Get Mystery Box with random crypto!

QesemAcademy

የቴሌግራም ቻናል አርማ qesemacademy — QesemAcademy Q
የቴሌግራም ቻናል አርማ qesemacademy — QesemAcademy
የሰርጥ አድራሻ: @qesemacademy
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19
የሰርጥ መግለጫ

💡ቀሰም Academy ከHigh school እስከ Campus ለሚማሩ ተማሪዎች ፤ ቲቶሪያሎችን ፣ጠቃሚ የንባብ ስልቶችን ፤Soft Copy የሆኑ አጋዥ የንባብ ማቴሪያሎችን ፣ትምህርታዊ መረጃዎችን እና አነቃቂ መልዕክቶችን በማዘጋጀት ለተማሪዎች ንቃት የሚተጋ ቻናል ነው!
Are u advertiser ?Contact us : @QesemADs_Bot
Addis Ababa, Ethiopia

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-01-13 20:55:00 ገራሚ የፊልም ቻናል
988 viewsᴅᴀɢɪᴍ , 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 20:24:18
የ12ኛ ክፍል ዉጤት እንደተለቀቀ የምታዩበት ህጋዊ የትምህርት ሚኒስቴር ቻናልን ይቀላቀላሉ

ትምህርት ሚኒስትር

https://t.me/+bsPn7ZSkOw1kNjk0
https://t.me/+bsPn7ZSkOw1kNjk0
1.1K viewsᴅᴀɢɪᴍ , 17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 18:17:36
እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ።



ልዩ ቅናሽ የገናን በዓልን በማስመልከት

ኦሪጅናል ኤርፖድ መግዛት ለፈለጋችሁ ሁሉ !

1000ብር   600 ብር ብቻ

     አምስት ቀን ሚቆይ ቻርጀር
      Touch ሴንሰር ያለዉ
       packed


ያመጣነዉ ለጊዜዉ  3 ደርዘን(36 ፍሬ) ብቻ ስለሆነ ቶሎ በመዉሰድ ራሶትን ከነዛ እድለኞች አንዱ ያድርጉ።

ማሳሰቢያ፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
      -4 ኪሎ ካምፓስ
      -5 ኪሎ ካምፓስ ወይም
      -6 ኪሎ ካምፓስ  መቶ መቀበል ለሚችል ብቻ።

መግዛት የፈለጋችሁ ተማሪዎች ከታች በተቀመጠዉ የቴሌግራም አድራሻ ዉስጥ በመግባት ስልክ ቁጥራችሁን እና የትኛዉ ካምፓስ እንደምትገኙ ፃፉልን።

የቴሌግራም አድራሻችን @Rambo_one
2.0K viewsMr.x, 15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 08:04:01
እንኮን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ።



ልዩ ቅናሽ የገናን በዓልን በማስመልከት

ኦሪጅናል ኤርፖድ መግዛት ለፈለጋችሁ ሁሉ !

1000ብር   600 ብር ብቻ

     አምስት ቀን ሚቆይ ቻርጀር
      Touch ሴንሰር ያለዉ
       packed

መግዛት የፈለጋችሁ ልጆች ከታች ባለዉ የቴሌግራም አድራሻ ዉስጥ በመግባት ስልክ ቁጥራችሁን አስቀምጡልን አዲስ አበባ ዉስጥ በ ራሳችን ትራንስፖርት ያሉበት ቦታ ድረስ ከ ገና ስጦታችን ጋር የምንልክሎት ይሆናል።
ከክፍለ ሀገር ሁለትና ከዚያ በላይ ሆናችሁ ለምትመጡ በ Ethio-Post በኩል የምንልክላችሁ ይሆናል።


የቴሌግራም አድራሻችን          @one1753

መልካም የገና በዓል
1.7K viewsMr.x, 05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 08:02:55
በመጪው ሰኔ ከ256 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ይሰጣል።

ለተመራቂ ተማሪዎቹ የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ከመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 146 ሺህ እና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 110 ሺህ በድምሩ ለ 256 ሺህ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እንደሚሰጥ በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢፕድ ገልጸዋል።

