Get Mystery Box with random crypto!

VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ shewapress — VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹 V
የቴሌግራም ቻናል አርማ shewapress — VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @shewapress
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.05K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ፈጣን እና እውነተኛ መረጃወች ይተላለፉበታል።
መረጃ ፣ ሀሳብ ፣ አስተያዬት ለመስጠት @melkah
የyoutube አድራሻች👉👉
https://youtube.com/channel/UC05y0-96PuPy2yRN0Sk4a3A

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 89

2022-05-20 17:30:33
ሰላም ያረፈደችው ወልድ ከተማ በ አፋኙ የብልፅግና መንግስት ሰራዊት እየታመሰች ነዉ?!

መከላከያ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ተኩስ ከፍቶ እያወደማት ነው።
በርካቶች ተጎድተዋል አዳጎ ላይ የነበረው ሁኔታም ወደሙጋድ ፣ መነሀሪያና ፒያሳ ተስፋፍቷል ፣ከተኩስ የተረፈው ህዝብ በየመንደሩ መውጫ መግቢያዎች ላይ ተፋጧል::

@shewapress
9.9K views14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 16:23:18
#መረጃ

ዛሬ ወልዲያ ላይ 17 ኦነግ ሸኔ የመከላከያን ልብስ ለብሰው ወልዲያ ላይ በአማራ ክልል ልዩ ሀይል ተይዘዋል!!!

Mohammed Hassen

@Shewapress
10.9K views13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 16:02:13
በአማራ ሕዝብ ላይ እየተደረገ ያለው መንግስታዊ አፈና በእጅጉ የጠበቅነውን የአገራዊ ምክክር የትብብር ቀና እርሾዎችን እየደፋ ነው። በዚህ መንገድ ግን መቼውንም ስለጋራ ነገ ማሰብ ከባድ ይሆናል። አዝናለሁ!

ክርስቲያን ታደለ

@shewapress
10.7K views13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 14:11:33 ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተላለፈ መልዕክት

ለመላው የአማራ ህዝብ በሙሉ!

ወልድያ ከተማ አዳጎ አደባባይ የሚገኘው የምስራቅ አማራ ፋኖ ሎጅስቲክ ካምፓችን በአድማ ብተና ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት ከበባ ተደርጎብናል።

በህልዉና ትግሉ ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ከአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ጎን በመሰለፍ ታላቅ መስዋዕትነት በመክፈል አገራችንን ከመፍረስ ታድገናል። በአሁኑ ጊዜም ራያ ግንባር ጎለሻ እና አዲስ ቅኝ ከትግሬ ወራሪ ሃይል ጋር ተፋጠን ምሽግ ላይ እንገኛለን። ምሽግ ላለው ሰራዊታችን የሚሆን ቀለብ የምናከማችበትን የትግሬ ወራሪ ሃይል አባል የሆነ ህንጻ ካለቀቃችሁ በሚል ሰበብ እኛን የማፍረስ ተግባር እየተፈጸመብን ይገኛል።

ከ 130 በላይ ቁስለኛ እና ከ 80 በላይ መስዋዕትነት የከፈሉ ጉዶቻችንን አደራ እና ቤተሰቦቻቸዉን ይዘን ባለንበት በአሁኑ ጊዜ አባላቶቻችን ላይ ወከባ ከበባ አፈናና እስራት እየተካሄደብን ይገኛል። ይሄ ድርጊት በተዘዋዋሪ ፋኖን የማፍረስ ብሎም አማራን አንገት የማስደፋት እና ፍትህ እኩልነትና ነጻነት የመንፈግ ተግባር መሆኑን ሁሉም የአማራ ህዝብ ሊገነዘበው ይገባል።

ስለሆነም መላው የአማራ ህዝብ እና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እየተደረገብን ያለዉን ህግ በማስከበር ሰበብ አማራን አንገት የማስደፋት ተግባር በትግስት እያየን ያለንበት ሁኔታ ከአቅም በላይ በመሆኑ መላው የአማራ ህዝብ ከጎናችን እንዲሰለፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

