Get Mystery Box with random crypto!

#News Alert- ብሄራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የአገሪቱን ወቅታዊ የጸጥታ | አገልግል

#News Alert- ብሄራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የአገሪቱን ወቅታዊ የጸጥታ እና የብሄራዊ ደኅንነት ስጋቶች መገምገሙን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ምክር ቤቱ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ የትግራዩ ጁንታ፣ የሱማሊያው አልሸባብ፣ በኮንትሮባንድ የተሠማሩ አካላት፣ ሕገወጥ ታጣቂዎች፣ ጽንፈኛ መገናኛ ብዙኀን፣ የፖለቲካ ቡድኖች እና አክራሪ ሐይማኖተኞች እንዲሁም የውጭ ጣልቃ ገብነት በአገሪቱ ላይ የደቀኑትን ስጋት መገምገሙን አብራርቷል።

መንግሥት እነዚህን አገራዊ ስጋቶች በሆደ ሰፊነት መያዙ እንደ ድክመት እንደተቆጠረበት ማረጋገጡን የገለጠው ምክር ቤቱ፣ መንግሥት ከእንግዲህ በመገናኛ ብዙኀን፣ ማኅበረሰብ አንቂነት፣ በሐይማኖት እና በፖለቲካ ድርጅት ሽፋን የሚደረጉ አገር የማፍረስ ሴራዎችን መንግሥት አይታገስም ብሏል። ምክር ቤቱ በዚሁ መግለጫው፣ አልሸባብ ከትግራዩ "ጁንታ" እና ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ለመፍጠር የሞከራቸውን ትስስሮችም የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በተሳካ ሁኔታ አክሽፈዋል ብሏል።

ምክር ቤቱ ባለፈው ሚያዝያ ወር ባደረገው ግምገማ ያስቀመጣቸው ግቦች ባብዛኛው እንደተሳኩ ማረጋጠን እና የመንግሥት ሕግ የማስከበር ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጫው አክሎ ገልጧል። ምክር ቤቱ በዚሁ መግለጫው፣ በተለይ በኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና አማራ ክልሎች በርካታ ሕገወጥ ቡድኖች እና ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ፣ ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎች እንደተሰበሰቡ እና በሕገወጥ እንቅስቃሴ የተገኙ የማኅበረሰብ አንቂዎች ሥርዓት እንዲይዙ መደረጉንም አብራርቷል።