Get Mystery Box with random crypto!

ከሸዋ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ ፋኖን በማሳደድ እና የተለያዩ አፈናዎችን ለማድረግ በመሞከር የአማራ | VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹

ከሸዋ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ

ፋኖን በማሳደድ እና የተለያዩ አፈናዎችን ለማድረግ በመሞከር የአማራ ህዝብን ጥያቄ ማስቆም አይቻልም

የአማራው ህዝብ ከምን ጊዜውም በላይ አንድነቱን አስጠንቆ የተቃጣበትን የህልውና አደጋ መቀልበስ በሚያስፈልግበት ሰዓት ፋኖን እና የአማራን ምሁራንን፣የማህበረሰብ አንቂወችንና የተቀዋሚ ፓርቲ አመራሮችን በማፈን እና ለማፈን ሙከራ ማድረጉ እጅግ በጣም ዋጋ የሚያስከፍል ተግባር መሆኑን አዉቃችሁ ይህንን ተግባር በአስቸኳይ እንዲትቆሙ እናሳስባለን!!

በተለይ በዛሬዉ እለት በነጻነት ታጋዩ አርበኛ ዘመነ ካሴ ላይ እየተደረገ ያለውን ከበባ ባስቸኳይ እንዲቆም እናሳስባለን!
አማራ ባራቱም አቅጣጫ ተከቦ የጦር ነጋሪት እየተጎሰመበት ባለበት ሰዓት የአማራ አፈና ማከናወን የህዝባችንን ልዕልና መጋፋት እና ከጠላት ጋር ማበር መሆኑ ታውቆ የመንግስት የጸጥታ አካላት ነኛ ባዮች ባስቸኳይ ከዚህ ድርጊታችሁ ታቅባችሁ ያፋናችኋቸውን የአማራ ልጆች ባስቸኳይ እንድትለቁ ስንል እናሳስባለን።

ያ ሳይሆን ቀርቶ በማናለብኝነት ለሚደረግ ማንኛው የጸረ ሰላም እንቅስቃሴ የሸዋ ፋኖ በተለያዩ የአማራ ግዛቶች ከሚገኙ የትግል አጋሮቹ ጋር በመሆን ምላሽ የሚሰጥ መሆኑ ታውቆ በዚህ ሂደት ውስጥ ለሚፈጠር ነገር ሙሉ ሃላፊነቱን መንግስት ይወስዳል!!!

ድል ለተገፋው እና ጭቁኑ ህዝብ!!!
ሸዋ ፋኖ ግንቦት 12/2014

@shewapress