* በዚህ አጋጣሚም የሃገር መከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ሃይል ሚሊሻ አድማ ብተናና ህዝባዊ ፖሊስ ወንድም እህቶቻችን ሁላችንም በአንድ ምሽግ በጋራ ጠላታችንን ታግለናልና እየሆነ ያለዉን ነገር ህግ ከማስከበር የዘለለ ተግባር መሆኑን አውቃችሁ ሁኔታዉን በሰላማዊ መንገድ በጋራ እንድንፈታው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

@shewapress
11.7K views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 13:33:43
ከሸዋ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ

ፋኖን በማሳደድ እና የተለያዩ አፈናዎችን ለማድረግ በመሞከር የአማራ ህዝብን ጥያቄ ማስቆም አይቻልም

የአማራው ህዝብ ከምን ጊዜውም በላይ አንድነቱን አስጠንቆ የተቃጣበትን የህልውና አደጋ መቀልበስ በሚያስፈልግበት ሰዓት ፋኖን እና የአማራን ምሁራንን፣የማህበረሰብ አንቂወችንና የተቀዋሚ ፓርቲ አመራሮችን በማፈን እና ለማፈን ሙከራ ማድረጉ እጅግ በጣም ዋጋ የሚያስከፍል ተግባር መሆኑን አዉቃችሁ ይህንን ተግባር በአስቸኳይ እንዲትቆሙ እናሳስባለን!!

በተለይ በዛሬዉ እለት በነጻነት ታጋዩ አርበኛ ዘመነ ካሴ ላይ እየተደረገ ያለውን ከበባ ባስቸኳይ እንዲቆም እናሳስባለን!
አማራ ባራቱም አቅጣጫ ተከቦ የጦር ነጋሪት እየተጎሰመበት ባለበት ሰዓት የአማራ አፈና ማከናወን የህዝባችንን ልዕልና መጋፋት እና ከጠላት ጋር ማበር መሆኑ ታውቆ የመንግስት የጸጥታ አካላት ነኛ ባዮች ባስቸኳይ ከዚህ ድርጊታችሁ ታቅባችሁ ያፋናችኋቸውን የአማራ ልጆች ባስቸኳይ እንድትለቁ ስንል እናሳስባለን።

ያ ሳይሆን ቀርቶ በማናለብኝነት ለሚደረግ ማንኛው የጸረ ሰላም እንቅስቃሴ የሸዋ ፋኖ በተለያዩ የአማራ ግዛቶች ከሚገኙ የትግል አጋሮቹ ጋር በመሆን ምላሽ የሚሰጥ መሆኑ ታውቆ በዚህ ሂደት ውስጥ ለሚፈጠር ነገር ሙሉ ሃላፊነቱን መንግስት ይወስዳል!!!

ድል ለተገፋው እና ጭቁኑ ህዝብ!!!
ሸዋ ፋኖ ግንቦት 12/2014

@shewapress
11.4K viewsedited  10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 13:24:40 በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአብን አባላት የተሰጠ መግለጫ!

*

በሕግ ማስከበር ስም የሚነሱ የሕዝብ ጥያቄዎችንና ጠያቂዎችን የማጥፋትና ሕዝባችንን አንገት የማስደፋት እንቅስቃሴ አጥብቀን እንቃወማለን!

(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የሕዝብ ተወካይ አባላት የተሰጠ መግለጫ፤)
*
ባለፉት አራት ዓመታት በሕዝባችን ላይ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚደርስበት ሁሉንአቀፍ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጅምላ ጭፍጨፋ፣ መፈናቀል ቅርጹንና አድማሱን እያሰፋ ተባብሶ ቀጥሏል። ይባስ ብሎም ትሕነግ፣ የቤንሻንጉል ነጻ አውጭና ኦነግ ሸኔ የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት ይፋዊ ጦርነት ከፍተው ሕዝባችን ኅልውናው አደጋ ላይ ወድቆ በጠላቶቹ ከበባ ሥር ይገኛል።

