Get Mystery Box with random crypto!

VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ shewapress — VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹 V
የቴሌግራም ቻናል አርማ shewapress — VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @shewapress
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.05K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ፈጣን እና እውነተኛ መረጃወች ይተላለፉበታል።
መረጃ ፣ ሀሳብ ፣ አስተያዬት ለመስጠት @melkah
የyoutube አድራሻች👉👉
https://youtube.com/channel/UC05y0-96PuPy2yRN0Sk4a3A

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 92

2022-05-17 20:44:20
የጀነራል ተፈራ ማሞ ባለቤት ወ/ሮ መነን ለኢሳት ከተናገሩት።

@shewapress
14.5K viewsedited  17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 20:04:12
የጄኔራል ተፈራ ማሞ ምክትል የነበሩትና በጦርነቱ ወቅት በርካታ መስዋዕትነት የከፈሉት ኮማንደር ቢሰጥ ጌታሁን በ አፋኒው የብልፅግና መንግስት ታፍነው ተወስደዋል።

@shewapress
@Shewapress
13.7K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 13:37:33
#መረጃ

ወሎ ሲወረር ከቤተሰቡ ጋር የፈረጠጠው የደሴና የኮምቦልቻ ከተማ አመራር ፋኖን እንዴት እናጥፋው በሚል ሕዝብን ለማወያየት ሞክሮ ከባድ ተቃውሞ አጋጥሞት ተበትኗል።

@shewapress
@Shewapresa
14.8K viewsedited  10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 13:33:04
ፋኖ ግርማ መንግሥቱን ዛሬ ረፉዱ ላይ አስረውታል። ለምን እንደታሰረ ተቋቋመ የተባለው ኮማንድ ፖስት ብቻ ነው የሚያውቀው። ጀኔራል ተፈራ ማሞ ታፍኖ ተወስዷል። ማን እንደያዛቸው እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም። የምኒልክ ብርጌድ አዛዥ ፋኖ አተነህ ድረስ፣ ፋኖ ሰለሞን አባተ (በጦርነቱ የቆሰለ)፣ ፋኖ ጌታቸው ሙጩ እና አሸናፊ አካሉ (ከዚህ በፊት ታስሮ ቶርቸር የተደረገ) ከታሰሩት መካከል ይገኙበታል። በጣም የሚያስገርመው ሰሞኑን በተካሄደው ሽልማት የታሰሩም አሉ። በጦርነቱ የቆሰሉ ሁሉ ታስረዋል። እንዲህ ያለ የጅምላ አፈሳ ምን አይነት መፍትሔ እንደሚያመጣ አላውቅም።
Tadele Tibebu

@Shewapress
@Shewapress
14.3K views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 12:30:46 ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ አዲስ አበባ ውስጥ ከቤታቸው እንደወጡ አለመመለሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ገለፁ።

ወ/ሮ መነን ስለ ባለቤታቸው ሲናገሩ ትናንት ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው 5፡15 አካባቢ የወጡት ከጓደኛቸው ጋር ቀጠሮ እንደነበራቸው ለቢቢሲ አማርኛ ገልፀዋል።

ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤታቸው ባለመመለሳቸው ደጋግመው ወደ ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ቢደውሉም ምላሽ አለማግኘታቸውን ይናገራሉ።

ጄኔራል ተፈራ ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም በቅርቡ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው መስራታቸው ይታወሳል ።

እንደ ወ/ሮ መነን ገለፃ ከሆነ ጄኔራል ተፈራ ያገኟቸው ሰዎች በዕለቱ አስከ 10 ሰዓት ድረስ አብረው መቆየታቸውን እና ከዚያ በኋላ እንደተለያዩ ነግረዋቸዋል።

ከዚያ በኋላ ግን የደረሱበትን ለማወቅ እንዳልቻሉ ባለቤታቸው ተናግረዋል

ጄኔራል ተፈራ ሞሞ ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥነት ከተነሱ በኋላ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ በመቅረብ አስተያየታቸውን ይሰጡ ነበር።

ወ/ሮ መነን የባለቤታቸውን መጥፋት አስመልክቶ ወደ ፌደራል ወንጀል ምርመራ እንዲሁም አዲስ አበባ ፖሊስ በመሄድ ቢጠይቁም ግለሰቡ "በቁጥጥራቸው ስር እንደማይገኝ" እንደገለፁላቸው ይናገራሉ።