የፈተናውን መመሪያ ሰነድ ከማዘጋጀት ጀምሮ ለፈተናው የሚያስፈልጉ ነገሮችን የማሟላት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን የኮምፒዩተር አቅርቦት እና የተፈታኞች ብዛት በመለየት የመውጫ ፈተናውን በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

ሚኒስቴሩ ለፈተናው መሳካት ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ጋር በቅንጅት ይሠራል ብለዋል።

@QesemAcademy
1.4K viewsMr.x, 05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 08:01:54
ስትሮክን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ።

ስትሮክ በርካታ የዓለም ህዝብን የአልጋ ቁራኛ ያደረገ በሽታ ነው፡፡ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሶፍትዌር በመጠቀም እንግሊዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከበሽታው ማዳን መቻሏን ዴይሊሜል ዘግቧል፡፡

ሶፍትዌሩ ለሀኪሞች ያለው እገዛ ለታማሚው ሰው አስፈላጊውን ህክምና እንዲያደርጉ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ታካሚዎች በቶሎ ከህመማቸው እንዲፈወሱ ይረዳቸዋል ማለት ነው፡፡

የእንግሊዝ የጤና ሚኒስትር ስቲቭ ባርክሌ Brainomax በተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ እውን የሆነው ይህ ሶፍትዌር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በጤና ስርዓቱ ላይ እያመጣ ስላለው እምርታ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም ከበሽታው ለማገገም ያለውን እድል ከ 16 ወደ 48 በመቶ ከፍ እንዲል ስለማድረጉ እንግሊዝ አስታውቃለች፡፡ በየ ዓመቱ 85 ሺ ሰዎች በስትሮክ ለሚጠቁባት እንግሊዝ ይህ የአርቲፊሻል ኢንትለጀንስ ግኝት ትርጉሙ ከፍ ያለ ስለመሆኑ ሪፖርቱ አትቷል፡፡

EAI


@QesemAcademY
1.3K viewsMr.x, edited  05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 21:26:45
እንኮን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ።



ልዩ ቅናሽ የገናን በዓልን በማስመልከት

ኦሪጅናል ኤርፖድ መግዛት ለፈለጋችሁ ሁሉ !

1000ብር   600 ብር ብቻ

     አምስት ቀን ሚቆይ ቻርጀር
      Touch ሴንሰር ያለዉ
       packed

መግዛት የፈለጋችሁ ልጆች ከታች ባለዉ የቴሌግራም አድራሻ ዉስጥ በመግባት ስልክ ቁጥራችሁን አስቀምጡልን አዲስ አበባ ዉስጥ በ ራሳችን ትራንስፖርት ያሉበት ቦታ ድረስ ከ ገና ስጦታችን ጋር የምንልክሎት ይሆናል።
ከክፍለ ሀገር ሁለትና ከዚያ በላይ ሆናችሁ ለምትመጡ በ Ethio-Post በኩል የምንልክላችሁ ይሆናል።


የቴሌግራም አድራሻችን          @one1753

መልካም የገና በዓል
1.5K viewsMr.x, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 09:13:48
በ ቀሰም ገፅ ላይ ማስታወቂያ ማሰራት ለምትፈልጉ ደንበኞች በሙሉ

ቀሰም Academy ባለፉት ሁለት አመታት ለ High school እና ለግቢ ተማሪዎች ፣ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ መጣጥፎችን እንካችሁ በማለት ሲያገለግል የቆየ በአሁኑ ሰዓትም ከ 38,700 ቤተሰቦችን ለማፍራት ችሏል! ቻናላችን ከምንጊዜውም በላይ የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማስፋት የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ለመሸፈን በሚል ፣ ምርት እና አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅ ለሚፈልጉ ደንበኞች በሩን ክፍት አርጓል!

