Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxslijoch — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxslijoch — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxslijoch
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.17K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ምንማማርበት :መዝሙር: ስብከቶች ይተላለፋል !

መንፈሳዊ ትምህርቶች : መንፈሳዊ ጥያቄዎች : ስብከት : መዝሙር : ይቀርብበታል #ጉዞው ገዳማት #ሰማህታት ታሪክ ይቀርባል!
FacebookGroup : ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ይቀላቀሉ ::

#shear

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-12 06:01:37 የተስፋ ቃላት

እኛ ዛሬ ወደፊት የምንኖርባት #የእግዚአብሔር ሀገር በተስፋ ዓይኖቻችን ልንመለከት እንጂ ይሁን ሁካታና ግርግር የበዛበት ዓለም ልንመለከት አይገባም።

ለእኛ በጣም አስቸጋሪ መስሎ የሚታየን ችግር #በእግዚአብሔር ዘንድ መፍትሔ አሉትም። ማንኛውም የተዘጋ በር ለመክፈት በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ቁልፍ አንድ ብቻ ሳሆን ብዙ ቁልፎች ናቸው። በእንደዚህ ዓይነት መንገድ የተከፈተውን ማንም ሊዘጋው አይችልም ፡፡ ራዕ 3፥7።

ተስፋ ፍርሀትን ጭንቀትን ግራ መጋባትን በመከላከል ዕረፍትን ይሰጣል።ተስፋ ዕረፍትን ከመጠቱ በላይ በተስፋ ደስ እንዲለን ተነግሮናል። ሮሜ 12፡2

መጥፎውን ወደ በጎ መቀየር የሚቻለውን #የእግዚአብሔር አሠራር ሳትይዝ ወደ ችግሮችህ ብቻ አትመልከት።

#እግዚአብሔር ሁሉም አጋጣሚዎች እርሱ በወደድው መንገድ ማስኬድ ይቻለዋል።

በሰዎች ድካም ሊደረግ የማይቻለው ሁሉ #በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ይቻላል። የሰዎች ጥበብ  ሊወጣው ያልቻለውንም #የእግዚአብሔር  ጥበብ ያመጣዋል።

  ምንጊዜም በመለከታዊ ዕርዳታ የተከበብክ ስለሆንህ ብቻህን ላለመሆንህ እርግጠኛ ሁን፡፡
የሰማያት ወዳጆቻችንና ቅዱሳን ሁሉ በአንተ ዙርያ ሁነው ስለ አንተ እንደሚማልዱም እወቅ።

    join @ortodoxslijoch
3.0K views03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 07:20:49 በሕይወትህ በረከት እንዲበዛልህ አመስጋኝ ሁን! ”

          

በሕይወታችን ብዙ ልናሟላቸው የምንፈልጋቸው ነገሮች
ይኖራሉ። ጠቢቡ ሰለሞን በመጽሐፈ መክብብ 1:7 ላይ ሲናገር
" ፈሳሾች ሁሉ ወደ ባሕሩ ይሄዳሉ ባሕሩ ግን አይሞላም "
ይላል።

ይህም ምን ቢሰጠው የትኛውም ያህል ቢትረፈረፍለት
የሰው ልጅ ምኞትና ፍላጎት ማለቂያ የለውምና። እኛም ገንዘብ፤
ስራ፤ ፍቅር፤ ዝና፤ ስልጣን፤ በምኞት ቋጠሯችን ውስጥ
ካካበትናቸው ጥቂቶቹ ናቸው።
መመኘቱ ባልከፋ …..ነገር ግን ብዙዎቻችን የሌለንን ስንመለከት
ያሉንን ነገሮች ዓይን እንነፍጋቸዋለን ስለዚህ መጠየቅ እንጂ
ማመስገን ይሳነናል፤ በዚህም ሁልግዜ ጠያቂዎች እንጂ
አመስጋኞች አይደለንም። ልብ በሉ ምኞቶቻችን ሁሉ ሊሳኩ
የሚችሉት ባለን ነገሮች መጀመሪያ መደሰት እና ማመስገን
ስንጀምር ነው።

