Get Mystery Box with random crypto!

VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ shewapress — VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹 V
የቴሌግራም ቻናል አርማ shewapress — VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @shewapress
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.05K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ፈጣን እና እውነተኛ መረጃወች ይተላለፉበታል።
መረጃ ፣ ሀሳብ ፣ አስተያዬት ለመስጠት @melkah
የyoutube አድራሻች👉👉
https://youtube.com/channel/UC05y0-96PuPy2yRN0Sk4a3A

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 93

2022-05-15 15:30:21
የአማራ ልዩ ሃይል ከወልቃይት ሆመራ ኮሪደር ጠቅልሎ ወጣ

ዛሬ የወጣው የመጨረሻው 3 የአማራ ልዩ ሀይል ሻለቃም ዛሪማ አካባቢ እንዲሰፍር ተደርጓል።

ፋኖ ግን ቀደም ብሎ ሙሉ በሙሉ ከአካባቢው ነቅሎ እንዲወጣ ሆኗል።

በባዕከር እና ሁመራ እንዲሁም በሱዳን ኮሪደር ቀጠናውን ከአሸባሪ ሀይል ሲቆጣጠር የነበረው የኤርትራ ጦርም በአብይ አህመድ ውጡልኝ ትዕዛዝ፣ ዛሬ ሙሉ በሙሉ አካባቢውን ትቶ ወደ ራሱ ቀጠና እንዲሄድ ተደርጓል።

አሁን ወልቃይት ሆመራ ኮሪደር ተሸፈነ የሚባለው በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሲሆን፣ መከላከያውም በአብይ አህመድ ቀጭን ትዕዛዝ ወልቃይትን ለቀህ ውጣ ሲባል ለቅቆ እንደሚወጣ ግልፅ ነው።

@shewapress
10.0K viewsedited  12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 14:27:29
ግንቦት 07 ቀን 2014 ዓ.ም የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በየጁቤ ወረዳ ለወራት ያህክል መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና የወሰዱ የሶስተኛ ዙር ሰልጣኞችን አስመርቋል!

በምርቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ አርቲስት መብሬ መንግስቴ እና አርቲስት ስማቸው ካሳ ተገኝተው የጀግንነት ስራን የሚያወድሱ የሙዚቃ ስራወችን አቅርበዋል።

@Shewapress
@Shewapress
1.1K views11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 11:30:24
ዛሬ ማለትም ግንቦት 7 2014 ዓም የአማራ ፋኖ ምንሊክ ብርጌድ አዛዥ አንተነህ ድረስና ምክትል አዛዥ አርበኛ መብረቱ እና አባላቶቹን በመያዝ ወደ ወልቃይት እያቀኑ ባሉበት ወቅት ሙሴባንብ ላይ በመከላከያ ተከበው ይገኛሉ ።በአዛዡ አንተነህ ድረስ ላይ ከዚህ በፊት የተለያዩ ሴራወች የሀስት ክሶች ስም የማጥፋቶች ሲያቀርቡበት የነበረም ሲሆን ህዝቡም እውነታውን ስለሚያውቅና አንተነህም ከእውነት ጋር በመቆሙ አሸናፊ መሆን ችሏል ብለዋል ምንጮቻችን ።

Ashara media

@Shewapress
@Shewapress
5.6K views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 07:27:20 ለዛሬ እዚህ መድረስ የብዙ ጀግና ፋኖወች ሂወት ተከፍሎልናል።

ስለ ፋኖ አላማ ፋኖ ሞላ ደስየ በክብር ከመሰዋቱ በፊት የተናገረው።
ፋኖ ነበልባሉ እሱ ሞቶ ሰው እንድኖር ያደርጋል ፣ፋኖ ነበልባሉ ሂወትን ሰጥቶ ሂወትን ያኖራል።

ሊንኩን ተጭነው ያዳምጡት

" on YouTube


4.5K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 14:49:48
"የአማራነት እሴታችንን አድሰናል" - ዘመነ ካሴ