በአሁኑ ሰዓትም ባለቤታቸውን ለማግኘት ሊኖሩበት ይችላሉ ወደተባሉ የተለያዩ የደኅንነትና የፀጥታ ተቋማት በመሄድ ፍለጋቸውን መቀጠላቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

ጄኔራል ተፈራ ማሞ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ናቸው።

ጄኔራል ተፈራ የስኳር ሕመምተኛ መሆናቸውን የገለፁት ባለቤታቸው የታዘላቸውን መድኃኒት እየወሰዱ አንደነበር አመልክተው፣ መድኃኒታቸውን ካልወሰዱ አንደሚታመሙ በመጥቀስ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ባለቤታቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከሚኖሩበት ባሕርዳር ወደ አዲስ አበባ የመጡት በእግራቸው ውስጥ የሚገኙትን ጥይቶች በተመለከተ የሕክምና ክትትል ለማድረግ እንደነበረም ጨምረው አስረድተዋል።

"እስሩን ለምዶታል ያለፈበትም ነው፤ የሚያሳስበን ጤናው ሁኔታ ነው" ብለዋል።

የጄነራሉን መሰወር በተመለከተ የፌደራልም ሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስካሁን ያሉት ነገር የለም።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባል ሆነው ለዓመታት በከፍተኛ መኮንንነት ያገለገሉት ብርጋዲዬር ጄነራል ተፈራ ማሞ ከአስር ዓመት በፊት መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ አሲረዋል በሚል ከሌሎች ጋር ተከሰው ለዓመታት በአስር ላይ ቆይተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎም ከእስር ተለቀው በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

በቅርቡም የህወሓት ኃይሎች ወደ አማራና አፋር ክልሎች በመግባት ጥቃት በሰነዘሩበት ጊዜ የክልሉን ልዩ ኃይል በበላይነት ሲመሩ የነበሩ ሲሆን፣ ከጥቂት ወራት በፊት ደግሞ ከዚሁ ኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጋቸው ይታወሳል

BBC Amharic

@Shewapress
@Shewapress
13.3K views09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 10:19:41
~ብ/ጀ ተፈራ ማሞ በጭንቅ ወቅት "ና አግዘን" ሲባል ሰተት ብሎ የገባ ባለውለታ ነው!

~ወታደራዊ መኮንኖች ከትህነግ ገንዘብ እንደገባላቸው መንግስትም አምኗል። ጄ/ል ተፈራ ከእነዛ መኮንኖች በተቃራኒ ነው። አንዳንዶች ድልን በገንዘብ ሲሸጡ ተፈራ ማሞ ሽንፈትን በሕይወቱ ለመለወጥ ከተራ ወታደሩ ጋር የከረመ ጀግና ነው። የአሸባሪው ተላላኪዎች "በ50 ሜትር ርቀት ውስጥ ነበር" እያሉ ሲናገሩ የሰማነው ነው።

~የፌደራል ባለስልጣናት ከመከላከያ መኮንኖች ያልተናነሰ ለተፈራ ሲደውሉ መክረማቸውን የማይሰማ ከመሰላቸው ተሳስተዋል። ግንባር ላይ ስለከረመ ነው።

~ ተፈራ እንደ ድፍረቱ ግልፅ ነው። የነበረውን ይናገራል። እጅግ የሚያሳዝነው ጦርነት የቀለበሰው ጀግናው ተፈራ የታፈነው ጦርነቱን ያስጀመሩት የትህነግ ፖለቲከኞችና ወታደራዊ አዛዦችን በፈታ ኃይል መሆኑ ነው።


ተፈራ ትህነግ የሚቆጣጠረው ከተማ ውስጥ ቢታፈን አያስገርምም። ተፈራ የታፈነው አዲስ አበባ ላይ። አሸባሪው ሊይዛት ሲያሰፈስፍ ተፈራ ወሎና ሸዋ ላይ ታግሎ ያተረፋት ከተማ ውስጥ ነው የታፈነው። ይህን የሚያደርጉት ሌላ መገለጫ የላቸውም። ከአሸባሪው ህወሃት ጋር የጋራ አላማ ያላቸው ካልሆኑ በስተቀር።

Getachew shiferaw

@Shewapress
@Shewapress
12.7K views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 09:46:16 የዜጎች እስር፣ እገታና መሰወር እጅግ አሳሳቢና በአስቸኳይ መቆም ያለበት ድርጊት ነው! ጀነራል ተፈራ ማሞን ጨምሮ በየአካባቢው የታፈኑና የታሰሩ የፋኖ አባላት በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አደርጋለሁ!
(ዶር ደሳለኝ ጫኔ)