ለምሳሌ፦ አንድ ወዳጃችን በችግራችን ደርሶ ረዳን እንበል፤
ላደረገልን እርዳታ ምስጋና ካልሰጠነው እንዴት ብሎ በሌላ
ችግራችን ይደርስልናል?፤ አምላካችን እግዚአብሔርም
ላደረገልን ነገር ባመሰገንነው ቁጥር ሌሎች ልመናችንን ሰምቶ
በበረከት ላይ በረከት ያትረፈርፍልናል።

ስለዚህ ሁልግዜ
አመስጋኝ አንደበት ሊኖረን ይገባል።
ነገር ግን በምስጋና ፈንታ “በቂ ገንዘብ አላገኝም”፤ “ኑሮዬ
ምስቅልቅሉ የወጣ ነው” ፤ “መልካም የትዳር አጋር
አላገኘሁም”፤ “ስኬታማ አይደለሁም” " እግዚአብሔር
አይሰማኝም" የምንልና የምንማረር ከሆነ ያለንን ነገሮች
እንዳናይ ከማድረጋቸውም በላይ በረከታችንን የማራቅና ያለንም
በረከት ልናጣና ልንነጠቅ እንችላለን።
ብዙዎቻችን ግን ይህንን አንረዳም።

ለደቂቃ ልቦናችንን ሰብስበን
ካስተዋልነው እያንዳንዶቻችን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን
እንኳን፤ ልናመሰግን የምንችልበት ብዙ ምክንያቶች አሉን።

እንደው ዋጋቸውን እያራከስን ነው እንጂ እያንዳንዶቻችን ሌሎች
የሚመኟቸው ነገሮች እኛ ጋር ዋጋ አጥተው ተቀምጠዋል።

ለምሳሌ፦ የአልጋ ቁራኛ የሆነ ሰው በህይወቱ የሚመኘው ነገር
ሙሉ ጤንነትን ሆኖ ሳለ፤ ጤነኛው ሰው ግን ስላለው ጤና
አለማመስገኑ አይገርምም?
ካስተዋልነው አንዲት ቃል ህይወታችንን በርግጥም

ትለውጣለች….. ለጠቢብ ሰው አንዲት ቃል ይበቃዋል ይባል
የለ በማቴዎስ ወንጌል 25:29 “ ላለው ሁሉ ይሰጠዋል
ይበዛለትማል…. ለሌለው ግን ያው ያለውም እንኳን
ይወሰድበታል” የሚለው ቃል የሚያስረዳን ሁላችንም ለተሰጠን
ማንኛውም መክሊት መጀመሪያ ምስጋና እናቅርብ ያኔ…ሌሎች
በረከቶቻችንን፣ ይመጣሉ።
እግዚአብሔርንም ስለሰጠን ነገር ሁሉ ካመሰገንነው ባለን ላይ
ሁሉ ለመጨመር አያመነታም ።

                    ሼር

      Join @ortodoxslijoch
4.3K views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 21:32:22 ግንቦት 1

"የብርሃናት ንጉሥ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ ዛሬ የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ተወለደች። ከሊባኖስ ተራሮች ርግብ ጸዐዳ ተወለደች፤ በሔዋን ምክንያት የተዘጋው የሕይወት መንገድ ይከፈትልን ዘንድ የሕይወት እናት ዛሬ ተወለደች፡፡ የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመብርሃን ዛሬ ተወለደች፡፡

ኢያቄምና ሐና ዳግሚት ሰማይ ተብላ የተጠራችውን ድንግልን ወለዱ፤ እውነተኛው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመ ፀሐይ (የፀሐይ እናት) ቅድስት ድንግል ዛሬ ተወለደች፤ ብርሃንን ለማስገኘት መወለድ መታደል ነው፤ ከሰው ልጆችም መካከል መመረጥ ዕፁብ ድንቅ ነው፤ የመድኃኔዓለም እናት ለመሆን መወለድ ሰማያዊ ፀጋ ነው።

በእውነት እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት። ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን እመብርሃን ዛሬ ተወልዳልናለችና ደስ ይበለን እልልም እንበል።"

የአለሙን ሁሉ መድኃኒት ለወለደች ለብርሃናት ጌታ እናት በቀራንዮ በመስቀሉ ስር እናት ትሆነን ዘንድ ለተሠጠችን ለመመኪያችን ዘውድ ለተወዳጇ ለቅድስተ ቅዱሳን እናታችን ልደት በዓል እንኳን አደረሰን

