Get Mystery Box with random crypto!

VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ shewapress — VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹 V
የቴሌግራም ቻናል አርማ shewapress — VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @shewapress
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.05K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ፈጣን እና እውነተኛ መረጃወች ይተላለፉበታል።
መረጃ ፣ ሀሳብ ፣ አስተያዬት ለመስጠት @melkah
የyoutube አድራሻች👉👉
https://youtube.com/channel/UC05y0-96PuPy2yRN0Sk4a3A

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 88

2022-05-21 17:42:48
#ሰበር

መስከረም አበራ አዲስ አበባ አየር ማረፊያ ላይ በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ታፍናለች።

@Shewapress
9.9K viewsedited  14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 14:51:28 ከ አማራ ህዝባ ሀይል (ፋኖ) የተሰጠ መግለጫ።

የአማራ ሕዝብ በኑሮ ውድነት፣ በህልውና ስጋት፣ በወረራ እና በመሳሰሉት ችግሮች ውስጥ እንዲዳክር ያደረገው መሰረታዊ ምክንያት የሀገሪቱ የፖለቲካ ብልሽት እንደሆነ ይታወቃል። ይህንን የፖለቲካ ብልሽት ያመጡት ደግሞ ደካሞች እና ግብዞች የተሰባሰቡበት የአማራ ብልፅግና ነው።
በሀገሪቱ የፖለቲካ የኃይል ሚዛን ውስጥ የሚወክለውን ህዝብ ወርድ እና ቁመት የሚመጥን የኃይል አሰላለፍ ማስመር ያልቻለው እና ከስህተቱ መማር የማይችለው ቡድን ከዚህ ቀደም በኮራባሎች አሁን ደግሞ በቴክኖክራቶች ታግዞ አንድ ጋት አሻግሮ መመልከት በማይችለው እይታው አማራውንም ኢትዮጵያንም ወደ ከፋ አዘቅት ውስጥ እየከተተ ይገኛል።

"የኦህዴድ-ኦነግ-ኦፌኮን ጥምረት" ለማስደሰት በሚደረግ ሩጫ ውስጥ ውድ የአማራ ልጆችን ህይወት ለመቅጠፍ ሌት ከቀን እየባዘነ ይገኛል። የፌደራል መንግስትም ሆነ የክልሉ መንግስት ባወጡት መግለጫ ህግ የምናስከብረው ሰዉ ወጦ መግባት ስላልቻለ፣ ስለተዘረፈ ነው ይበሉ እንጅ እነሱ እየጨፈጨፉት ያለው ይህንኑ ወንጀል ተሰራበት የሚሉትን ህዝብ ነው።

ኦነግ ሸኔ በሽወች የሚቆጠሩ አመራሮችን ገድሏል። ሁለት ሶስት ዞኖችን ተቆጣጥሯል። በብዙ የወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ አካባቢወች ባንዲራውን ሰቅሏል። የሚታገለውም የኦሮሞ ነፃ መንግስት ለመመስረት መሆኑ ይታወቃል። ፋኖን ከሸኔ ጋር ለማመጣጠን የሚያበቃ አንዳችም ነገር ባይኖርም ብአዴን የኦሮሞ ብሔርተኞችን ለማስደሰት በሚያደርገው ሩጫ ውስጥ ራሱን ጠልፎ እየጣለ መሆኑን ሊገነዘበው ይገባል።

ሞጣ፣ ወልድያ እና መርዓዊን ጨምሮ ከቀናት በፊት የሰላም አየር የነበረባቸውን ከተሞች የወራሪ ጦር ዘመቻ በሚመስል መልኩ በንፁሃን የደም ጎርፍ ያጠበው ክልሉን አስተዳድራለሁ የሚለው ኋላ ቀር መንግስት መሆኑ የአደባባይ ሐቅ ነው።

በብዙ የክልሉ አካባቢወች አፈናውን የሸሹ ወጣቶች፣ ፋኖወች እና ምሁራን ጫካ ገብተዋል። በአንዳንድ አካባቢወችም አፈናውን የመከላከል ውጊያ እየተደረገ ነው። ይሁን እንጅ የክልሉ መንግስት በያዘው የእብሪት እና የግብዝነት አቋም በመቀጠሉ ክልሉ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ይገኛል።

ስለሆነም በህግ ማስከበር ስም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣ ያለ ተጨባጭ ወንጀል፣ ያለ አስቸኳይ ግዜ አዋጅ ግለሰቦችን የማፈን እና ወደ Concentration ካምፕ የማስገባት ህገ ወጥ አሰራር እንዲቋረጥ እንዲሁም በኑሮ ውድነት እየተጠበሰ ባለው ከተሜ እና በማዳበሪያ እጥረት በሚሰቃየው አርሶ አደር ላይ የተጀመረው "ወረራ" በአስቸኳይ እንዲቆም ሁሉም በየድርሻው ርብርብ እንዲያደርግ እናሳስባለን።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
ግንቦት 13 ቀን 2014 ዓ.ም
ባሕር ዳር-ኢትዮጵያ

@shewapress
@Shewapress
11.8K viewsedited  11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 12:17:55
የጎንደር ፋኖ ሻለቃ ሸርብን ከአፋኙ ቡድን ማስለቀቅ ችሏል።

ሌሎቻችሁም ተናበቡ ከጎንደር ፋኖ ተማሩ።

@shewapress
12.2K views09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 11:36:33
የመዲናዋ ህንፃዎች ግራጫ ቀለም ሊቀቡ ነው በሚል የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው ተባለ

የአዲስ አበባ ህንፃዎች ሁሉ ግራጫ ቀለም ሊቀቡ ነው በሚል ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ አስታወቁ።

