ስጠይቃቸው መታወቂያ ለማሳየት ፍላጎት የላቸውም። ሲሳደቡ ነበር" ይላል።

በግለሰቦቹ አለባበስ እና ሁኔታ የመንግሥት ኃይሎች ስለመሆናቸው ጥርጣሬ አደረብኝ የሚለው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፤ ሊይዙት የመጡ ሰዎችን እንዲህ ሲል ይገልጻቸዋል።

"አለባበሳቸው የተለያየ ሲሆን ኮፍያ ባለው ሹራብ የተሸፈኑ አሉበት። ፀጉራቸው ያደገ። ሁኔታቸው እንደ 'ጋንግስተር' [አደገኛ ቦዘኔ] ነው። . . . የተደራጀ የሕገ-ወጥ ቡድን መጣ ብዬ ነው ያሰብኩት" ይላል።

ጨምሮም ሊይዙት ከመጡት ሰዎች መካከል አንዱ ቪዲዮ መቅረጽ መጀመሩን ጎበዜ ይናገራል። በተደጋጋሚ ማንነታቸውን ሲጠይቅ ከግለሰቦቹ መካከል አንዱ የፀጥታ ኃይል መሆናቸውን እንደነገረው እና መታወቂያ እንዳሳየው ያስታውሳል።

"ያሳየኝ መታወቂያ የመከላከያ ሠራዊት አባል እና የመረጃ ምናምን ይላል። ከዚያ ወደ ውጪ ይዘውኝ ወጡ" በማለት ጎበዜ ይናገራል።

ጎበዜ ግለሰቦቹ ይዘውት የሄዱበት መኪና የአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሌዳ እንዳለው ይናገራል።

በግለሰቦቹ ተይዞ ከመኖሪያ ቤቱ ከወጣ በኋላ ዓይኑን በጨርቅ ሸፍነው ይዘውት እንደሄዱ ይናገራል። በመኪናው እየተጓዙ፤ "በጣም እየተጯጯሁ ይነጋገራሉ። ከንግግራቸው ጦር ኃይሎች አካባቢ እንደወሰዱኝ ማወቅ ችያለሁ" ይላል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ግለሰቦቹ ይዘውት ወደሚሄዱበት ቦታ 'ጀነራል' እያሉ ከሚጠሩት ግለሰብ ትዕዛዝ ይቀበሉ ነበር ይላል።

"አቅጣጫ እየነገራቸው ነበር ግን ያወቁት አይመስለኝም። መጨረሻ ላይ አንድ ግቢ ውስጥ ይዘውኝ ገቡ። ሰፊ ግቢ ነው። ግቢ ውስጥ ያሉት ቤቶች የድሮ ቤቶች ናቸው። ወለላቸው ጣውላ ነው። እዚያ ነው ይዘው ያቆዩኝ"።

ጎበዜ በቀጣይ ግን መርማሪ መጥቶ ጥያቄ እንዳቀረበለት ይናገራል።

"መርማሪው ሲመጣ ፊቴ ይሸፈናል" ያለው ጋዜጠኛ ጎበዜ፤ ጥያቄ ሲያቀርብለት ከነበረው ግለሰብ ሦስት ጉዳዮች በተደጋጋሚ ማንሳቱን ያስታውሳል።

"የመጀመሪያው አንተ ፋኖን ትደግፋለህ፤ የፋኖ አባል ነህ የሚል ነው። ሁለተኛ ደግሞ አንተ ኦሮሞ ጠል ነህ የሚል ነው። ሦስተኛው ደግሞ በተለያዩ ግጭቶች ውስጥ እጅህ አለበት የሚል ነው" በማለት ያስረዳል።

ጋዜጠኛ ሲሳይ ጥያቄ ሲያቀርቡለት የነበሩት ጉዳዮች በመገናኛ ብዙሃኃን ከሚናገራቸው እና በማኅብራዊ ሚዲያዎች የሚጽፋቸው ጉዳዮች እንደሆኑ ይናገራል።

ጎበዜ ተይዞ በነበረበት ወቅትም ስለያዙት ግለሰቦች ማንነት ጥያቄ ሲያቀርብ እንደነበረና "አንዳንዴ መከላከያ ነን ይላሉ። መከላከያ እና ደኅንነት ተቀናጅተው እንደያዙኝም ይናገራሉ።"

ጋዜጠኛ ጎበዜ ከመኖሪያ ቤቱ ተይዞ ሲወጣ የአገር መከላከያ ሠሌዳ ባለው መኪና መወሰዱ እና ግለሰቦቹ መንገድ ይጠቆሙ የነበሩት 'ጀነራል' እያሉ በሚጠሩት ግለሰብ በመሆኑ ተይዞ የነበረው በአገር መከላከያ እንደሆነ እንደሚያምን ይገልጻል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ታስሮ በነበረበት ወቅት ምንም አይነት አካላዊ ጥቃት እንዳልተፈጸመበት እና የምግብ ችግር እንዳልነበረበት ለቢቢሲ ተናግሯል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ትናንት ግንቦት 1/2014 ዓ.ም. ምሽት 3 ሰዓት አካባቢ ይዘውት የቆዩት ሰዎች ዓይኑን በጨርቅ አስረው መኖሪያ ቤቱ ጥለውት እንደሄዱ ተናግሯል።

ጎበዜ የያዙት ግለሰቦች ከመልቀቃቸው በፊት " 'እንደዚህ አይነት ሥራ አትስራ። አገራችንን የምንገነባው አንድ ላይ ነው። የትም ቦታ ብትሆን ከእኛ አታመልጥም።' የሚል ማስፈራሪያ ምክር ያለበት ንግግር ተናግረውኛል" ይላል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ተይዞ የቆየበት ሁኔታ እና የቀረበበት ማስፈራሪያ ከሚዲያ ሥራው እንደማያዛንፈው ተናግሯል።

"ሊከታተሉኝ ይችላሉ። ቤተሰብ ጓደኛ 'ተው ይቅርብህ' በሚሉ ምክንያቶች ጫናዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ ግን እኔን ወደ ኋላ አይመልሰኝም። በሚዲያ ሥራዬ እቀጥላለሁ።"

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ከዚያም ደግሞ የኛ በሚባል ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ሲሰራ ነበር።

ጋዜጠኛ ጎበዜ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የህወሓት ኃይሎች ወደ አማራ ክልል ዘልቀው በገቡ ወቅት በፌስቡክ ገጹ በሚያጋራቸው መረጃዎች የብዙዎችን ትኩረት ስቦ ነበር።

በጉዳዩ ላይ የአገር መከላከያ ሠራዊት አስተያየትን ለማካተት ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።

BBC Amharic

@Shewapress
@Shewapress
14.2K views14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 17:19:33
ሰበር

ህወሃት ወደ ኤርትራ ሮኬት ተኮሰች። ከመተኮሷ በላይ ጥያቄ የሆነብን ከየት አመጣችው የሚለው ነው???

ከሶስት ቀናት በፊት በራማ እና ባድመ በኩል የኤርትራን ሰራዊት ምት መቋቋም ያቃተው የህወሓት ሰራዊት ወደ ኋላ ማፈግፈጉን ተከትሎ በሮኬት ለማስደንበር ዛሬ ወደ ኤርትራ ወሰን መተኮሷን የመረጫ ምንጮቻችን አድርሰውናል።

@shewapress
@Shewapress
13.5K views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