2022-05-27 16:05:36
ታሪክን የኋሊት
መሀመድ ኡመር ጋዳፊ ስለ መንግስቱ ሀይለማሪያም የተናገረው።
.
ኮረኔል መንግስቱን እወደው ነበር። ብዙም እንደሚባለው አምባገነን አልነበረም። ከኮረኔል መንግስቱ ጋር በፈረጆቹ 1988 አዲስ አበባ ላይ በዝግ መክረን ነበር። የአፍሪካ ጥምር ጦር ለማቋቋምና በቀይ ባህር ዳርቻ ያሉ አገሮችን ለመቆጣጠር አስበን ነበር። መንግስቱም እሽ ብሎ ተስማምተን ነበር። ወዲያው ግን ለመንግስቱ የቤት ስራ ተሰጠው።
በኢትዮጵያ የመሰነጣጠቅ ፖለቲካ ተጀምሯል። መንግስቱ ጥምር ጦር ለማቋቋም ያሰበው አገሪቱ ላይ ያሉትን ታጣቂዎች ከደመሰሰ በኋላ ነው። ሱዳንና ግብፅ ኬኒያ ጅቡቲ ግን ለጥምር ጦር ማቋቋም እሽ ብለውን በኋላ ከድተውናል። ለአሜሪካና ለእስራኤል ሚስጥሩን ሸጡት። በዚህ የተናደደው መንግስቱ የጅቡቲውን መሪ አሰፈራራው። አንዲት የምዕራባውያን ጅቡቲ ከሰፈረ፣ አለቅህም የሚል ነበር ማስፈራሪያው። በወቅቱ መንግስቱ ከምዕራባውያን ጋር ጥል ነበር። ያጣላቸው እነሱ ጅቡቲን ላይ መተው ለመስፈር ፈልገው እሱ አይቻልም ብሎ ጅቡቲን ማስፈራራቱ ነው።። ፈረንሳይ ከጁቡቲ አልፋ ማሊ፣ ጊኒን፣ ኒጀርን በቅኝ ግዛት እየገዛች ነበር።
.
መንግስቱ ባንድ ግዜ ከሁሉም ጋር ተጣላ። ሱዳንና ግብፅ ጁቡቲ ኬኒያ ሲአይኤ ሞሳድ
ሆነው መከሩበት። ያነየ እነ ሱዳን እነ ግብፅ እነ ኬኒያ እነ ጅቢቲ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስቱን ለሚዋጉ ሀይሎች ድጋፍ ያደርጉ ነበር። እኔ ሱዳንን ተይ ብያት ነበር። መጨረሻ ላይ ግን ሳናሰበው መንግስቱን አሶረዱት። በተቻለኝ አቅም ግን ከነበሩን አውሮፕላኖች በተጨማሪ ያሉንን የጀት ቦንቦች ለመንግስቱ ሰተነው ነበር። እስራኤል አሜሪካ ኬኒያ ጅቡቲ ግብፅ ሱዳን ምዕራባውያን ሆነው ነው መንግስቱን የወገት። ሩሲያ ግን ያነየ ከኢትዮጵያ ጎን ብትሆንም እንዳሁኑ አቅም የላትም ነበር።
እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ላይ የምታደርሰውን ግፍ መንግስቱ መቃወሙ ነው ያስጠመደው። ሁለተኛ የቀይ ባህር በር ከኢትዮጵያ በላይ አለቃ የለውም የሚል ህልም ነበረው። አሜሪካና አጋሯቿ ግን ጁቡቲና ኬኒያን መጀመሪያ ይዘዋል። ሱዳን በግብፅ ተሸውዳ ለሽምቅ ተዋጊዎቹ ማሰልጠኛ ማዕከል ተደርጋ ነበር። ሁለት ጊዜ የኛ ጀቶች ከሊቢያ በረው ድብደባ አድርገው ነበር። ግን የተባለው ውጤት አልመጣም። ጓድ መንግስቱም እንዲህ በቀላሉ የሚበገር አልነበረም። በኋላ ላይ ጀነራሎቹ ለዶላር ፍቅር ሲወድቁ እሱም ተሸነፈ።
.
ከዛ በኋላ ኤርትራም አገር ሆነች። ኢትዮጵያም አገር ሆነች። ሁለቱን አገሮች የመሰረቷቸው ምዕራባውያን እና አሜሪካ እስራኤል ናቸው ። ኢሳያስ እንደገና ከዳቸው። ኢትዮጵያን የሚመራው ቡድን ሁሉም ነገሩ አሜሪካ ሁሉም ስረአቱ ምዕራባውያን ሆኖ መጣ። የአፍሪካ ነፃነት አቀንቃኝ የሆነችው አገር ኢትዮጵያ፣ የምዕራባውያን ተላላኪ ስትሆን የአፍሪካ ህብረት ከአዲስ አበባ ወደ ሊቢያ እንዲዛወር ተከራኬሪያለሁ።
ሆኖም መንግስቱ ወደር የለለው ጥቁር የአፍሪካን አንድነትን ወዳጅና አፍቃሪ መሪ ነበር። መንግስቱ ባይሴርበት ኖሮ፣ ሱዳንና ግብፅ፣ ኬኒያና ጅቡቲ፣ ባይከዱን የአፍሪካ ጥምር ጦርና ፣የጥምር ጦሩ አመታዊ ሀብት በአፍሪካ ወርቅ ብቻ እንዲሸፈን ተስማምተን ነበር። ግን አልሆነም።
ፕሬዚዳንት መሀመድ ኡመር ጋዳፊ በዘመነ ስልጣኑ የሚለው የታሪክ መፅሀፉ ላይ ካሰፈራቸው በልጁ የታተመው አዲሱ የአባቱ ሂዎተ መፀሀፍ ላይ የተወሰደ።
አሁን ፕሬዝዳንት መሀመድ ኡመር ጋዳፊ ሞቷል። ፕሬዝዳንት ኮረኔል መንግስቱም ዝንባቡዌ ሆነው የተወለዱበትን 81ኛ አመታቸውን እያከበሩ ነው።
ሱሌማን አብደላ
============================
629 views13:05