Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxslijoch — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxslijoch — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxslijoch
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.17K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ምንማማርበት :መዝሙር: ስብከቶች ይተላለፋል !

መንፈሳዊ ትምህርቶች : መንፈሳዊ ጥያቄዎች : ስብከት : መዝሙር : ይቀርብበታል #ጉዞው ገዳማት #ሰማህታት ታሪክ ይቀርባል!
FacebookGroup : ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ይቀላቀሉ ::

#shear

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 26

2022-07-05 14:16:09 "ከሞት ወዲያ መብራት አለ ።
ከመቃብር በላይ ብርሃን አለ ።"

ታላቁ ሊቅ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል … ‹ሰው እግዚአብሔር ሲለየው፤ ጠባዩ እንደ አራዊት፤ አመጋገቡ እንደ እንስሳ፣ ሆኖ መልኩ ብቻ የእግዚአብሔር ሆኖ ይቀራል›።

በጣም ቀለል ባለ አገላለጽ ሲም ካርዱ የወጣ ሞባይል ማለት ነው። ጥሪ የማይቀበል…....እኔ በዕውነቱ ከተማው ፈርሶ እየተሰራ ነው እየተባለ ዐይናማዎቹ ሲያወሩም ሲያስወሩም እሰማለው። ፈርሶ መሰራት ያለበት ግን የሰዉ አስተሳሰብ ነው።... የሰዉ አስተሳሰብ ፈርሶ ካልተሰራ፤ የተሰራ ከተማ ይፈርሳል። ጃፓንና ቻይና ሀገራቸውን ያለሙት መጀመሪያ አስተሳሰባቸውን አልምተው ነው።

ቤታችሁ ገብታችሁ እንድታጤኑት ነው  እንደምታዩኝ እኔ ዐይነ ስውር ነኝ። ቀላል አይደለም.... እንክዋን ዘውትር ዓይን አጥቶ አንድ ቀን መብራት ሲሄድ ስንት እንደምታማርሩ ታውቅታላችሁ።

እኔ ግን ዓይኔ ባለማየቱ አንድ ቀን እንኳን አልቅሼ አላውቅም። ከሞት ወዲያ መብራት አለ። ከመቃብር በላይ መብራት አለ።
 
ወደ መቃብር ሲወርድ ማንም ዓይነ ስውር ነው። ማንም ዐይኑ እያየ የተቀበረ የለም።

ተስፋችን ግን ምንድን ነው?

ከሞት ወዲያ ሕይወት አለ። ከሞት ወዲያ ብርሃን አለ...

አንድ አንድ ጊዜ እመኛለሁ የማይረባ ነገር ስናይ (ዓይናችንን) የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር... መልካም ነገር እስክናይ ድረስ ለጊዜው የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር።

አሁን እንደው ጆሮ በካርድ የሚሰራ ቢሆን ሐሜት እንሰማ ነበር? የምንፈልገውን (ብቻ) አውርተን ስዊች ኦፍ እናደርገው ነበር። ችግሩ ብዙ ነው፡፡ ስንት ዞማ ጸጉር ይዞ አስተሳሰቡ የከረደደ አለ።

እባካችሁ ሰው እንሁን… የንጉሠ ነገሥቱ የክርስቶስ አልጋ ወራሾች ነን... የደስታችሁ ልኬት የደስታችሁ ሚዛን ምግብና መጠጥ አይሁን፤ መኪናና ቤት ዝናንም አታርጉ።

እኛ መለኪያችን ጽድቅ ነው።
መከኪያችን መንግሥተ ሰማያት ነው።
ያ የምንገባበት ቤት ደግም የተዋበ፣ የደመቀ፣ መብራት ውሀ የማይሄድበት፤ 24 ሰዓት ክርስቶስ የሚያበራበት፤ 24 ሰዓት የሕይወት ውሀ የሚጠጣበት፤ ሀብታም፤ ደሀ፣ ተራ ሰው የማይባልበት፣ እገሌ ግባ እገሌ ውጣ የማይባልበት ቦታ
ነው።

