Get Mystery Box with random crypto!

አገልግል

የቴሌግራም ቻናል አርማ ourmereja — አገልግል
የቴሌግራም ቻናል አርማ ourmereja — አገልግል
የሰርጥ አድራሻ: @ourmereja
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.21K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-07-02 10:10:40 ከዚ ቻነል ምን ማግኘት ነው የሚፈልጉት ?
anonymous poll

ሁሉንም – 8
57%

ዋና ዋና ሀገራዊ ዜናዎች – 2
14%

ሳይንሳዊ እና ትምህርታዊ ነገሮችን – 2
14%

አነቃቂ ጥቅሶች እና አባባሎች – 2
14%

14 people voted so far.
471 views07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 07:09:36 You'll never regret ignoring anything that feels off, forced, fake, unnecessary or not aligned with your healing and growth.
438 views04:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 13:40:08 የትግራይ ክልል መንግስት ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ ለድርድር ዝግጁ መሆኑንና የኬንያው ፕሬዝዳንት አደራዳሪ እንዲሆኑ ፍላጎት እንዳለው ባሰራጨው ደብዳቤ የገለጠ ሲሆን ለክልሉ ህዝብ ግን ትግሉን ወደመጨረሻው ምዕራፍ ለማሸጋገር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል። 
የክልሉ ኘሬዝዳንት ደብረፅዮን ገብረሚካዔል ማክሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች በትግርኛ በሰጡት መግለጫ በቅርቡ በተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች የተደረጉ ኮንፈረንሶች ትግሉ ወደ መጨረሻ ደረጃ እንዲደርስ ከመግባባት ተደርሷል ብለዋል።
ከፌደራል መንግስት ጋር እየተካሄደ ነው በሚባለው ውይይትና ድርድር ዙርያ እስከ አሁን ድረስ ምንም አይነት ድርድር  አልተካሄደም ፣ ህዝባችን ከበባ ላይ  እንዲሁም መሬታችን ተወሮ ባለበት ሁኔታ ወደ ድርድር የምንቀርብበት ሁኔታ የለም ሲሉ ደብረፅዮን አብራርተዋል።
በአጠቃላይ ዋና አላማችን የትግራይ ህዝብ መብትና ጥቅም ማስከበር ሲሆን የትግራይ ሉአላዊ ግዛት መከበር ፣ ሪፈረንደም ፣ የትግራይ ሰራዊት ሁኔታ ፣ በትግራይ ላይ “የዘር ማጥፋት የፈፀሙ” ተጠያቂ እንዲሆኑ መስራት እና ተገቢ ካሳ እንዲከፈል ማድረግ ለድርድር የማይቀርቡ ነጥቦች ናቸው ብለዋል ።
“የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ መውጣት አለበት፣ ባልወጣበት ሁኔታ አንደራደርም” ያሉት ፕሬዝዳንቱ “በቅርብ ጊዜ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የትግራይ መንግስት በምዕራብ ትግራይ ላይ ያለውን አቋም ቀይሯል ተላሳልሷል የሚባለው ውሸት ነው፡፡ ይልቁንም የተያዙ መሬቶቻችንን ለማስለቀቅ ነው እየሰራን ነው” ብለዋል።
ደብረፂዮን ጨምረውም  “ውይይት አይኑር አላልንም። ነገር ግን አስቀድሜ የዘረዘርኳቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ ምን ነገር ይዘን ነው የምንወያየው? ሲሉ ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል በራሳቸው በክልሉ ፕሬዝዳንት ተፅፎ ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ በተሰራጨ ደብዳቤ የትግራይ ክልል በአፍሪቃ ሕብረት በኩል የሚደረገውን ድርድር ለመቀጠል እንደሚቸገርና በአደራዳሪው ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ላይ የገለልተኝነት ጥያቄ አንስቷል። የአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽነርንም በብርቱ ተችቷል። 
በምትኩም የኬንያው ኘሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አደራዳሪ እንዲሆኑ እንደሚፈልግ የትግራይ ክልል መንግስት በደብዳቤው አስታውቋል። 
ኬንያታ ገለልተኛ መሆናቸውን ያስመሰከሩና እምነት የምንጥልባቸው መሪ ናቸው ያለው የትግራይ ክልል ደብዳቤ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስና የመንግስታቱ ድርጅት በድርድሩ እንዲሳተፉ ፍላጎት እንዳለው ዘርዝሯል። 
የታንዛኒያ መንግስት እያደረገ ያለውን የሰላም ጥረት ያመሰገነው የትግራይ ክልል የአፍሪቃ ህብረት አባል ሐገር የሆነችው ኬንያ ከዚህ ቀደም ያደረገችውን የማደራደር ሙከራ በዝርዝር አላብራራም። 