በቀሰም ላይ የ High school እንዲሁም የCampus ተማሪ ወጣቶች ተሰብስበው ስላሉ እንደ ፅህፈት መሳሪያዎች ፤ Electronics ፣ Scholarship Conseltancy ፤ Fashion ፤ Tutor ፣ እና ሌሉሎች ከትምህርትጋር የተያያዙ ምርት እና አገልግሎትዎን በማስተዋወቅዎ የሚያገኙት የተለየ አትራፊ ያደርጎታል!

ቻናላችን ከታች ያሉትን የማስታወቂያ ይዘቶች በጭራሽ አይቀበልም ፦
የፍትወት ቀስቃሽ ምስሎች
የመድሃኒት እና የ አደንዛዥ ዕፅ ምርቶች
አሳሳች የማስታወቂያ ፅሁፎች

ምርት እና አገልግሎታችሁን ማስተዋወቅ የምትፈልጉ ክቡራን ደንበኞች ፣ ልዩ ቅናሽ ያለው ተመጣጣኝ ዋጋ እየጠበቃችሁ ስለሆነ @QesemADs_Bot ላይ አናግሩን!
227 viewsቻLu, 06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 09:03:06 #Qesem_Motivation


ፈልገው!

አንድ የኔ የምትለው ፣ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ልታጣውና እንዲለይህ የማትፈልገው ፣ ዘወትር በአብሮነቱ የምትደሰትበት ፣ ስለ እርዳታው የምትረካበት ፣ ጭንቀትህን የምታጋራው ፣ ሃሳብህን የምታካፍለው ፣ ህልምህን የምታዋየው ያንተ የሆነ ሰው ያስፈልግሃል ። እርሱን አተህ መኖር የማትችለው ፣ እንዲለይህ ሳይሆን የተወሰነ እንዲርቅህ እንኳን የማትፈልገው ሁነኛ ልዩ ሰው ያሻሃል ። በዚህ ሃሳብ ጅረት ብዙ ሰዎችን ታስባለህ ፤ ማንን የልብ ወዳጅህ ፣ ማንንስ የቅርብህ ሰው ማድረግ እንዳለብህ በማውጣትና በማውረድ፣ በዙሪያህ ያሉ ሰዎችንም ልታነፃፅር ትችላለህ ። ነገር ግን ድካምህ ሁሉ ትርፍ አልባ ከንቱ ድካም እንደሆነ ስታውቅ በእራስህ ማዘንህ አይቀርም ። ሁሌም አብሮህ እያለ የዘነጋሀውን ፣ በሄድክበት ሁሉ የሚከተልህን ፣ ባንተ መኖር ውስጥ ያለን አንድ ሰው ተመልከት ።

አዎ! ጀግናዬ..! እርሱን ፈልገው! ያንን በውስጥህ የፈጠርከውን ፣ ሌላ አካል እንዲያደርግልህ የምትጠብቀውን ፣ አለኝታህ እንዲሆን የምትመኘውን ፣ መተማመኛህ ይሆን ዘንድ የምትናፍቀውን ፣ ጠባቂህ እንዲሁም ተረጂህ እንደሆን የምትፈልገውን ሌላኛውን ሰው በውስጥህ ፈልገው ። ለእራሱ ጠበቃ መሆን የሚችለውን ፣ የፈለገውን ከማድረግ ወደኋላ የማይለውን ፣ እራሱን እስከ ጥግ የሚወደውን ፣ በውስጡ ያለውን ፍቅር ለሰዎች በጉልህ የሚያካፍለውን ፣ እራሱን በመሆን ሌሎችም እራሳቸውን እንዲሆኑ ፣ በእራሳቸው እንዲቆሙ ፣ በማንነታቸው እንዲኮር ማድረግ የሚችለውን አስደናቂ ሰው በእራስህ ውስጥ ፈልገው ። አምላክ ይወድሃል ፣ ለዚህም በአምሳሉ ፈጥሮሃል ፣ በመንፈሱ ቃኝቶሃል ፤ ህያዊት ነፍስን አድሎሃል ። የትኛውም ሰው ሌላውን ተደግፎና በሌላው ላይ ተንጠልጥሎ ይኖር ዘንድ አልተፈጠረም ። ወደ ምድር መምጣትህ በእራሱ ለእራስህ ብቁ መሆንህን ማሳያ ነው ።