    Join @ortodoxslijoch
6.8K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 06:26:13 #እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" #ልደታ ለማርያም ድንግል "*+

#ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ:
ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ::

" ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን:
ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) "

=>የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኩዋ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን::

+ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል::

+እመቤታችን ከአዳም ስሕተት በሁዋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: (ኢሳ. 1:9)

+ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ቀን: በሊባኖስ ተራራ ከ2,022 ዓመታት በፊት ተወልዳለች::

"ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ" (መኃልይ. 4:8)

=>ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች ልጅ የላችሁም በሚል ይናቁ ነበር::

+ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ::
እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም::

+የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች::

+ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን 2ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ::

+እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::

+በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::

+እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች::
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . .
ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም)

+"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ."
"ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9)

+እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች::

=>የእመቤታችን የዘር ሐረግ:-
*አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ=
*በእናቷ:-
-ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና::
*በአባቷ በኩል:-
-ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል::

+ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች::

=>የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን::

=>ግንቦት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን

=>+"+ መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው::
ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል::
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . .
ሰው እናታችን ጽዮን ይላል::
በውስጧም ሰው ተወለደ::
እርሱም ራሱ ልዑል መሠረታት:: +"+ (መዝ. 86:1-6)

<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ  ከፍ አድርጋቸው/
7.1K views03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 09:09:50 ሚያዚያ 23/8/2015 # ቅዱስ_ጊዮርጊስ

ለሰማዕቱ # ቅዱስ_ጊዮርጊስ አመታዊ የእረፍት መታሠቢያ ክብረ በዓል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን
ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቱ የፍልስጤም መኮንን ዞሮንቶስ (እንስጣቴዎስ) እናቱ ደግሞ (አቅሌሲያ) ቴዎብስታ ትባላለች በፍልስጤም ልዳ ጥር 20 በ277 ዓ.ም ተወለደ ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ ብሩህ ሀረገ ወይን ፀሐይ ዘልዳ ማለት ነው

ቅዱስ ጊዮርጊሰ በፋርስ በኢራን ዱድያኖስ የተባለ ንጉሥ ነገስታቱን ሰብስቦ ሰባ ጣኦታትን ሲያሰግድ ተመለከተ በዚህን ጊዜም ቤተ መንግስት ድረስ በመገስገሰሰ ተቃውሞውን በማሰማት ክርስቲያን መሆኑን መስክሯል ከዚህም በኋላ በተለያዩ ነገስታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰው ህሊና ሊታሰቡ የማይቻላቸው አስራ ዘጠኝ መከራዎች ደርሰውበታል ቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስት ጊዜ ሞቶ ሶስት ጊዜ ተነስቷል የእግዚአብሔር ተአምር በተደጋጋሚ ተገልፆለታል

የቅዱስ ጊዮርጊስ መከራ በጥቂቱ፦ክርስቲያን በመሆኑ ብቻ ወደ እስር ቤት ተወረወረ፤እጆቹና እግሮቹ ታስሮ ተገረፈ ፤የብረት ጫማ አጥልቀው አስኬዱት፤ከብረት አልጋ ላይ አስተኝተው እሳት አነደዱበት፤እጆቹን የኋሊት አሰሩት፤በመጋዝ ለሁለት ሰነጠቁት

የጋለ ሳህን ከጭንቅላቱ ላይ አስቀመጡበት፤ሰውነቱን በጩቤ ፈተፈቱት፤ችቦ እና እሳት አንድደው በግራና በቀኝ አቃጠሉት
ምላሱን በቢላዋ ቆረጡት፤በአፍንጫው ቀዳዳዎች በሚስማር መተው ቸነከሩት፤በመጥረቢያ ፈለጡት፤ቅጥራን አፍልተው በጭንቅላቱ ላይ ደፉበት፤በበሬ አስረው ጎተቱት፤ጥርሶቹን በጉጥ አስረው ነቃቀሉት፤ከብረት ድስት ውስጥ ጨምረው ቀቀሉት፤አስጎንብሰው አሸዋ ጫኑበት፤ከእንጨት ላይ አንጠልጥለው በእሳት አጋዩት፤በወፍጮ ፈጩት

