Get Mystery Box with random crypto!

ስትሮክን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ። ስትሮክ በርካታ የዓለም ህዝብን የአልጋ ቁራኛ ያደረገ በሽ | QesemAcademy

ስትሮክን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ።

ስትሮክ በርካታ የዓለም ህዝብን የአልጋ ቁራኛ ያደረገ በሽታ ነው፡፡ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሶፍትዌር በመጠቀም እንግሊዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከበሽታው ማዳን መቻሏን ዴይሊሜል ዘግቧል፡፡

ሶፍትዌሩ ለሀኪሞች ያለው እገዛ ለታማሚው ሰው አስፈላጊውን ህክምና እንዲያደርጉ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ታካሚዎች በቶሎ ከህመማቸው እንዲፈወሱ ይረዳቸዋል ማለት ነው፡፡

የእንግሊዝ የጤና ሚኒስትር ስቲቭ ባርክሌ Brainomax በተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ እውን የሆነው ይህ ሶፍትዌር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በጤና ስርዓቱ ላይ እያመጣ ስላለው እምርታ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም ከበሽታው ለማገገም ያለውን እድል ከ 16 ወደ 48 በመቶ ከፍ እንዲል ስለማድረጉ እንግሊዝ አስታውቃለች፡፡ በየ ዓመቱ 85 ሺ ሰዎች በስትሮክ ለሚጠቁባት እንግሊዝ ይህ የአርቲፊሻል ኢንትለጀንስ ግኝት ትርጉሙ ከፍ ያለ ስለመሆኑ ሪፖርቱ አትቷል፡፡

EAI


@QesemAcademY