አዎ! የሚወዱህ ሰዎች ይኖራሉ ፣ በምትፈልጋቸው ጊዜ ሁሉ እንደሚጠብቁህ ግን እርግጠኛ አይደለህም ። ወገን ፣ ዘመድ ፣ ቤተሰብ ፣ ጓደኛ ይኖርሃል ምኞትና ህልምህ ግን በእነርሱ አይሞላም ፤ በእነርሱም አይሳካም ። ከጀርባህ ያለው ጭብጨባ ብርታትህ እንጂ ከግብህ የሚያደርስህ አይደለም ። በምናብህ የሳልከው ፣ ሁሌም ሲደግፍህና ሲያበረታታህ ፣ አብሮህ ሲጓዝ ፣ ለህልምህ ግበዓት ሲሆን ፣ ወደ ከፍታው ሲመራህ የምትመለከተው ያ ሰው ሩቅ ያለ እንዳይመስልህ ። ርቀቱን በማሰብም ረጅም ርቀት አትጓዝ ፣ ብዙ ወጪ አታውጣ ። ያለረፍት ሌትተቀን ስትፈልገው የነበረው ሰው የትም ሳይሆን ውስጥህ ነው ያለው ። ትግል የሌለው ፣ ድካም የማይጠይቅ ፣ በጥበቃ የማያሰለች ፣ የማያታክት እውቀትና እምነትህን ብቻ የሚሻ ቀላል ፍለጋ ነው ። አይበገሬውን ግሩም ሰው ፈልገህ አግኘው ፤ ዘወትር የሚጠብቅህን ድንቅ ሰው አስወጣው ። ለአራስህ በሚያገለግልህ መጠን ብዙዎችን ያገለግል ዘንድ ብቁና ዝግጁ አድርገው ።



@QesemAcademy
332 viewsMr.x, 06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 09:00:08
የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የ5ኛ ዓመት የኤሌክትሮ መካኒካል ተማሪ የነበረው ተማሪ ታድሷል ዘመነ ነጋሲ ታህሳስ 30 ቀን 2015 ዓ.ም.  በደረሰበት ድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት  ተለይቷል ሲል ዩንቨርሲቲው በፌስቡክ ገጹ አሳውቋል።

ዩኒቨርስቲው ጨምሮም በተማሪው ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልፆ ለቤተሰቦቹ ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለጓደኞቹና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ተመኝቷል።

ደብረታቦር ዩንቨርሲቲ በሀዘን መግለጫው የተማሪ ታድሷል ዘመነን ህልፈት ምክንያት ባይጠቅስም ጥቆማ ያደረሱን የግቢው የATC ቤተሰቦች <ሟች ተማሪ ታድሷል እና ሁለት ሴት ተማሪዎች ከቤተክርስቲያን ሲመለሱ የሴቶቹን የሞባይል ቀፎ ለመውሰድ ሲሞክሩ ሟች ተማሪ ታድሷል በመጋፈጡ ተኩሰው እንደገደሉት ነግረውናል።>

የተማሪው ህይወት ያለፈው ከዩንቨርሲቲው በቅርብ ርቀት ላይ  መሆኑን የነገሩን ተማሪዎቹ በዛሬው ዕለትም ድርጊቱን ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን ሰምተናል።

በከተማው በተለይም በግቢ ተማሪዎች ላይ የሚፈፀመው ጭካኔ የተሞላበት ዝርፊያ ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መምጣቱ እና በዩንቨርሲቲው አካባቢ የሚደፈሩ ሴት ተማሪዎች ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ የከተማው አስተዳደር ትኩረት ሰጥቶ መፍትሄ ይሰጣቸው ዘንድ የደብረታቦር ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ጠይቀዋል።


   @QesemAcademy
353 viewsMr.x, 06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