ሁላችንንም የመንግስቱ ወራሽ ያድርገን ፣ አሜን።

በመጋቤ ሐዲስ እሸቱ
   join @ortodoxslijoch
6.8K views11:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 20:14:13
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቀም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው።

ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።

በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ - መንፈሳዊው መንገድ መጽሐፍ አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)

የሕይወት ፡ እናቱ ፡ ሆይ፤ ተቀዳሚ ፡ ተከታይ ፡ በሌለው ፡ በአንድ ፡ ልጅሽና ፡ በእኛ ፡ መካከል ፡ አስታርቂን።

Join @ortodoxslijoch
6.1K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 17:06:51 #መድሃኒአለም ማለት የአለም ሁሉ መድሃኒት ማለት ነዉ
ስጋዉን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ለኛ ሲል ህይወቱን የሰጠ

፨ አሮንና ልጆቹን ....... ለክህነት የመረጠ
፨ ኤልያስን ....... በአዉሎ ነፋስ የነጠቀ
፨ እዮብን ....... በባእድ ሀገር ከፍ ከፍ ያደረገ
፨ ሎጥን ........ ከእሳት ያወጣ
፨ ለሳምሶን ........ ሀይልን የሰጠ
፨ አዛርያን አናንያን ሚሳኤልን ....... ከእሳት የታደገ
፨ ጥበብና ማስተዋልን ....... ለሰለሞን የሰጠ
፨ ያዕቆብን ....... በመንገዱ የጠበቀ እና የባረከ
፨ እስራኤልን ....... ከግብፅ ባርነት ያወጣ
፨ ለሙሴ ....... ጽላት የሰጠ
ለኪሩቤል ላይ የተቀመጠ ክብሩንም የገለጠ ስጦታዉ የማያልቅበት

#ቸሩ_መድሃኒአለም_ይክበር
_ይመስገን_አሜን /፫/
#መድኃኒአለም _የገዢዎች ሁሉ ገዢ
#መድኃኒአለም ____ የነገስታት ሁሉ ንጉስ
#መድኃኒአለም ____ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ ነዉ
ኃይሌን ጉልበቴን ታድሳለህ
ቀና ቀና እንድል ታደርጋለህ
መድኃኒአለም መድኃኒቴ

መ ____ መሃሪ ይቅር ባይ አምላክ
ድ ____ ድካሜን ተመልከት ስለዉ ተበርክኬ
ኃ ____ ኃያላት የማይችሉህ የኃያላን ኃያል
ነ ____ ነፍሴ ትልኃለች ጌታዬ ይረዳኛል
አ ____ አለምን ለማዳን መስቀል ላይ የዋለ
ለ ____ ለዘላለም ፍቅር ነህ ሁሌ የማትቀየር
ም ____ ምህረትህ የበዛ
#የድንግል_ማርያም_ልጅ_ቸሩ_መድኃኒአለም_አንተ_ነ
ህ_አባቴ !!

ቸሩ መድኃኒአለም በያላቹሁበት ይጠብቃችሁ ወጥቶ ከመቅረት ከድንገተኛ አደጋ ይጠብቃችሁ አሜን/፫/
የሚያኖረን ሰዉ ሳይሆን የአለም መድኃኒት የሆነዉ ለእኛ ሲል የእሾህ አክሊል የደፈዉ ቸሩ መድኃኒአለም ነዉ።
ቸሩ መድኃኒአለም ሃገራችን ይጠብቅልን
የዲያብሌስ ስራ እጅግ ተስፋፍቶብን
የሰዉኛ ዘይቤዉ ከእኛ ዘንድ ጠፍቶብን
ምግባራችን ከፍቶ ትዛዝህን ሽረን
..... በበደል ጨቂተን

