Get Mystery Box with random crypto!

VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ shewapress — VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹 V
የቴሌግራም ቻናል አርማ shewapress — VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @shewapress
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.05K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ፈጣን እና እውነተኛ መረጃወች ይተላለፉበታል።
መረጃ ፣ ሀሳብ ፣ አስተያዬት ለመስጠት @melkah
የyoutube አድራሻች👉👉
https://youtube.com/channel/UC05y0-96PuPy2yRN0Sk4a3A

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 91

2022-05-19 13:46:35
#መረጃ

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድም ወረዳ ጀብውሃ በሚገኙ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ላይ ከበባ በማድረግ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጥቃት ፈጽሟል።

ግንቦት 10/2014 በተፈጸመው ጥቃት አንድ የልዩ ኃይል አባል በመቁሰሉ ቁስለኛውን ይዘው በፓትሮ ወደ ሸዋሮቢት ሲጓዙ ተጨማሪ የደፈጣ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።

በጥቃቱም የሶስት የልዩ ኃይል አባላት ህይወት አልፏል፤ መኪናውም በመገልበጡ የቆሰሉም እንዳሉ መረጃወች ደርሰውናል።

የክልሉ መንግስትም የአማራ ጠላትንና ለህዝባችን ስጋት የሚሆኑትን መንጥሮ ከማስወገድ ይልቅ የ አማራ ህዝብ ጠባቂ የሆኑትን ፋኖወችን ማፈኑን እና ማዋከቡን ተያይዞታል።

@shewapress
@Shewapress
11.3K viewsedited  10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 11:32:23
#መረጃ

ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ቀጥሏል

ማዕከላዊ ጎንደር አለፋ ጣቁሳ ደልጊ ከተማ ላይም ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት የሄደው አፋኝ ቡድን እና በአማራ ፋኖ አባላት መካከል ተኩስ ተከፍቷል።

እስካሁን ባለው የተኩስ ልውውጥ በአፋኙ ቡድን በኩል ሁለት(2) ሰዎች የተመቱ ሲሆን አንድ ሰው ቆስሏል። በፋኖዎች በኩል የደረሰ ጉዳት የለም!

የአማራ ልዩ ሀይል አባላት አብሮን ምሽግ የከረመውን ፋኖን አንመታም በማለት አድማ እያደረጉ ነው። በአድማብተናውም ውስጥም በዚሁ ምክንያት ከፍተኛ ውጥረት መፈጠሩን መረጃወች ደርሰውናል።

@shewapress
11.6K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 10:01:40
ሞጣ ጀግናየን አላሳፍንም ብላለች

ዛሬ ረፋድ ሞጣ ላይ አንድ የፋኖ አለቃን የብአዴን ሰዎች በግዳጅ አፍነው ሊወስዱት ሲሞክሩ በተነሳ ግርግር የሞጣ ከተማ ነዋሪ ሊታፈን የነበረውን የፋኖ አለቃ በማስለቀቅ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን እያሰማ ይገኛል።

ይሄ ነው የሚያስፈልገው ሁልህም አማራ ጀግናህን ለ አፋኙ ማፊያ ቡድን አሳልፈህ እንዳትሰጥ ወጥር

@shewapress
@Shewapress
12.0K views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 08:50:28 የጀነራል ተፈራ ማሞ ባለቤት ወ/ሮ መነን ስለ ባለቤታቸው የተናገሩት።

ሊንኩን ተጭነው ያድምጡት #subscribe ማድረግ አይርሱ

Watch "የጀነራል ተፈራ ማሞ ባለቤት ወ/ሮ መነን ሀይሌ ስለ ባለቤታቸው ከራሷ አንደበት የተናገረችው።" on YouTube


11.9K views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 08:08:01
#መረጃ

የአማራ ፋኖ በደቡብ ወሎ የፋይናነስ ኃላፊ የሆነው ፋኖ አማረ ወርቄ ከምሽቱ 4:30 ላይ ታፍኖ ተወስዷል።

የአማራ ፋኖ በደቡብ ወሎ የፋይናንስ ሀላፊ የሆነው ፋኖ አማረ ወርቄ በቀን 10/9/14አ.ም በደሴ ከተማ ከምሽቱ 4 :30 ላይ ባልታወቁ ሀይሎች ታፍኖ ተወስዷል።በዛሬው እለት ምክትል ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዘላለም ጫኔና ሌሎች 3 አባሎቻችን መታሰራቸውን ዘግበን ነበር።

አማራ ጀግኖችህ በየተራ እየታፈኑ ነው ታዳ ምን ትጠብቃለህ???

