2022-08-08 07:09:12
ዋና ዋና ዜናዎች
1፤ልማት ባንክ በተጠናቀቀው በጀት አመት 11 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከሰጠው ብድር ሰበሰበ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተጠናቀቀው 2014 በጀት አመት 10 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ከሰጠው ብድር መሰብሰቡን ጠቅሶ በበጀት ዓመቱ 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ማትረፍ መቻሉን ገልፀዋል። ባንኩ የትግራይ ክልል ፕሮጀክቶችን ሳይጨምር የተበላሸ ብድር ደረጃን ወደ 17 በመቶ ማውረድ መቻሉንም አስታውቋል። በብድር አሰባሰብ ላይ የጀመረውን ስራ በማጠናከር በተያዘው 2015 በጀት አመት 14 ቢሊየን ብር ከብድር ለመሰብሰብ ማቀዱንም ባንኩ ይፋ አድርጓል።
2፤ህብረተሰቡ እውቅና ከሌላቸው ዲጂታል መገበያያ ገንዘቦች እራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ።
በኢትዮጵያ እውቅና የሌለውን ምናባዊ ንብረት ወይም ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ ለመጠቀም ከሚንቀሳቅሱ አካላት ህብረተሰቡ እራሱን መጠበቅ እንዳለበት የፋይናንስ ደሕንነት አገልግሎት አሳስቧል። አገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ባለው የጥቁር ገበያ የሚሳተፉ አካላትን ለይቶ እርምጃ እንዲወሰድባቸው በማድረግ ሂደትም አገልግሎቱ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑም ተገልጿል። በተለይም ‘ቢትኮይን’ እና ‘ክሪፕቶከረንሲ’ የተሰኙ የ’ኦን ላይን’ ዲጂታል ገንዘብ ዝውውሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
3፤እስራኤል በጋዛ በሰነዘረችው ጥቃት የሟቾች ቁጥር 32 ደረሰ።
በየጊዜው ግጭት ውስጥ የሚገቡት እስራኤል እና ፍልስጥም አሁንም መልሰው ግጭት ውስጥ ገብተዋል። የእስራኤል ጦር ባሳለፍነው ሰኞ የእስላሚክ ጅሀድ የተሰኘው ቡድን መሪ የሆኑት ባሳም አልሳዲን በዌስት ባንክ ማሰራቸውን ተከትሎ በጋዛ አውዳሚ ግጭት ተቀስቅሷል። በጋዛ ሰርጥ ውስጥ እየተካሄደ ባለው በዚህ ጦርነት እስራኤል በተኮሰቻቸው የሮኬት ጥቃቶች የሞቱ ሰዎች ቁጥር 32 መድረሱን ሮይተርስ ዘግቧል።
4፤ሩሲያ ለዩክሬን ሲዋጉ የነበሩ የውጭ ቅጥረኛ ወታደሮችን መግደሏን ገለፀች።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በዩክሬን በፈፀመው የአየር ድብደባ በርካታ ቁጥር ያላቸው ለዩክሬን ሲዋጉ የነበሩ የውጭ ሀገራት ቅጥረኛ ወታደሮችን መግደሉን አስታውቋል። የአየር ጥቃቱ ዓለም አቀፍ ተዋጊችን የያዘ የዩክሬን ክፍለ ጦርን ኢላማ ያደረገ እንደነበረም ታውቋል።
በአየር ጥቃቱም ከ80 በላይ የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ቅጥረኛ ወታደሮችን መግደሉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
5፤ማንችስተር ዩናይትድ አመቱን በሽንፈት ጀመረ።
በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ስር የመጀመሪያ የፕርሚየር ሊግ ጨዋታቸውን ማድረግ የቻሉት ማንችስተር ዩናይትዶች በብራይተን 2 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ለብራይተን ፓስካል ግሮስ ሁለቱንም ግቦች ማስቆጠር ሲችል ሌላኛው የብራይተን ተጫዋች ማክ አሊስተር በራሱ መረብ ላይ ለዩናይትድ አስቆጥሯል። አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ክለቡን እንደሚለቅ ሲጠበቅ የነበረውን ፖርቹጋላዊውን ክርስቲያኖ ሮናልዶ በተጠባባቂ ወንበር አስቀምጠው ሲጀምሩ በሁለተኛው አጋማሽ ግን ቀይረው አስገብተውታል።
312 views04:09