Get Mystery Box with random crypto!

#Qesem_Motivation ፈልገው! አንድ የኔ የምትለው ፣ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ | QesemAcademy

#Qesem_Motivation


ፈልገው!

አንድ የኔ የምትለው ፣ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ልታጣውና እንዲለይህ የማትፈልገው ፣ ዘወትር በአብሮነቱ የምትደሰትበት ፣ ስለ እርዳታው የምትረካበት ፣ ጭንቀትህን የምታጋራው ፣ ሃሳብህን የምታካፍለው ፣ ህልምህን የምታዋየው ያንተ የሆነ ሰው ያስፈልግሃል ። እርሱን አተህ መኖር የማትችለው ፣ እንዲለይህ ሳይሆን የተወሰነ እንዲርቅህ እንኳን የማትፈልገው ሁነኛ ልዩ ሰው ያሻሃል ። በዚህ ሃሳብ ጅረት ብዙ ሰዎችን ታስባለህ ፤ ማንን የልብ ወዳጅህ ፣ ማንንስ የቅርብህ ሰው ማድረግ እንዳለብህ በማውጣትና በማውረድ፣ በዙሪያህ ያሉ ሰዎችንም ልታነፃፅር ትችላለህ ። ነገር ግን ድካምህ ሁሉ ትርፍ አልባ ከንቱ ድካም እንደሆነ ስታውቅ በእራስህ ማዘንህ አይቀርም ። ሁሌም አብሮህ እያለ የዘነጋሀውን ፣ በሄድክበት ሁሉ የሚከተልህን ፣ ባንተ መኖር ውስጥ ያለን አንድ ሰው ተመልከት ።

አዎ! ጀግናዬ..! እርሱን ፈልገው! ያንን በውስጥህ የፈጠርከውን ፣ ሌላ አካል እንዲያደርግልህ የምትጠብቀውን ፣ አለኝታህ እንዲሆን የምትመኘውን ፣ መተማመኛህ ይሆን ዘንድ የምትናፍቀውን ፣ ጠባቂህ እንዲሁም ተረጂህ እንደሆን የምትፈልገውን ሌላኛውን ሰው በውስጥህ ፈልገው ። ለእራሱ ጠበቃ መሆን የሚችለውን ፣ የፈለገውን ከማድረግ ወደኋላ የማይለውን ፣ እራሱን እስከ ጥግ የሚወደውን ፣ በውስጡ ያለውን ፍቅር ለሰዎች በጉልህ የሚያካፍለውን ፣ እራሱን በመሆን ሌሎችም እራሳቸውን እንዲሆኑ ፣ በእራሳቸው እንዲቆሙ ፣ በማንነታቸው እንዲኮር ማድረግ የሚችለውን አስደናቂ ሰው በእራስህ ውስጥ ፈልገው ። አምላክ ይወድሃል ፣ ለዚህም በአምሳሉ ፈጥሮሃል ፣ በመንፈሱ ቃኝቶሃል ፤ ህያዊት ነፍስን አድሎሃል ። የትኛውም ሰው ሌላውን ተደግፎና በሌላው ላይ ተንጠልጥሎ ይኖር ዘንድ አልተፈጠረም ። ወደ ምድር መምጣትህ በእራሱ ለእራስህ ብቁ መሆንህን ማሳያ ነው ።

አዎ! የሚወዱህ ሰዎች ይኖራሉ ፣ በምትፈልጋቸው ጊዜ ሁሉ እንደሚጠብቁህ ግን እርግጠኛ አይደለህም ። ወገን ፣ ዘመድ ፣ ቤተሰብ ፣ ጓደኛ ይኖርሃል ምኞትና ህልምህ ግን በእነርሱ አይሞላም ፤ በእነርሱም አይሳካም ። ከጀርባህ ያለው ጭብጨባ ብርታትህ እንጂ ከግብህ የሚያደርስህ አይደለም ። በምናብህ የሳልከው ፣ ሁሌም ሲደግፍህና ሲያበረታታህ ፣ አብሮህ ሲጓዝ ፣ ለህልምህ ግበዓት ሲሆን ፣ ወደ ከፍታው ሲመራህ የምትመለከተው ያ ሰው ሩቅ ያለ እንዳይመስልህ ። ርቀቱን በማሰብም ረጅም ርቀት አትጓዝ ፣ ብዙ ወጪ አታውጣ ። ያለረፍት ሌትተቀን ስትፈልገው የነበረው ሰው የትም ሳይሆን ውስጥህ ነው ያለው ። ትግል የሌለው ፣ ድካም የማይጠይቅ ፣ በጥበቃ የማያሰለች ፣ የማያታክት እውቀትና እምነትህን ብቻ የሚሻ ቀላል ፍለጋ ነው ። አይበገሬውን ግሩም ሰው ፈልገህ አግኘው ፤ ዘወትር የሚጠብቅህን ድንቅ ሰው አስወጣው ። ለአራስህ በሚያገለግልህ መጠን ብዙዎችን ያገለግል ዘንድ ብቁና ዝግጁ አድርገው ።



@QesemAcademy