የቢሮ ኃላፊው በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የህንፃ ስታንዳርድና የውጭ ማስታወቂያ ስታንዳርድ እየተዘጋጀ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህን መነሻ አድርጎ በማህበራዊ ትስስር ገጾች አዲስ ከተማ ግራጫ ቀለም ልትቀባ ነው በሚል በስፋት ሲዘዋወር የታየው መረጃ የተሳሳተ ነው ብለዋል፡፡

እስካሁን ድረስ የከተማዋ ህንጻዎች ቀለም ምን አይነት ይሁን የሚለው ጉዳይ ለውይይት ቀረበ እንጂ የከተማ አስተዳደሩ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ውሳኔ እንዳላሳለፈ አመልክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይም ከዚህ ቀደም ‹‹ከተማችን ቡራቡሬ ሆና ባለቤት አልባ መስላለች›› ማለታቸውን ያስታወሱት የቢሮ ኃላፊው፤ ይህን ችግር ማንኛውም የመዲናዋ ነዋሪም ሊታዘብ ይችላል። የከተማ አስተዳደሩም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቷል ብለዋል።

ችግሩን ለመፍታት የውጭ ማስታወቂያውና የከተ ማዋ ቀለም ሁኔታ የሚመራበት ስታንዳርድ ዝግጅት ተደረገ እንጂ ውሳኔ ላይ አለመድረሱን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

@shewapress
12.2K views08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 10:00:53
በብልፅግና ሰራዊትበግፍ የተገ*ደለዉን የምስራቅ አማራ ፋኖ አማረ ለመሸኘት ዝግጅት ተጀምሯል።

"ፋኖ አማራ እኔ ነኝ!"
"አማራን አዋርዶ መግዛት ታሪክን አለማወቅ ነው ለክብራችን አንደፈርም!"

በወልዲያ ወጣቶች ድምፅ መሪ መፈክር!!

የሸዋ ፕረስ መረጃወችን በተለያዩ አማራጮች ለማግኘት

https://youtube.com/channel/UC05y0-96PuPy2yRN0Sk4a3A

FaceBook:https://www.facebook.com/shewapressss

https://www.facebook.com/shewapresss

Telegram https://t.me/shewapress

Tiktok https://vm.tiktok.com/ZMLTVkrs5/
12.8K viewsedited  07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 07:44:32 ትጥቅ አስፈታለሁ የሚባለው ነገር ደምና ስጋችንን እንደ መለያየት ነው እኛ የ አሳምነው ልጆች ነን።

የፋኖ ጥብቅ አቋም እና መልዕክት።

on YouTube


13.3K views04:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 21:21:25
ለጊዜው ሰፋ ባለ ሀሳብ መግባባት አዳጋች እንደሚሆን ይጠበቃል። ባጭሩ፣ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀሙ ጅምላ አፈናዎችና ጥቃቶች ባስቸኳይ መቆም አለባቸው ነው። በወገኖቻችን ላይ የአካልና የሞት ጉዳት ያደረሱ አካላት ተጠያቂ መሆን አለባቸው ነው። የተፈፀመውን ነገር ለማስተባበልና ለማድበስበስ የሚያስችል ምንም አይነት ምክንያት ማቅረብ አይቻልም!

ችግሩ እንዳይባባስና በህዝባችን ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያስከትል ጥረት ማድረግ ይገባል። ይሄው ነው!

የሱፍ ኢብራሔም

@shewapress
6.5K viewsedited  18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 20:20:22
የአማራ ልዩ ሃይል ከአፋኙ ሰራዊት ጋር ትብብር እንደሌለዉ ወልዲያ ላይ የታፈኑትን ፋኖዎችን በማስለቀቅ አረጋግጧል።

ወልድያን አተራምሶ ማምሻውን ደግሞ ወደ ራያ ቆቦ ያቀናው አፋኝ ቡድን 7 የዞብአምባ ብርጌድ ህዝባዊ ሃይል/ፋኖ አፍኖ ወደጣቢያ የወሰደ ቢሆንም በፋኖ ሃይሉ ብርቱ ጥረትና የአማራ ልዩ ሃይል ድንቅ አጋዥነት ልጆቹን አስለቅቀዋል::

@shewapress
8.7K views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 18:03:13 የአርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ ጥፋት አማራ ተደራጅቶ ከጠላቶቹ እና ከወራሪወቹ እራሱን ይጠብቅ ማለቱ ብቻ ነው

ስልጣን እንደማይፈልግም ለገዝው መንግስት አስረግጦ ነግሯቸዋል።

አርበኛ ዘመነ ካሴ ለመንግስት ያስተላለፈውን መልዕክቱን ላልሰማችሁ ወይም ለትውስታ

Watch "አርበኛ ዘመነ ካሴ ለመንግስት ያስተላለፈው አስደናቂ መልእክት።" on YouTube


10.7K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 17:36:24
ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ የ10 ቀን ቀነ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው!

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ባህርዳር ከተማ ፖሊስ መምሪያና የአማራ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮምሽን ጀነራል ተፈራ ማሞን ፍ/ቤት እንዲያቀርቡ ባስተላለፈው ትዕዛዝ መሰረት በዛሬው እለት ፍ/ቤት ቀርበዋል።

አቃቢ ህግ የክስ ዝርዝሩን በኢሳትና መሰል ሚድያዎች ቃለ መጠይቅ በመስጠት ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል ሲል አሰምቷል።

ባመለከቱት የዋስትና ጥያቄ ጉዳይ ፍርድ ቤት የቀረቡት ጀነራሉ የጠየቁት የዋስትና መብት ውድቅ ተደርጎ ለግንቦት 22 2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።

@shewapress
10.6K views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