በዚህ እለት ደሞ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስለ ቤተ ክርስቲያን ፍቅር ሲል በሰይፍ ተቀልቶ በመንኮራኩር ተፈጭቶ ወደ እቶን እሳት ተወርውሮ ለአእምሮ በሚከብድ መልኩ ብዙ መከራን ተቀብሎ በ 27 አመቱ ሚያዚያ 23 ቀን መከራን ተቀብሎ በሰማዕትነት አርፏል

እግዚአብሔር ሰማዕታትን በደም ቅዱሳንን በተጋድሎ ያፀናል አምላክ እኛንም በሀይማኖት በምግባር እንድንፀና የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን "አሜን"
4.0K views06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 06:52:38 “መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” ምሳ. 31፡29

ክርስቶስን ያከበሩ፤ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ እውነትን የመሰከሩ፤ ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፤ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ታላላቅ የምድር ነገስታትን፤ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ከነዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ፡፡

ቅድስት ድንግል ሆይ አንቺ እኮ፡- ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ፤ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የሰላም አለቃ፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ ከሆነውም አንዳችም እንኳን ያለርሱ ያልሆነ፤ ዓለምን ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የመለሰ፤ መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚንቀጠቀጡለት፤ የሁሉ ፈጣሪ፤ የሁሉ አምላክ እናት ነሽ፡፡

በፊትም አሁንም ወደፊትም ካንቺ በቀር ፈጣሪዋን ልጄ ብላ የምትጠራ ሴት አልነበረችም፤ የለችም፤ አትኖርምም ክርስቶስም እናቴ ብሎ የሚጠራት ብቸኛዋ ሴት አንቺ ነሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡

እናት ስትሆኝ ድንግል፤ ድንግል ስትሆኝ እናት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ብሎ የሚጠራሽ ብቸኛዋ ሴት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡

እግዚአብሔር መርጦና ጠብቆ ያስቀረሽ ዘር በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ ለዓለም ሁሉ ድህነት ምልክት የሆንሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡

እናቴ ሆይ እንግዲህ እኔ ምን ልናገር? ሺህ ቃላትን ብደረድር ያንቺን ክብር ልገልፀውስ እንደምን እችላለው? አዎ አሁንም እላለሁ “መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” ምሳ. 31፡29

የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር፤ ምልጃ ቃል ኪዳኗ ይጠብቀን፡፡ አሜን!!!

      Join @ortodoxslijoch
2.6K views03:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 06:04:44 #እኔ_በእግዚአብሔር_ፊት_የምቆመው_ገብርኤል_ነኝ (ሉቃ 1፥19)
#ይህ_ገብርኤል_ነው
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤ የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ዳንኤልን ከአነብስት ያዳነው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ወደ ዘካሪያስ የተላከ የዮሐንስ ልደት ያበሰረ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ቂርቆስና ኤናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ሰብአ ሰገልነረ በኮከብ ምልክት የመራቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ድንግል ማርያሜና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
የብርሃን ወርቅ የተቀዳጀ
#ገብርኤል_ነወ ።
የአሸናፊና የኀኃይል መልአክ
#ገብርኤል_ነው ።
ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ
#ገብርኤል_ነው ።
#የመልአኩ_የቅዱስ_ገብርኤል_ጥበቃና_ረድኤት_አይለየን
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
      Join @ortodoxslijoch
1.8K views03:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 05:24:27 ከሰዎች ጋር በሰላም ለመኖር የሚረዱህ ምክሮች
─ ─━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─ ─
ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።

“ሁለተኛይቱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።”
(ማርቆስ 12፥31)

ለመስማት እንጂ ለመናገር አትፍጠን፡፡
“ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤”
(ያዕ.1:19)

ይቅር ስትል ቂም አትያዝ፡፡
"እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ፤ በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት።"
(ቆላስይስ 3፡13-14)

በሁሉም ነገር ትዕግሥተኛ ሁን።
“ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤”
(1ኛ ቆሮንቶስ 13፥4)

ሳትሰስት ሰጥ።
“ኀጥእ ቀኑን ሁሉ ምኞትን ይመኛል፤ ጻድቅ ግን ይሰጣል፥ አይሰስትም።”
(ምሳሌ 21፥26)

የሰው ንግግር ሳታቋርጥ አዳምጥ።
“ሳይሰማ ነገርን በሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል።”
(ምሳሌ 18፥13)