ገዢው መንግስት በፓርቲ ሰነዶቹ ላይ በግልጽ እንዳመላከተው ፋኖን ኢ—መደበኛ ኃይል ነው በሚል ፍረጃ ርምጃ እንደሚወስድበት ገልጾ ነበር።

የፋኖን አደረጃጀትና መጠናከር አስፈላጊ ያደረገው ጉዳይ ግልጽ ነበር። ትሕነግ መሩ የትግሬ ወረሪ ኃይል የአማራ ክልልን ወርሮ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎችን ሲገድል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶችን በጅምላ ሲደፍርና ከ300 ቢሊየን ብር በላይ የሚደርስ ሀብት ንብረት ሲያወድም የፌደራል መንግስቱም ሆነ የአማራ ክልል መንግስት ይህን አውዳሚ የሽብርና የዘረፋ ሀይል ማስቆም የሚችሉበት ቁመና ላይ አልነበሩም።
የአማራ ወጣቶች በህዝባቸው ላይ የደረሰውን ይሄንን አስከፊ ጥቃት በአይናቸው አይተዋል፣ በደረሰው ነገርም ክፉኛ ተቆጥተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ወረራው አድማሱን ሲያሰፋ መንግስት የትግሬን ወራሪና አውዳሚ መንጋ በመደበኛው የመንግስት የመከላከያና የፀጽታ መዋቅርና አደረጃጀት ማስቆም ስለማይቻል ዜጎች ያላቸውን ትጥቅ ታጥቀው፣ ስንቃቸውን ሰንቀው ወደ ግንባር እንዲዘምቱና ጠላትን እንዲደመስሱ፣ እንዲሁም በምርኮ ያገኙትን መሳሪያ እንዲታጠቁ ጥሪ ማቅረቡም ይታወቃል።
እነዚህ ሁለት የህይዎት ተሞክሮዎች ወይም ገጠመኞች የአማራን ወጣት አስተምረውታል፣ በበጎም ለውጠውታልም።

በርካታ የአማራ ወጣት ወደ መከላከያና ልዩ ኃይል እንዲቀላቀል ከማድረጉም በላይ በየአካባቢው ወታደራዊ ስልጠናዎችን የሚሰጡ የፋኖ አደረጃጀቶችን እንዲያማትር፣ መሳሪያ የመታጠቅና ወደፊት ለሚያጋጥሙ የትግሬ ወረራ ስጋቶች ራሱን እንዲያዘጋጅ ገፊ ምክንያት ሆኖታል።

አሁንም የትህነግ መራሹ የትግሬ ወራሪ ሀይል ለዳግም ወረራ የጦርነት ነጋሪት እየመታ ባለበት በዚህ ወቅት በህግ ማስከበር ስም የፋኖ አባላትንም ሆነ ትጥቅ ያላቸውን ዜጎች በጅምላ ማሰርና ማዋከብ፣ እንዲሁም የማገትና መሰወር ወንጀል በአስቸኳይ ሊታረም የሚገባው የለየለት መንግስታዊ ውንብድና ነው። ከዚህ ባለፈም ክልሉ አሁን ካለበት የፀጽታና የደህንነት ስጋት ላይ በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንደሚሆንና ይብሱን ወደ አለመረጋጋት እንዳይመራው ስጋት አለኝ። ጉዳዩ ስሱና በጥንቃቄ ሊታይ የሚገባው ነው።

በርግጥ ከፋኖ አደረጃጀት ጋር ተያይዞ መቀረፍ ያለበቸው የእዝ ጠገግና ሰንሰለት፣ የተጠያቂነትና ውጤታማ ቁጥጥር እንዲሁም ከመደበኛው የህግ ማስከበር መዋቅር ጋር ያለው መስተጋብርና ትስስር መፍትሄ ሊፈለግለት የሚገባው ጉዳይ ነው።

ፋኖ ከመንግስት የፀጥታ መዋቅር የጎንዮሽ ወይም እሱን የሚተካ እንዳልሆነና በመደበኛና የእለት ከእለት የህግ ማስከበር ውስጥ ምንም ድርሻ የሌለው፤ ይልቁንም አገርና ህዝብ የደህንነት ችግር ውስጥ ሲወድቁ የራሱን መሳሪያ ታጥቆ ከጠላት ጋር የሚፋለም ሀይል መሆኑን ሰፊ የግንዛቤና የተግባቦት ስራ እንደሚጠይቅ ግልጽ ነው።