አዲሱ የአማራ ትውልድ ባለፉት 50 አመታት ሲገዘገዝ የነበረውን አማራነት ነው ከፈዘዘበት እንደገና ቀስቅሰን ያስነሳነው፣ የተጠራቀመውን የፖለቲካ ክፋት አቧራ ነው አራግፈን እንዲያንፀባርቅ ያደረግነው፣ የጠወለገውን ቅጠል ነው እንደገና ውሃ ፈሶበት እንዲለመልም ያደረግነው።

ፋኖነት እና አርበኝነት የሚባሉ የአማራ እሴቶች እንዲጠፉ ተደርጎ ነበር። ይሄን አሁን እየመለስነው ነው። የአማራነት እሴታችንን አድሰናል።

ከ15 ቀናት በፊት BBC አማርኛ ቃለ መጠይቅ አድርጎልኝ ነበር። ነገር ግን አላስተላለፈውም። ከውጭም፣ ከውስጥም ከእየ ጉድጓዱ ተጠራርቶ የመጣውን ጠላታችንን በሃይላችን እንበትነዋለን።

አርበኛ እና ፋኖ ዘመነ ካሴ - ለEthio 360 የተናገረው

@shewapress
2.5K views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 10:22:14 ባህርዳር ከተማ

ህዝብ ሲሸልምህ እንደዚህ ነው
ዘመነ ካሴ በለው
ዘመነ ካሴ በለው

https://vm.tiktok.com/ZMLcNdmWt/?k=1
3.2K views07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 19:54:03 ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፀጥታ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፀጥታው ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ በዝርዝር ገምግሟል፡፡ የወያኔ ወራሪ ቡድን በየቀኑ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ የትግራይን ህዝብ ለጦርነት እያነሳሳ በአማራ ክልል ላይ ዳግም ጦርነት አውጇል፡፡

ይህን አደገኛ ቅዠቱን ለመመከትና ለመቀልበስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የክልሉ መንግስት የፀጥታ ምክርቤት በአንክሮ ተወያይቶበታል፡፡ ጸጥታ ምክርቤቱ በየደረጃው ያለው የፀጥታ መዋቅር ዝግጁ መሆን እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በሌላ በኩል በየደረጃው በተደረጉ ህዝባዊ ውይይቶች ላይ ጎልተው ከወጡ ወሳኝ ጉዳዮች መካከል አንዱ የህግ ማስከበር ስራ መላላት ተጠቃሽ መሆኑን ጸጥታ ምክር ቤቱ በጥልቀት አንስቷል፡፡

በቅርብ ጊዜ ደግሞ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የአማራን የውስጥ አንድነት ለማዳከም፣ ህዝብ ከህዝብ በማጋጨትና በማጋደል ላይ ተሰማርተው ለጠላት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እየሰሩ ያሉ የተደራጁና ያልተደራጁ ኃይሎች እየተበራከቱ መምጣታቸው ተጨባጭ የፀጥታ ስጋት እየፈጠሩ መሆኑን በዝርዝር ተወያይቶበታል፡፡

እነዚህ ኃይሎች በእምነት፣ በፖለቲካ፣ በብሔር ህዝባችን እየከፋፈሉ የአማራን የውስጥ አንድነት በማዳከም ለጥቃት ተጋላጭ እንዲሆን የሚያደርጉት ሙከራ በአጭር ካልተቀጨ በህዝባችንና በክልላችን ሰላምና ደህንነት ላይ ዘላቂ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ድምዳሜ ላይ ደርሶአል፡፡

የህገ-ወጥ ንግድን በማስፋፋት ካለው ሀገራዊ የምርት እጥረት በተጨማሪ ሰው ሰራሽ የምርት እጥረት በመፍጠር የኑሮ ውድነት የሚያባብሱ፣ ምርትን ለጠላት በኮንትሮባንድ አሳልፈው የሚልኩ፣ የህዝብን ሃብት የሚዘርፉ፣ የዜጐችን ነጻ እንቅስቃሴ የሚገድቡ ድርጊቶች በየአካባቢው ያቆጠቆጡ መጥተው ለክልሉ የፀጥታ ስጋት መሆናቸውን ጸጥታ ምክርቤቱ ለይቷል፡፡ ከዚህም በላይ በተለያዩ የክልሉ አካባቢወች እየተስፋፋ የመጣው ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር የክልሉን ሰላምና ደህንነት ስጋት ውስጥ እየጣለ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም መሳሪያን ለመሞከር በሚል በሃዘንና በደስታ ላይ በግዴለሽነት በሚተኮስ ጥይት የንጹሀን ህይወት እየቀጨ እና የህዝባችን የፀጥታ ስጋትና የሃዘን ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ጸጥታ ምክርቤቱ በአንክሮ ተመልክቷል፡፡

