Get Mystery Box with random crypto!

አገልግል

የቴሌግራም ቻናል አርማ ourmereja — አገልግል
የቴሌግራም ቻናል አርማ ourmereja — አገልግል
የሰርጥ አድራሻ: @ourmereja
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.21K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-08 20:07:52 ኢንዶሚ ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው
በአገራችን በህጋዊ መንገድ ከውጪ አገር የሚገባ የኢንዶሚን ምርት የለም ተብሏል

በካንሰር የመያዝ እድልን የሚያስከትል ንጥረ ነገርን ይዟል በተባለው ኢንዶሚን ኑድልስ ላይ የተለያዩ አገራት ምርመራ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ ማሌዥያና ታይዋን በኢንዶሚን ላይ “ኢቲሊን ኦክሳይድ” የተባለውን ካንሰር አምጪ ንጥረ ነገር በማግኘታቸው ምርቶቹን ከገበያ ላይ እንዲሰበሰቡ ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን፣ በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ከውጪ አገር የሚገባ የኢንዶሚን ኑድልስ ምርት አለመኖሩን አመልክቷል፡፡ የባለስልጣኑ ምግብ ተቋማት ቁጥጥር ሃላፊ አቶ በትረ ጌታሁን ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ በባለስልጣኑ ተመዝግቦ በህጋዊ መንገድ ከውጪ አገር የሚገባ ኢንዶሚን የተባለ ምርት አለመኖሩን ጠቁመው፤ በአገር ውስጥ የሚመረትና በባለስልጣኑ ቁጥጥር የሚደረግበት ምርት አለ ብለዋል። ጉዳዩ እንደተሰማ በዚሁ የአገር ውስጥ ምርት ላይ ምርመራ መደረጉን የገለፁት ሃላፊው በምርቱም ላይ የተባለውን ዓይነት ለጤና ጎጂ የሆነ ንጥረ ነገር አለመገኘቱን አመልክተዋል፡፡ በካንሰር የመያዝ እድልን ያስከትላል የተባለውን ንጥረ ነገር ይዟል በተባለው የኢንዶሚን ምርት ላይ ምርመራ ማድረግ ከጀመሩ የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ ናይጄሪያ ስትሆን፤ ከኢንዶሚን ኑድልስ ምርት የተለያዩ ናሙናዎችንና ቅመማ ቅመሞችን በመውሰድ ኢቲሊን አክሳይድ የተባለው ንጥረ ነገር መኖር አለመኖሩን ለማወቅ ምርመራ እያደረገች መሆኑን አስታውቃለች፡፡በማሌዥያና ታይዋን ልዩ የዶሮ ጣዕም ባለው የኢንዶሚን ምርት ላይ ካንሰር አምጪው አደገኛው ንጥረ ነገር በመገኘቱ ምርቶቹ ከገበያ እንዲሰበሰቡ ተደርገዋል፡፡
ኢንዶሚን የተባለውን ኑድልስ የሚያመርተው የኢንዶኔዥያው ግዙፍ የምግብ አምራች ተቋም “ኢንዶፍድስ” የምግብ ምርቱ ጤናማ መሆኑን በመግለፅ እየተከራከረ ነው፡፡
361 viewsedited  17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 14:46:16
በመንግስትና በኦነግ ሸኔ መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር ያለስምምነት ተጠናቀቀ

ዋዜማ- በመንግስትና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) መካከል ላለፈው አንድ ሳምንት ሲደረግ የነበረው ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን የመንግስት ዋና ተደራዳሪ ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።

ሬድዋን በፅሁፍ መግለጫቸው ሁለቱ ወገኖች በታንዛኒያ በመጀመሪያው ዙር ያደረጉት ድርድር ገንቢ እንደነበር ነገር ግን በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት መድረስ አለመቻሉን ገልፀዋል። ስምምነት ያልተደረሰባቸውን ጉዳዮች ግን አልተናገሩም።

የሰላም ድርድሩ አስፈላጊነት ላይ በሁለቱም ወገን መግባባት መኖሩንና በቀጣይ ተመሳሳይ ድርድር ለማድረግ ዝግጁነት መኖሩንም ሬድዋን አመልክተዋል። አደራዳሪዎችን ያመሰገኑት ሬድዋን መንግስት ለሰላም ዝግጁ መሆኑንና በሀገሪቱ ህገመንግስት ማዕቀፍ ውስጥ ማናቸውንም ግጭቶች ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን አመልክተዋል።
በድርድሩ ዙሪያ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) በኩል ይህ ዘገባ እከተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ የተባለ ነገርየለም።
524 viewsedited  11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 08:32:45 በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች ትናንት እንደገና መከፈት እንደጀመሩ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለጡን ጠቅሶ የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። በክልሉ በኮሮና ወረርሽኝና ከዚያም በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ኹሉም ትምህርት ቤቶች ከሦስት ዓመታት በላይ ተዘግተው ነበር። በክልሉ የሚገኙ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች በጦርነቱ ከባድ ወይም ከፊል ጉዳት እንደደረሰባቸው ሲገለጽ ቆይቷል።
57 views05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 21:27:58
136 views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 12:51:23
241 views09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 07:47:04
ለራያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች
202 viewsedited  04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 15:20:15
ለአክሱም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች
457 viewsedited  12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 20:43:46
በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው የትምህርት ተቋማትን ዳግም ሥራ ለማስጀመር ሁሉም አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉና እንዲተባበሩ የዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች ጥሪ አቀረቡ።

በትግራይ ክልል ሥራ ያቆሙ ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሥራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

በዚህም መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎችን ዳግም ሥራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን ኢዜአ ያነጋገራቸው የዩኒቨርሲቲዎች የሥራ ኃላፊዎች ገልጸዋል።

ተቋማቱን ሥራ ለማስጀመር ከትምህርት ሚኒስቴር ፈቃድ በተጨማሪ ለመማር ማስተማር አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ለማሟላት በጀት ሊመደብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በመሆኑም ሁሉም አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉና እንዲተባበሩ የዩኒቨርሲቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮቹ ጥሪ አቅርበዋል።
265 viewsedited  17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 18:45:22
#Amhara-Tigray
በትግራይ የትምህርት ሁኔታ ለመምከር በሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የተመራ የፌደራል የልዑካን ቡድን መቀሌ ገብቷል።
የመቀሌ ዩንቨርስቲ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ፕሮፈሰር ክንድያና ገብረህይወት የባህርዳር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው፣የደብብርሃን ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ንጉስ ታደሰን ጨምሮ በመቀሌ ተገናኝተው እንዲህ ተቃቅፈዋል።
186 views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 07:46:55 በመቀለ ዩኒቨርሲቲ ተመድበን የነበርን እና በተፈጠረው ሀገራዊ አለመግባባት ምክነያት ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች በጊዜያዊነት ተመድበን ትምህርታችንን መጨረሳችን ይታወቃል። ነገር ግን በሚገርም ሁኔታ ዛሬ ባህርዳር ጥበበ ጊዮን specialized hospital ለመዎዳደር ሄደን እናንተን አይመለከትም ተብለን ሳንመዘገብ ተመለስን  ለሚመለከተው ሰው ብታሳውቅልን?
439 views04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