@shewapress
12.3K viewsedited  05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 20:15:02
የጀነራል ተፈራ ማሞ ባለቤት ባለቤታቸው በባህርዳር እንደሚገኙ እና ደህና መሆናቸውን መልዕክት እንደደረሳቸው ለ BBC ተናግረዋል።

@shewapress
@Shewapress
7.1K viewsedited  17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 19:43:10
ጀነራል ተፈራ ማሞን አፋኙ የብልፅግና መንግስት በአዲሰ አበባ አፍኖ ወደ ባ/ዳር ከተማ ለሚገኘው ብአደን አስተላልፈው መስጠታቸው መረጃወች ደርሰውናል።

የመረጃ ምንጮቻችን እንደገለፁልን አሁን ጀነራል ተፈራ ማሞ በ ባህርዳር 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ ገልፀውልናል።

@shewapresa
7.8K viewsedited  16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 17:47:07 በአማራ ልሂቃን ላይ መንግሥታዊ እገታ በመፈጸም የሚቆም ጥያቄም ሆነ የሚጸና ሥልጣን የለም!

(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በአማራ ክልል ምክር ቤት ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ተወካይ አባላት የተሰጠ መግለጫ፤)
*
የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በተለይም በአማራ ሕዝብ ላይ በሚፈጸሙ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች፣ ጅምላ ጭፍጨፋዎች እና መፈናቀሎችን በዘላቂነት በማስቆም መንግሥታዊ ሚናውን እንዲወጣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እንደ ድርጅትና በልዩ ልዩ ምክር ቤቶች ሕዝብ ‘ተናገር በከንፈሬ’ ብሎ የላካቸው ተወካዮቹ ሲወተውቱ መክረማቸው ይታወቃል። ይሁን እንጂ የአማራ ተወላጆች በግሬደር ሲቀበሩ፣ ከተሞች ሲወድሙ ጭምር የመንግሥትነት መሠረታዊ ሥራዎችን ማለትም የዜጎችን ደኅንነት ማስጠበቅ፣ ሕግና ሥርዐትን ማንበርና የተሳለጠ አመራር መስጠት ያልቻለው መንግሥት ሕዝባችን በኅልውና አደጋ ላይ በወደቀበት በአሁኑ ጊዜ በአማራ ሊቃን ማለትም በአብን አባላትና አመራሮች፣ በፋኖ አባላትና አገራቸውንና ሕዝባቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያገለገሉ የጦር መኮንኖችን ማንነትን መሠረት ባደረገ መልኩ የአፈና፣ የሕገ-ወጥ እስራት እና የመንግሥታዊ እገታ ሥራዎች ላይ መጠመዱ በአማራ ክልል ምክር ቤት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ተወካይ አባላትን አሳዝኖናል።

ይህ መንግሥታዊ የእገታና የአፈሳ ዘመቻ ‘ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ፤ ከአማራ ጋር ሒሳብ አወራርዳለሁ’ ብሎ በዕብሪት አገሪቱን እያመሰ ያለው ትሕነግ የጦር ነጋሪት በሚጎስምበት፣ ከፊል የአማራ ሕዝብ በዚህ ዕቡይ የሽብር ቡድን መዳፍ ውስጥ ሆኖ በሚሰቃይበትና መላው የአማራ ሕዝብ ከወንድሞቹ ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድነት ቆሞ አሸባሪውን መመከት በሚገባው ወቅት መሆኑ ደግሞ የመንግሥታዊ አፈናው ዓላማ ሕዝብን ለዳግም ጥቃት የማመቻቸት እና ከሽብር ቡድኑ ትሕነግ ጋር እንደመተባበር የሚቆጠር ነው።
በመሆኑም እኛ በአማራ ክልል ምክር ቤት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ተወካይ አባላት በጉዳዩ አሳሳቢነት ላይ ከተወያየን በኋላ የሚከተሉትን አቋሞች ወስደናል፤