በአጠቃላይ አሜሪካን ጨምሮ በየትኛውም አለም ዘመናዊ ዴሞክራሲዎች መግባባት ላይ እንደተደረሰበትና በአለም አቀፍ ደረጃም ተቀባይነት ወደ ማግኜት የደረሰው እሳቤ ጤናቸው የተረጋገጠና የኋላ ታሪክ ምርመራ ያለፉ ዜጎች የተመዘገበ መሳሪያ ታጥቀው ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን፣ ሀብትና ንብረታቸውን እንዲሁም አገርና ህዝባቸውን ጭምር የመጠበቅ መብት አላቸው። አሜሪካውያን second amendement right; the right to bear arms ይሉታል።

መሳሪያ የመያዝ መብት ከመሰረታዊ የሰው ልጆች በህይዎት የመኖር መብት እና ሰርቶ ሀብት አፍርቶ ከመጠቀም እንዲሁም ከነፃነት መብት ጋር በከፍተኛ ሁኔታ የሚተሳሰር እና ሊከበር ወይም ጥበቃ ሊሰጠው የሚገባ መብት ነው። ቁጥጥር ያስፈልገዋል፤ ቁጥጥሩም ሲሰራ ከዜጎች ጋር በቂ ውይይት ተደርጎበትና ማህበረሰቡን ተሳታፊ ባደረገ መንገድ እንጅ ህዝቡ የጠላት ወረራ ቋፍ ላይ ባለበት ወቅት አይመስለኝም።

ጀነራል ተፈራ ማሞና አሸናፊ አካሉ እንዲሁም ሌሎች በዚህ ሰሞን የታሰሩ ፋኖዎች በአስቸኳይ ይፈቱ፣ ችግሮች ካሉም በምክክር ይፈቱ!

@Shewapress
@Shewapress
12.1K viewsedited  06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 09:46:14
11.3K views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 08:32:49 ጀነራል ተፈራ ማሞ ሽልማት እንጅ በፍፁም ካቴና አይገባውም።

ጀነራል ተፈራ ማሞ በጦርነቱ ወቅት ስለፈፀሙት ጀግንነት እና ክህደት ስለፈፀሙት አንዳድ ጀነራሎች የተናገሩት አዳምጡት።

Watch "ጀነራል ተፈራ ማሞ የ አንዳድ የመከላከያ ጀነራሎች እና መኮንኖችን ጉድ አጋለጡ።" on YouTube


11.6K views05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 08:17:14 ከአማራ ፋኖ በባህርዳር የተሰጠ

አስቸኳይ መግለጫ

አርበኝነት ዉርሳችን ሲሆን ታሪካዊነት ደግሞ ትርፋችን ነዉ!!!

እንደሚታወቀዉ የአማራ ህዝብ ማህበራዊ እረፍቱን ማጣት ከጀመረ በርካታ ዓመታት ተቆጥሯል ፤ባለፉት ሶስት አመታት ግን መንግስት መር ጭፍጨፋዎች፤ ግድያዎችና ዉድመቶች በአማራ ህዝብ ላይ በሰፊዉ ተባብሰዉ ቀጥለዋል፡፡ በመሆኑም ባለፉት ሶስት ዓመታት ብቻ ሚሊዮን አማራዎች ለስደት፣ ረሃብና መፈናቀል ሲጋለጡ፤ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ደግሞ መንግስት መር በሆነ የዘር ጭፍጨፋ እንዲያልቁ ተደርገዋል፡፡ በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉ ደግሞ ሰሜን ክፍሉን ‹የተራዘመ ጦርነት ዉስጥ እንዲከርም› በማድረግ የአማራ ህዝብ በቁጥር ለመግለፅ በሚያስቸግር አሃዝ ብዙ ንብረት ሲወድምበት፤ ሃብትና ንብረቱን ከማጣትም በላይ ዉድ ልጆችን ሲሰዋ ከርሟል፡፡ ፋኖ የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ የህልዉና አጣብቂኝ ዉስጥ ሲገባ፤ እንደ ክልል ደግሞ የመፈራረስ እድል ሲገጥመዉ ስንቁን ከቤቱ ትጥቁን ከአያቱ ይዞ በመዝመት የአማራ ህዝብን አለኝታነት ያረጋገጠ ባህላዊ ሰራዊት ነዉ፡፡ ይህ ሃይል በደህና ጊዜ አራሽ፤ በችግር ጊዜ ደግሞ ፈጥኖ ደራሽ ትዉፊቱን ሲያስቀጥል በተለያዩ አዉደ ዉጊያዎችና ምሽግ ሰበራዎች በመሳተፍ ጭምር እንጅ ጭንቅ ቀን ሲመጣ ሀብት መዝብሮ የሚሮጥ ስብስብ አልነበረም፡፡ የአማራ ፋኖ በባህርዳር በአርቢት-ጋሸና ግንባር ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ እስከሞት ድረስ በታመኑ የህዝብ ልጆች ላይ ማለትም ‹‹ፋኖ ጌታቸዉ ሙጩ›› እና ‹‹ፋኖ ሰለሞን አባተ›› ላይ የእስራት ሁኔታ ሲገጥማቸዉ በሌሎች በርካታ አባላቶቹ ላይ ደግሞ የወከባ፤ ሽብርና ከበባ ሁኔታን እያስተናገዱ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም የአማራ ፋኖ በባህርዳር በወከባ፤ እስር፤ ከበባና እንግልት ዉስጥ ሁኖም ከዚህ በታች ያሉትን አቋም ለአካባቢያችን፤ አማራና ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብ ለማሳወቅ ይገደዳል፡፡