ይህ የትግራይ ክልል ደብዳቤ በናይጄሪያው የቀድሞ ኘሬዝዳንት ኦባሳንጆ በአፍሪቃ ሕብረት በኩል ሲደረግ የነበረውን የድርድር ሙከራ ወደፊት ለመራመድ እንደሚያዳግተው ግልፅ አድርጓል። 
በፌደራሉ መንግስት በኩል 
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ትናንት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለቀርቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት አገርን ወክሎ የሚደራደር ብሄራዊ ኮሚቴ እንደተቋቋመ ገልጸዋል። 
ብሄራዊ የድርድር ኮሚቴውን የሚመሩት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደሆኑ እና ኮሚቴው በቅርቡ ለገዥው ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምክረ ሃሳቡን እንደሚያቀርብ እና ያኔ ምክረ ሃሳቡ ለሕዝብ እንደሚገለጽ ተናግረዋል። 
ዐቢይ ከሕወሃት ጋር እስካሁን በየትም አገር ድርድር እንዳልተጀመረም ገልጸዋል።
996 views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 18:42:58
ሪፖርተር ጋዜጣ እና የተለያዩ ሚዲያዎች ዛሬ ባወጡት መረጃ በቀጣይ ጥቂት ሳምንታት ስልክ፣ መብራት፣ ባንክ እና ሌሎች አገልግሎቶች በትግራይ ክልል ሊጀመሩ እንደሚችሉ ገልጿል። በዚህም ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ከፍተኛ የፖለቲካ ሃለፊ ገልፀውልናል ብሏል።
========================
872 views15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 07:01:11 የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ የፈረንሳዩ ጋዜጣ ሊ ሞንድ ሕወሃት በወልቃይት ላይ ያለውን የይገባኛል ጥያቄ ቀስ በቀስ እየተወ ስለመሆኑ ከምዕራባዊያን ዲፕሎማቶች ሰምቻለሁ በማለት ያወጣውን ዘገባ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሠፈሩት መልዕክት አጣጥለውታል። ሕወሃት ለዘገባው ኦፊሴላዊ ምላሽ እንደሚሰጥ የገለጡት ጌታቸው፣ ሕወሃት በኃይል የተያዙ ሁሉንም የትግራይ አካባቢዎች በሰላምም ይሁን በኃይል ለማስመለስ ቁርጠኛ ነው ብለዋል።
919 views04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 19:38:08
የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራዩ ሕወሃት በታንዛኒያ አሩሻ ከተማ ድርድር ሊጀምሩ እንደሚችሉ ከምንጮች መስማቱን ጠቅሶ የፈረንሳዩ ሊ ሞንድ ጋዜጣ ዘግቧል። ጋዜጣው የአፍሪካ እና ምዕራባዊያን አገራት ዲፕሎማቶች የሁለቱ ወገኖች ድርድሩን ከሰኔ ወር ማለቂያ በፊት ሊጀምሩ እንደሚችሉ ነግረውኛል ብሏል። ምዕራባዊያን ዲፕሎማቶች ሕወሃት የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች በሚቆጣጠሩት ወልቃይት ግዛት ላይ ያለውን የይገባኛል ጥያቄ ቀስ በቀስ እየተወው እንደሆነ ጥቆማ መስጠታቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጧል። ከመጋረጃው ጀርባ በሚደረገው ድርድር ከሁለቱ ወገኖች ከእያንዳንዳቸው አምስት አባላት ያሏቸው ተደራዳሪዎች ሊሳተፉበት እንደሚችሉም ዘገባው ጠቅሷል።
1.1K views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 21:54:26
#News Alert- ብሄራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የአገሪቱን ወቅታዊ የጸጥታ እና የብሄራዊ ደኅንነት ስጋቶች መገምገሙን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ምክር ቤቱ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ የትግራዩ ጁንታ፣ የሱማሊያው አልሸባብ፣ በኮንትሮባንድ የተሠማሩ አካላት፣ ሕገወጥ ታጣቂዎች፣ ጽንፈኛ መገናኛ ብዙኀን፣ የፖለቲካ ቡድኖች እና አክራሪ ሐይማኖተኞች እንዲሁም የውጭ ጣልቃ ገብነት በአገሪቱ ላይ የደቀኑትን ስጋት መገምገሙን አብራርቷል።

መንግሥት እነዚህን አገራዊ ስጋቶች በሆደ ሰፊነት መያዙ እንደ ድክመት እንደተቆጠረበት ማረጋገጡን የገለጠው ምክር ቤቱ፣ መንግሥት ከእንግዲህ በመገናኛ ብዙኀን፣ ማኅበረሰብ አንቂነት፣ በሐይማኖት እና በፖለቲካ ድርጅት ሽፋን የሚደረጉ አገር የማፍረስ ሴራዎችን መንግሥት አይታገስም ብሏል። ምክር ቤቱ በዚሁ መግለጫው፣ አልሸባብ ከትግራዩ "ጁንታ" እና ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ለመፍጠር የሞከራቸውን ትስስሮችም የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በተሳካ ሁኔታ አክሽፈዋል ብሏል።