፩. በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላት ላይ እየተደረገ ያለው የአፈና እና እስራት ዘመቻ እንዲቆም፣ የታሰሩትም በአስቸኳይ ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን። አብን ሕጋዊና ሰላማዊ ፓርቲ ሲሆን በፓርቲው ውስጣዊ ጉዳዮች ምክንያት የሃሳብ ልዩነት የያዙ አባላት እና አመራሮች ላይ የሚደረገው ወከባ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ መንግሥት ከመሰል ተግባራት እንዲቆጠብ እንጠይቃለን። በአንድም በሌላም መልኩ ለዚህ ሕገ-ወጥ እስራትና መንግሥታዊ እገታ ተባባሪ የሆኑ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና የሃሳብ ልዩነቱን በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እናሳስባለን።

፪. በፋኖ አባላት፣ በሕጋዊ ታጣቂዎችና ወጣቶች ላይ እየተደረገ ያለው አፈና፣ እስራት፣ ትጥቅ ማስወረድና መንግሥታዊ እገታ በአስቸኳይ እንዲቆም እና በዚህ ሕገ-ወጥ ዘመቻና መንግሥታዊ እገታ የታፈኑና የታሰሩ ዜጎች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን።

፫. አገራቸውንና ሕዝባቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያገለገሉ የጦር መኮንኖችንና የፀጥታ አመራሮች ላይ የሚፈጸመው መንግሥታዊ እገታና ስወራ በአስቸኳይ እንዲቆምና በዚህ ሰበብ በማንነታቸው ብቻ የታገቱ የጦር መኮንኖችንና የፀጥታ አመራሮች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን።

፬. ሕግ ማስከበርን ሰበብ በማድረግ የፌዴራል የፀጥታ መዋቅር በሕገ መንግሥቱ ለክልልና ለፌዴራል ተለይቶ የተሰጠውን ኃላፊነት እና ሚና በማፋለስ ክልሉን በሕገ-ወጥ መንገድ ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆም በአጽንኦት እንጠይቃለን።

፭. የአማራ ክልል መንግሥት በፌዴራል መንግሥቱ ለሚፈጸመው መንግሥታዊ እገታና ስወራ ተባባሪ ከመሆን ወጥቶ የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት እንዲያስከብር እየጠየቅን ጉዳዮቹን በሰላማዊ መንገድ በውይይት እንዲፈታ ጥሪ እናቀርባለን።

፮. መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአማራ ሊቃን ላይ የሚደረገውን መንግሥታዊ እገታና አፈና እንዲቃወምና ከአማራ ሕዝብ ጎን እንዲቆም እየጠየቅን ልዩ ልዩ የአማራ አደረጃጀቶች፣ ወጣቶች፣ ምሁራንና መላው ሕዝባችን የተጋረጠብንን የኅልውና አደጋ እና ከበባ ለመቀልበስ በአንድነት እንድትቆሙና በጋራ ጭቆናን በመቃወም ልጆቻችሁን እንድትጠብቁ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፥ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!

ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም
ባሕር ዳር፣ አማራ፥ ኢትዮጵያ

@Shewapress
@Shewapress
9.6K viewsedited  14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 17:47:05
9.1K views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 07:00:18
#መረጃ

በሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረማሪያም ከሰም ወረዳ ሾላገበያ 01 ቀበሌ የፋኖን አሰልጣኝ ጥላሁን ካሳን መታፈን ተከትሎ ተቃውሞ ቀሰቀሰ

በሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረማሪያም ከሰም ወረዳ ሾላገበያ 01 ቀበሌ የፋኖን አሰልጣኝ ጥላሁን ካሳን በአፋኙ የብልፅግና መንግስት አፍኖ መውሰዱን ተከትሎ በአካባቢው ነዋሪ ህዝባዊ ተቃውሞ በማድረግ ጥላሁን ካሳን ለማስፈታት ሲሞክር በሕዝቡ ላይ ጥይት በመተኮስ ዋና አሰልጣኙ በጥይት ተመቶ ደ/ብርሃን ሪ/ሆስፒታል ይገኛል። በሌላ በኩል ፋኖ ዘውዱ የተባለው ህይወቱ አልፏል።

@shewapress
@Shewapress
13.2K viewsedited  04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