1ኛ). ከበጌምድር ወንድሞቻችን ‹የወልቃይት አስመላሽ ኮሚቴ› የተላከልንን የዝግጅት ትዕዛዝ ለማስተጎጎል የተሸረበ ሴራ መሆኑን ስለምንረዳ እኛ ላይ እየተደረገ ያለዉ ደም አፋሳሽ ሂደት በአስቸኳይ ወደ ሰገባዉ እንዲመለስ ስንል ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

2ኛ). ነገሮቹን የምናይበት የትዕግስት መነፅር እንደ ፍርሃት የሚቆጠር ሁኖ ራስን ወደመከላከል አጠፋ ስንገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መዲናዋ ባህርዳር ለሚፈጠርባት ትርምስ፤ ሁከትና ብጥብጥ ‹መንግስትና መንግስት መሩ የአፈና ቡድን› ሃላፊነቱን ይወስዳል፡፡

3ኛ). የሐይማኖት አባቶች፤ የሃገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ነገ ይህ ለምን ተፈጠረ ብሎ ሙሾ አዉራጅነትና የሚዲያ ጋጋታን ከማስከተላቹህ በፊት ‹መንግስትንና መንግሰት መሩ የአፈና ቡድኑን› ተዉ ብላቹህ ትገስፁ ዘንድ እናሳስባለን፡፡

4ኛ). ፋኖ ላይ የሚደረጉ መጠነሰፊ እንግልቶች ባሉበት ሳይገቱ ከቀጠሉና የታሰሩብን አባሎቻችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የማይፈቱ ከሆነ ፋኖ ለሚዎስደዉ የአመፅ፤ ሰልፍ፤ ህዝባዊ እምቢተኝነትና አድማ (እንደ አስፈላጊነቱ እያደገ የሚሄድ) እንቅስቃሴዎች መንግስት ሃላፊነቱን ሙሉ ለሙሉ ይወስዳል፡፡

5ኛ). የአማራ ፋኖ በባህርዳር የአማራ ክልል ዋና ከተማ ላይ እንደመቀመጡ መጠን ለዘርፈ ብዙ ጥቃትና እንግልት ተጋላጭ በመሆናችን ራሳችንን ለመከላከል በምናደርገዉ ተጋድሎ በሁሉም አካባቢ ማለትም በአማራ ነባር አፅመ ርስቶች ሸዋ፤ ወሎ፤ ጎንደርና ጎጃም ያሉ የፋኖ አደረጃጀቶች እዉቅናዉ እንዲኖራቹህና ከአያቶቻችን በወረስነዉ የመተጋገዝ መንፈስ እንድነታችንን እንድናጠናክር ስንል ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
አርበኝነት ዉርሳችን ሲሆን ታሪካዊነት ደግሞ ትርፋችን ነዉ!!!
የአማራ ፋኖ በባህር ዳር
ግንቦት 09/2014 ዓ.ም
ባህር ዳር

@shewapress
@shewapress
12.5K views05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