Get Mystery Box with random crypto!

የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የ5ኛ ዓመት የኤሌክትሮ መካኒካል ተማሪ የነበረው ተማሪ ታድሷል ዘመነ ነጋሲ | QesemAcademy

የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የ5ኛ ዓመት የኤሌክትሮ መካኒካል ተማሪ የነበረው ተማሪ ታድሷል ዘመነ ነጋሲ ታህሳስ 30 ቀን 2015 ዓ.ም.  በደረሰበት ድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት  ተለይቷል ሲል ዩንቨርሲቲው በፌስቡክ ገጹ አሳውቋል።

ዩኒቨርስቲው ጨምሮም በተማሪው ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልፆ ለቤተሰቦቹ ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለጓደኞቹና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ተመኝቷል።

ደብረታቦር ዩንቨርሲቲ በሀዘን መግለጫው የተማሪ ታድሷል ዘመነን ህልፈት ምክንያት ባይጠቅስም ጥቆማ ያደረሱን የግቢው የATC ቤተሰቦች <ሟች ተማሪ ታድሷል እና ሁለት ሴት ተማሪዎች ከቤተክርስቲያን ሲመለሱ የሴቶቹን የሞባይል ቀፎ ለመውሰድ ሲሞክሩ ሟች ተማሪ ታድሷል በመጋፈጡ ተኩሰው እንደገደሉት ነግረውናል።>

የተማሪው ህይወት ያለፈው ከዩንቨርሲቲው በቅርብ ርቀት ላይ  መሆኑን የነገሩን ተማሪዎቹ በዛሬው ዕለትም ድርጊቱን ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን ሰምተናል።

በከተማው በተለይም በግቢ ተማሪዎች ላይ የሚፈፀመው ጭካኔ የተሞላበት ዝርፊያ ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መምጣቱ እና በዩንቨርሲቲው አካባቢ የሚደፈሩ ሴት ተማሪዎች ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ የከተማው አስተዳደር ትኩረት ሰጥቶ መፍትሄ ይሰጣቸው ዘንድ የደብረታቦር ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ጠይቀዋል።


   @QesemAcademy