Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራዩ ሕወሃት በታንዛኒያ አሩሻ ከተማ ድርድር ሊጀምሩ እንደሚችሉ ከምን | አገልግል

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራዩ ሕወሃት በታንዛኒያ አሩሻ ከተማ ድርድር ሊጀምሩ እንደሚችሉ ከምንጮች መስማቱን ጠቅሶ የፈረንሳዩ ሊ ሞንድ ጋዜጣ ዘግቧል። ጋዜጣው የአፍሪካ እና ምዕራባዊያን አገራት ዲፕሎማቶች የሁለቱ ወገኖች ድርድሩን ከሰኔ ወር ማለቂያ በፊት ሊጀምሩ እንደሚችሉ ነግረውኛል ብሏል። ምዕራባዊያን ዲፕሎማቶች ሕወሃት የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች በሚቆጣጠሩት ወልቃይት ግዛት ላይ ያለውን የይገባኛል ጥያቄ ቀስ በቀስ እየተወው እንደሆነ ጥቆማ መስጠታቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጧል። ከመጋረጃው ጀርባ በሚደረገው ድርድር ከሁለቱ ወገኖች ከእያንዳንዳቸው አምስት አባላት ያሏቸው ተደራዳሪዎች ሊሳተፉበት እንደሚችሉም ዘገባው ጠቅሷል።