ህገ-ወጥነትና ስርዓት አልበኝነት ስር እየሰደደ በመምጣቱ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች በሚያደርጉት ያልተገባ እንቅስቃሴ የክልሉን ልማቶች እያዳከመ፤ የዜጎችን ነጻ እንቅስቃሴ እየገደበ ፤ የኢንቨስትመንት እድሎችን እየዘጋ፣ የተፈጠረውን የስራ ዕድል እያጠፋ፣ ለቀጣይ ልማትም እንቅፋት በመሆንና በአጠቃላይ የአማራን ክልል ልማት በአደገኛ ሁኔታ እየተፈታተነ እንደሚገኝ አጽንኦት ሰጥቶ ተመልክቷል፡፡

እነዚህ ህገ-ወጥ ተግባራት በከተማም ሆነ በገጠር በአጭር ጊዜ ማረም ካልተቻለ የአማራ ክልል ልማት የሚያስቀጥል ሳይሆን የነበረውንም የሚያመክን የህገ-ወጥነትና የስርዓት አልበኝነት መናኸሪያ የሚያደርግ መሆኑን በመረዳት ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል መልክ መያዝ እንዳለባቸው ታምኖበታል፡፡ በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቀለው የሚገኙ ወገኖቻችንም በአግባቡ ምግብ እንዲያገኙ አድርጎ ወደ ቀያቸው ጊዜ መመለስ ካልተቻለ የፀጥታና ሰብአዊ ቀውስ እንደሚያስከትል ፀጥታ ምክርቤቱ ተወያይቶበታል፡፡

ከዚህ አንጻር መንግስት በየደረጃው ህግ የማስከበር ስራውን በጥብቅ በመፈፀም የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ማስከበር አለበት በማለት ህዝቡ በተለያዩ መድረኮች ያነሳቸውን ጥያቄዎች መርምሮ ትክክለኛ ጥያቄ መሆኑን አስምሮበታል፡፡

ስለሆነም የክልሉ ጸጥታ ምክር ቤት የአማራ ክልል ያለበትን የፀጥታ ሁኔታ በጥልቀት በመገምገም የወያኔን ዳግም ወረራ ለመቀልበስና ለመከላከል የውስጥ አንድነትን ማጠናከር፣ ሰላምና ደህንነትን መጠበቅ ቁልፍ ጉዳይ ነው ብሎ ያምናል። ህዝባችን ዳግሞ ለወያኔ ወረራ ለጥቃት እንዳይዳረግ እቅድሚያ ሰጥቶ እንደወትሮው ሁሉ የፀጥታ መዋቅሩ፣ ደጀኑ ህዝብ የራሱን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆን እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በመሆኑም በአንድ በኩል ከፌደራል የጸጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት ከወያኔ የሚሰነዘርብንን ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅና በዝግጁነት መቆም፤ በሌላ በኩል ደግሞ በውስጣችን ለወያኔ ሴራ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩትን ህገ-ወጦችንና ስርዓት አልበኞችን በመቆጣጠር የክልላችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ግንባር ቀደም የትኩረት አቅጣጫ እንዲሆኑ ወስኗል፡፡

ስለሆነም የክልሉ የጸጥታ ምክር ቤት በየደረጃው የጸጥታ ግብረ ሀይል አቋቁሞ ህገ-ወጥነትን ለመቆጣጠርና ህግን ለማስከበር ተገቢ ነው ያላቸውን ህጋዊ ርምጃ እንዲወስድ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በመሆኑም የክልላችን ህዝብ፣ ወጣቶች ፣ የገጠርና የከተማ ኗሪዎች ሰላምና ደህንነታችን ለመጠበቅ እና የውስጥ አንድነታችን ለማጠናከር የፀጥታ መዋቅሩ በሚወስደው እርምጃ ሁሉ ተባባሪ እንድትሆኑ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፀጥታ ምክር ቤት