እኛ የአብን የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትም መንግስት ትንሹን መንግስታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣና የሕዝባችንን ደኅንነት እንዲያረጋግጥ ስንወተውት ቆይተናል። ሆኖም መንግስት ለማሳሰቢያችን ጀሮ ባለመስጠቱና ስጋታችንን ባለመጋራቱ ሕዝባችን ማንነትን መሰረት ላደረገ ጅምላ ጭፍጨፋ፣ መፈናቀልና ስደት ከመዳረጉም በላይ ከተሞቹና በዘመናት ሂደት ያፈራው ንብረት ወድሞ ለአካላዊና ሥነልቦናዊ ችግር ተጋልጦ ይገኛል። በዚህም ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ በአገር ውስጥ መፈናቀል ከዓለም ቀዳሚ እስከመሆን ደርሳለች፡፡

ይባስ ብሎም የዜጎችን ኹለንተናዊ ደኅንነት ማስጠበቅ፣ ሕግና ሥርዓትን ማንበርና የተሳለጠ አመራር መስጠት ያልቻለው መንግሥት ሕዝባችን በትሕነግና ምስለኔዎቹ ኅልውናው አደጋ ላይ በወደቀበት በአሁኑ ጊዜ በነቁ አማሮች ማለትም በአብን አባላትና አመራሮች፣ በፋኖ አባላትና አገራቸውንና ሕዝባቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ባገለገሉ የጦር መኮነኖች ላይ ማንነትን መሰረት ባደረገ መልኩ የአፈና፣ የሕገ-ወጥ እስር እና የመንግስታዊ እገታ ሥራዎች ላይ መጠመዱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአብን የሕዝብ ተወካይ አባላትን አሳዝኖናል፡፡

መንግስት የሕዝባችንን ደኅንነት ለማረጋገጥና አገራዊ አንድነትን ለማንበር ከፖለቲካዊ ሴራ በጸዳ አኳኋን ሕግ ቢያስከብር እኛም ከመረጠን ሕዝብ ጋር ሆነን የምንደግፈው ቢሆንም አሁን እየተደረገ ያለው ግን ሕግ ማስከበር ሳይሆን በአማራ ሕዝብ የሚነሱ የሕዝብ ጥያቄዎችንና ጠያቂዎችን የማጥፋትና ሕዝባችንን አንገት የማስደፋት እንቅስቃሴ ነው። ይኼን ጉዳይ ለሕዝባችን ክብር ካለን ጽኑ ፍቅርና ታማኝነት የተነሳ በቸልታ የማንመለከተውና ከሕዝባችን ጋር ሆነን የምንታገለው ያደረ አማራ ጠል እሳቤ ነው። በመሆኑም እኛ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአብን የሕዝብ ተወካይ አባላት መንግስት በሕግ ማስከበር ስም እያደረገ ባለው መንግስታዊ እገታና አፈና አሳሳቢነት ላይ ከተወያዬን በኋላ፦

፩. በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን አባላትና አመራሮች፣ በፋኖ አባላት፣ በሕጋዊ ታጣቂዎችና ወጣቶች እንዲሁም አገራቸውንና ሕዝባቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያገለገሉ የጦር መኮነኖችንና የጸጥታ አመራሮች ላይ የሚፈጸመው መንግስታዊ እገታና ስወራ በአስቸኳይ እንዲቆምና በዚህ ሰበብ በማንነታቸው ብቻ የታገቱ አካላትም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን፡፡

፪. መንግስት በሕዝባችን ላይ እየፈፀመ ያለው ማዋከብ የታወቀ ጠላት የሚያደርገው ዓይነት ሲሆን ማዋከቡ በአስቸኳይ የማይቆም ከሆነ አገርና ሕዝብ በጉጉት የሚጠብቀው የአገራዊ ምክክር ከወዲሁ እንዲጨናገፍ የሚያደርግ ውጤት የሚያስከትል መሆኑን አጥብቀን ለማሳሰብ እንወዳለን።