መልስ ስትመልስ አትከራከር።
“ጥል ባለበት ዘንድ እርድ ከሞላበት ቤት በጸጥታ ደረቅ ቍራሽ ይሻላል።”
(ምሳሌ 17: 1)

የገባኽውን ቃል ጠብቅ፡፡
“የምትዘገይ ተስፋ ልብን ታሳዝናለች፤ የተገኘች ፈቃድ ግን የሕይወት ዛፍ ናት።”
(ምሳሌ 13፥12)

ሰውን ስታምን ካለመጠራጠር ይሁን፡፡
ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።”
(1ኛ ቆሮንቶስ 13፥7)

ሰዎች ላይ ክፉ አታስብ።
“በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤”
(ፊልጵስዩስ 2፥14-15)

ይቅር መባባልን ሁሌም አትዘንጋ።
መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።
(ኤፌሶን 4:31-32)
•••
☞ 🅢🅗🅐🅡🅔
        Join @ortodoxslijoch
2.2K views02:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 07:16:05 ◦ ዳግማይ_ትንሳኤ ማለት ዳግም መነሳት (ሁለተኛ መነሳት) ማለት ነው ።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤቶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ #ዳግማይ_ትንሳኤ ተብሏል ።
ሁለተኛ_ለምን_ተገለጠ?
◦ ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን ።
የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጉኔን ዳስስ ብሎታል ።

ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑ በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል ።ሃገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው ።ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች (የዳሰሰች)እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች ።እስካሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ ።
◦ሰንበትን ሊያጸናልን ።

የአይሁድ ሰንበት፣እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም(ቅዳሜ)ናት ።በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት ፣ከሙታን መካከል የተነሳባት፣አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት(ዳግማይ ትንሳኤ)፣መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች ።ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች ።ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት ።እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን)የምናሳልፈው ማለት አይደለም ።እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው እንጂ ።

◦ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት ፣ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል ።በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው ።
"ብጹዓን እለ እንዘ ኢይሬእዩ የአምኑ"
(ዮሐ20:29)

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን
     Join @ortodoxslijoch
2.2K views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 11:42:35 #አስርቱ_ትዕዛዛት እና #ስድስቱ #ቃላተ- #ወንጌል

1/ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ አይኑርህ። (ዘፀ 20÷1_6)
2/ የ አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ። ( ዘፀ 20÷7)
3/ በባልንጀራህ ላይ በሀሰት አትመስክር። (ዘፀ 20÷8)
4/ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ። ( ዘፀ 20 ÷12)
5 / አባትና እናትህን አክብር። (ዘፀ 20÷13)
6/ አትግደል። (ዘፀ 20÷4)
7 / አታመንዝር። (ዘፀ 20÷15)
8/ አትስረቅ። (ዘፀ 20÷16)
9/ ባልንጀራህን እንደ እራስህ ውደድ። ( ዘፀ 20÷17)
10/ የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ። ( ዘለዌ 19÷18)
    
     ስድስቱ ቃላተ-ወንጌል

1/ ለተራበ ማብላት፣ ማቴ( 25÷35)
2 /የተጠማ ማጠጣት፣ ማቴ(25 ÷3)
3 / እንግዳ መቀበል፣ ማቴ( 25 ÷ 35)
4 / የታረዘ ማልበስ፣ ማቴ ( 25_ 35)
/የታመመን ማየት፣ ማቴ( 25÷36)6/ የታሰረ መጠየቅ፣ ማቴ(25÷36)

        ስድስቱ ህግጋተ-ወንጌል

1/ በወንድምህ ላይ በከንቱ አትቆጣ። (ማቴ 5÷22_17
2/ ወደ ሴት አትመልከት በልብህም አታመንዝር። ( ማቴ5÷27)
/ ሚስትህን ካለ ዝሙት ምክንያት አትፍታ። ( ማቴ 5÷32)
4/ ፈፅመህ አትማል። ማቴ (5_÷34)
5/ ክፉን በክፉ አትመልስ። (ማቴ_ 5÷39)
6 / ጠላትህን ውደድ። ማቴ(5÷45) እግዚአብሔር የህጎቹ ጠባቂ ያድርገን፣
ቃሉ ወራሽ ከሳሽ እንዳይሆንብን በልቦናችን ፅላት ያሳድርልን አሜን።
        Join @ortodoxslijoch
1.2K views08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