Get Mystery Box with random crypto!

በመጪው ሰኔ ከ256 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ይሰጣል። ለተመራቂ ተማሪዎ | QesemAcademy

በመጪው ሰኔ ከ256 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ይሰጣል።

ለተመራቂ ተማሪዎቹ የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ከመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 146 ሺህ እና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 110 ሺህ በድምሩ ለ 256 ሺህ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እንደሚሰጥ በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢፕድ ገልጸዋል።

የፈተናውን መመሪያ ሰነድ ከማዘጋጀት ጀምሮ ለፈተናው የሚያስፈልጉ ነገሮችን የማሟላት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን የኮምፒዩተር አቅርቦት እና የተፈታኞች ብዛት በመለየት የመውጫ ፈተናውን በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

ሚኒስቴሩ ለፈተናው መሳካት ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ጋር በቅንጅት ይሠራል ብለዋል።

@QesemAcademy