ግንቦት 5/2014 ዓ.ም
ባህርዳር

@Shewapress
2.5K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 17:37:27 ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
***
ወራሪዉ የትግራይ አሸባሪ መንጋ ኃይል ወልቃይት ጠገዴንና አከባቢውን ከ16 ዓመት ታዳጊ ጀምሮ እስከ 70 ዓመት አዛውንት የሆነ ማንኛውንም ትግራዋይ፤ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብን እንዲወር የክተት አዋጅ አውጇል።

ማንነታችን እንደ ወንጀል ተቆጥሮ የአማራ ተወላጅ የሆነ ሁሉ በየሄደበት እንደ ዶሮ አፍኖ በመሰወር፣ በመግደል፣ አካልን በማጉደል፣ ከሰማይ በታች ከመሬት በላይ አለ የሚባል ግፍ ሁሉ ተፈፅሞብናል። በሺዎች የሚቆጠሩ ታሪክ አዋቂዎች፣ ስለ ህዝብ መብት ተከራካሪ የሆኑትን የሀይማኖት አባቶችን የት እንደደረሱ ሳይታወቅ ደብዛቸው ጠፍቷል።

ስለሆነም በኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል፣ በአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እንዲሁም ሚሊሻና ሌሎች የፀጥታ አካላት ጥምር ተጋድሎ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማህበረሰብ ነፃ ወጥቷል። ይህ የትናንት አኩሪ ገድላችን ነው።

መላው የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ ሆይ!!

ወራሪውና ተስፋፊው የትግራይ ኃይል ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ህልውናህን ሊያጠፋ ቆርጦ ተነስቷል። በመሆኑም በጠላት ዝግጅት መጠን ልክ በተጠንቀቅ እንድትቆም የወቅቱ አስገዳጅ ሁኔታ ሆኗል።

የተከበርከው የአማራ ህዝብ ሆይ!!

በህብረት፣ በአንድነት፣ በፅናት ስለታገልክ የስርዐት ለውጥ አምጥተኃል። ነፃነትም አግኝተኃል። ይሁን እንጂ ድጋሚ ህልውናህን ሊያጠፋ ከመላ ትግራይ የከተተ ወራሪ ኃይል በይፋ ጦርነት አውጆብኃል።

የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!!
የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የትግራይ ተስፋፊ ኃይል ባወጀው ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ገብቷል። ከአሁን በፊት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ስቃዩ ስቃዬ፣ በደሉ በደሌ ነው ብለህ ከፍተኛ ዋጋ ከፍለኃል። ይህን የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ያደንቃል እውቅናም ይሰጣል። ኃብት ማፍራት ይሁን በህይወት መኖር መኖርም አገር ሲኖር ነውና፤ ይህንን አገር አጥፊ ወራሪ ቡድን ለመመከት በምናደርገው ተጋድሎ ከጎናችን እንድትቆም ጥሪያችን እናስተላልፋለን።

ይህንን የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ጥሪ ተቀብያለሁ የሚል ሁሉ የአንድ ወር ስንቅ በማዘጋጀት በየቤቱና በየቀበሌው ሆኖ ለምናቀርበው የፈጥነህ ድረስ ጥሪ ዝግጁ ሆኖ እንዲጠብቅ ሲል ኮሚቴው መልዕክቱን ያስተላልፋል።

''ከአማራነታችን ዝቅ የሚያደርገን ምድራዊ ኃይል የለም!!''

የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ አየለ

@Shewapress
@shewapress
6.0K viewsedited  14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 17:37:23
5.7K views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 16:53:07
"ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ የአይበገሬነት እና የአትንኩኝ ባይነት ተምሳሌቶች ናቸው!

አቶ ደመቀ መኮንን

@Shewapress
@shewapress
6.7K views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