ምክር ቤቱ ባለፈው ሚያዝያ ወር ባደረገው ግምገማ ያስቀመጣቸው ግቦች ባብዛኛው እንደተሳኩ ማረጋጠን እና የመንግሥት ሕግ የማስከበር ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጫው አክሎ ገልጧል። ምክር ቤቱ በዚሁ መግለጫው፣ በተለይ በኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና አማራ ክልሎች በርካታ ሕገወጥ ቡድኖች እና ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ፣ ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎች እንደተሰበሰቡ እና በሕገወጥ እንቅስቃሴ የተገኙ የማኅበረሰብ አንቂዎች ሥርዓት እንዲይዙ መደረጉንም አብራርቷል።
821 viewsedited  18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 21:51:43 ፌደራል መንግሥት ለቀጣዩ ዓመት ካዘጋጀው 786 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ውስጥ ለትግራይ ክልል 12 ቢሊዮን ብር መመደቡን ለማወቅ ተችሏል ። ለኦሮሚያ ክልል 71 ቢሊዮን ብር፣ ለአማራ ክልል 44 ቢሊዮን ብር፣ ለደቡብ ክልል 26.5 ቢሊዮን ብር፣ ለሱማሌ ክልል 20.5 ቢሊዮን ብር፣ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 6.4 ቢሊዮን ብር፣ ለአፋር ክልል 6.2 ቢሊዮን ብር፣ ለቤንሻንጉል ክልል 3.7 ቢሊዮን ብር፣ ለሐረሬ ክልል 1.5 ቢሊዮን ብር፣ ለጋምቤላ ክልል 2.4 ቢሊዮን ብር እና ለሲዳማ ክልል ደሞ 8.4 ቢሊዮን ብር ድጎማ ተመድቦላቸዋል። በጀቱ የ234 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንደሚገጥመው እና ዘንድሮ ይመዘገባል ተብሎ የተጠበቀው የ8.7 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት እንደማይሳካ ገንዘብ ሚንስትር አሕመድ ትናንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል።
552 viewsedited  18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 19:03:34 SIGNS OF MATURITY:

- You forgive more
- You don't force love
- You don't judge easily
- You respect differences
- You become more open-minded
- You like to keep quiet instead of engaging in a nonsense fight
- Your happiness doesn't depend on other people but on your inner self.
762 views16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 17:36:02 ቱርክ (ተርኪ) ስሟን ወደ ተርኪዬ ቀየረች !

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) በድርጅቱ የቱርክ /ተርኪ ስያሜ ወደ ተርኪዬ መቀየሩን ዛሬ በይፋ አሳውቋል።

ይህ ተርኪዬ የሚለው ስያሜ የቱርክን ሕዝብ ባህል፣ ሥልጣኔ እና ዕሴቶችን በበለጠ የሚወክል አገላለጽ ነው " በማለት ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ባለፈው ወር ተናግረው ነበር።

ለውጡን ተከትሎ TRT የተሰኘው የሀገሪቱ የመንግስት ወዲያው ተግባራዊ አድርጓል።

ሚዲያው ለሀገሪቱ ስያሜ ለውጥ ምክንያት ብሎ ካስቀመጣቸው ነገሮች መካከል " ቱርኪ " የሚለው ስያሜ ምዕራባውያን በዓል ወቅት ለምግብ ከምትቀርበው የዶሮ ዝርያ ጋር መያያዙ እንደሆነ ገልጿል።

በተጨማሪ በኬምብሪጅ የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ላይ ለቃሉ ተሰጠው ትርጉም እንደሆነ ተመላክቷል። በመዝገበ ቃላቱ 'ተርኪ' የሚለው ቃል፤ 'ሙሉ በሙሉ ያልተሳካ' ወይም 'ውድቀት የሆነ ነገር' የሚል ትርጓሜን ይሰጣል።

የቱርክ /ተርኪ መንግስት ሀገሪቱን በአዲስ ስያሜ ተርኪዬ ለማስተዋወቅ ዘመቻ ማድረግ የሰነባበተ ሲሆን በአገሪቱ ተመርተው ወደ ውጪ የሚላኩ ሁሉም ምርቶች ላይ አዲሱ ስያሜ እንዲሰፍር ተደርጓል።

ካለፈው ጥር ወር ጀምሮም  "ሄሎ ተርኪዬ" የሚል የቱሪዝም ዘመቻ እየተካሄደ ነው።

መረጃው የቢቢሲ ነው።
748 views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