፫. ሕግ ማስከበርን ሰበብ በማድረግ የፌደራል የፀጥታ መዋቅር በሕገ መንግሥቱ ለክልልና ለፌድራል ተለይቶ የተሰጠውን ኃላፊነት እና ሚና በደፈጠጠ መልኩ ክልሉን በሕገ-ወጥ መንገድ ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆም እና የክልሉ መንግስት በፌደራል መንግስቱ ለሚፈጸመው መንግስታዊ እገታና ስወራ ተባባሪ ከመሆን ወጥቶ የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት እንዲያስከብር እየጠየቅን ጉዳዮቹን በሰላማዊ መንገድ በውይይት እንዲፈታ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

፬. በሕግ ማስከበር ሰበብ ከተሞችን የጦር አውድማ የማድረግና ንጹሐንን መግደል መንግስታዊ ሽብር በመሆኑ መንግስት የሚያደርገውን ይሄን ሕገወጥ የሽብር ሥራ በአስቸኳይ አቁሞ ሕዝባችንን በማወያዬት የሕዝብ ፍላጎቶችና ድምጾች እንዲሰሙ እንጠይቃለን፡፡

፭. መላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆችም መሰል መንግስት በአማራ ሕዝብ ላይ ያወጀውን መንግስታዊ ሽብርና ጦርነት እንዲያቆም መንግስት ላይ ጫና እንድታሳድሩ ለአማራ ሕዝብ ያላቸሁን አጋርነትም በተግባር እንዲያሳዩ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

፮. መላው የአማራ ሕዝብ በዚህ ፈታኝ ወቅት ውስጣዊ አንድነቱን እንዲያጠናክር እየጠየቅን በአማራ ስም የተደራጃችሁ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች፣ ወጣቶች፣ ምሁራንና መላው ሕዝባችን የአማራ ሕዝብ ላይ የተጋረጠውን የኅልውና አደጋና ከበባ በመቀልበስ ልጆቹን እንዲጠብቅ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!
ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ!

@shewapress
10.9K viewsedited  10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 12:29:37
#ሰበር መረጃ

የ አማራ አንቂወች በ አፋኙ ቡድን እየታፈሱ ነው

አክቲቪስት ቲና በላይ ታፍና ተወስዳለች።

አክቲቪስት ቲና በላይ በአሁኑ ሰዓት ባህር ዳር 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደምትገኝ ታውቋል።

የ አማራ አይን የሆኑ ልጆችን በማፈን የሚመጣ ለውጥ አይኖር።

@shewapress
11.2K views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 11:53:06 ከ አማራ ህዝባዊ ሀይል (ፋኖ) የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ሕዝብ የተደቀነበትን ተጨባጭ የህልውና አደጋ እንደ ህዝብ መመከት የሚችልበትን አቅጣጫ ከማሳየታችን በስተቀር አንዳችም የወንጀል ድርጊት አልፈፀምንም። ብልፅግና እና አሽከሮቹ ዛሬ ላይ የሚያሳድዷቸው አባሎቻችን ወንጀል ምንድን ነው? ተብለው አስር ግዜ ቢጠየቁ የሚሰጡት ብቸኛ መልስ ፎቶ ተነስታችኋል። ከተማ ውስጥ መሳሪያ ይዛችሁ ታይታችኋል የሚል ነው።

የብልፅግና መንግስት እስካሁን ድረስ በአሽሙርም በቀጥታም በእኛ ላይ ውግዘት ሲያደርስ ከመቆየቱ በስተቀር ኃላፊነት እንደሚሰማው መዋቅር ከእኛ ጋር የፊት ለፊት ውይይት ለማድረግ ፍላጎት አሳይቶ አያውቅም።

ይሁን እንጅ ህግ ማስከበር በሚል ስም በተከፈተው የፋኖ ብተና ዘመቻ የአማራ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ) አመራር እና አባላትን፣ ሌሎች የፋኖ አደረጃጀቶችን እና የነቁ ወጣት እና ምሁራንን ያለ ህጋዊ መንገድ ያለ መያዣ እና መበርበሪያ ትዕዛዝ በሌሊትም ጭምር እያፈነ ይገኛል።
ይኸ ዘመቻ አማራን የማንበርከክ ዘመቻ እንደሆነ መሬት ላይ እየተከናወነ ካለው ሂደት በቀላሉ መረዳት ይቻላል። በርካታ ንፁሃንን እና ለሀገር ዋጋ የከፈሉ ፋኖወች በጥይት እየተገደሉ ነው። ሌሎችም እየተሳደዱ ነው።

ስለሆነም:-
1/ የአማራ ሕዝብ ወንዝ እና ድንበር ሳይገድብህ ይህንን "ድምፅ አልባ ወረራ" በመቃወም ከፍትህ እና ከልጆችህ ጎን በመቆም በማንኛውም ዓይነት የትግል መንገድ ወራሪውን እንድትከላከል፣

2/ መላው አባላቶቻችን አርበኛ ዘመነ ካሴን ጨምሮ በሁሉም የህዝባዊ ኃይሉ አመራር እና አባላት ላይ እየተደረገ ያለውን አፈና እና ወረራ በመስበር ታሪካችንን በደማቅ ቀለም እንድንፅፍ፣

3/ መላው የአማራ ፋኖ በተናጥል እና በጅምላ የተደቀነበትን የመጥፋት አደጋ እና የአማራን ህዝብ የመወረር ተጨባጭ ሃቅ በመገንዘብ ህዝቡን በከፍተኛ ቁርጠኝነት፣ ትጋት እና ፍጥነት ህዝቡን በማስተባበር አፋኙ እና ወራሪው ቡድን ከድርጊቱ እንዲታቀብ የሚያደርግ ማናቸውንም የትግል መንገዶች እንድንጠቀም፣

4/ የአማራ ልዩ ኃይል እና አድማ ብተና አባላት በወንድሞቻችሁ ላይ ምላጭ ላለመሳብ ያሳያችሁትን ስክነት እና ህዝባዊነት አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እና የፀረ-ወረራ ተጋድሎውን እንድትቀላቀሉ፣

5/ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የማንንም መብት ሳንነካ፣ ንፁሃንን ሳንገድል፣ ሳንዘርፍ፣ ሳንደፍር፣ መንግስትን በሃይል የመገልበጥ ተግባር ውስጥ ሳንገባ የአማራን ህዝብ ህልውና እና የኢትዮጵያን አንድነት ለማፅናት የሚበጅ አደረጃጀት ለመፍጠር ስለጣርን ብቻ እንድንጠፋ የተዘመተብን መሆኑንን ተገንዝበህ ከጎናችን እንድትቆም ጥሪ እናስተላልፋለን።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ
ግንቦት 13 ቀን 2014 ዓ.ም
ባሕርዳር-ኢትዮጵያ

@Shewapress
11.4K viewsedited  08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 11:46:11
#ወልድያ አሁን!

በ ብልፅግና አፋኝ ቡድን ያላግባብ የታፈኑትና የታሰሩትን የወልድያ ወጣት ፍቱልን በሚል አደባባይ ወቷል : የትራንስፖርት እንቅስቃሴውም ቆሟል::

አዳጎ የሚገኘው የፋኖ ካንፕን ለማፈን የተሞከረ ቢሆንም ሁሉም በተጠንቀቅ ሆኖ በመጠበቁ እስካሁን አልተሳካም::

@shewapress
11.5K views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 10:40:51 የ አማራ ህዝብ ሆይ ሀብታሙ አያሌው ሀቁን ነግሮሃል ዳግም ጀግኖችህን እንዳታስበላ ከጀግኖችህ ጎን አሁን ነው መቆም ጀግኖችህን ካስበላህ ቡሃላ የ ጀግኖችህን ስም እየጠሩ መፎከር ከውርደት በስተቀር ጥቅም አይኖረውም።



12.3K views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