ዉስጣችን ሲያነባ ካንተ ተሰዉረን
ለሰዉ ልጅ ነዉና ደምህ የፈሰሰዉ
በምህረት እጆችህ እንባችን አብሰዉ
ምስጋና ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ጥንት ለነበረ አሁንም ላለ ኋላም የሚኖር ስሙ የተመሰገን ይሁን አሜን

Join @ortodoxslijoch
7.5K views14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 08:07:56 #እንኳን_ለአቡነ_ተክለሀይማኖት_መታስቢያ_ከብር_በአል አድርሳችሁ አድርስን አሜን ፫
#የጻድቁ_መታስቢያ_ለበርከት_ነው_የሀጣን_ስም_ግን ይጠፍሉ ምሳ 10:7 በስማይ የሚኖሩ ጻድቃን ባንድ ቃል ሆነው ተባብርው ያመስግናሉ ለስሙም ፈፀመው ይለምናሉ
መ"ሄኖክ 12:34ነብየን በነብይ ስም የሚቀበል የነብይ ዋጋ ይወስዳል
#ጻድቃንም_በጻድቃን ስም የሚቀበሉ የጻድቃን ዋጋ ይወስዳሉ ማቴ 10:41 ጻድቅ እንድ ዘንባባ ያፍራል እንድ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል መዝ 92;12 #ስለ ቃሉ የልኡል የቃሉ ባለቤት ልኡል #እግዚአብሔር ከአፅናፍ አለም እስከ አፅናፍ አለም #የተመስገነ ይሁን አሜን፫
#የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ረድኤት በርከታችው ይድርብን ፀሎታችውና አማላጅነታችው አይለየን አሜን፫

Join @ortodoxslijoch
7.6K views05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 19:18:54 ​​​​ሰኔ 21 ለሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#ሰኔ_20_እና_21

ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።

ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ።

ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር።

ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።

የእምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች።

ከበዓሉ ያሳትፈን የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን!

Join @ortodoxslijoch
11.8K views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 07:14:08 #እኔ_በእግዚአብሔር_ፊት_የምቆመው_ገብርኤል_ነኝ (ሉቃ 1፥19)
#ይህ_ገብርኤል_ነው
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤ የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ዳንኤልን ከአነብስት ያዳነው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ወደ ዘካሪያስ የተላከ የዮሐንስ ልደት ያበሰረ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ቂርቆስና ኤናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ሰብአ ሰገልነረ በኮከብ ምልክት የመራቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ድንግል ማርያሜና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
የብርሃን ወርቅ የተቀዳጀ
#ገብርኤል_ነወ ።
የአሸናፊና የኀኃይል መልአክ
#ገብርኤል_ነው ።
ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ
#ገብርኤል_ነው ።
#የመልአኩ_የቅዱስ_ገብርኤል_ጥበቃና_ረድኤት_አይለየን
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
Join @ortodoxslijoch
9.9K views04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 11:09:19 ኪዳነ ምህረት

ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃልኪዳን ማለት ነው፡፡በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው፡፡


እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ ክርስቶስ መካነ መቃብር ጎለጎታ እየወረደች ትፀልይ ነበር፡፡ ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችው ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ የምህረት ቃል ኪዳን ገባለት ፡፡


እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ፣ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ ቃልኪዳን አደረገ፡፡
« ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ። … » መዝ, 89 : 3 እንዲል መፅሐፉ፡፡

ስሟን ለሚጠሩ፣ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት ቃልኪዳን ሰጥቷታል ፡፡

ታላቁ መፅሐፍ እንዲህ ይላል፦
". . . ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ። " ኦሪት ዘፍ. 9 : 16

በዚህም መሠረት ቃልኪዳኗን ምክንያት በማድረግ ኪዳነ-ምህረት እያልን እንጠራታለ

እንኳን ለ«ኪዳነምህረት» አደረሳችሁ። የእመቤታችን ምህረት እና ረድዔት፤በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!!!
@ortodoxslijoch
@ortodoxslijoch
9.1K views08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 12:11:09 የተስፋ ቃላት

እኛ ዛሬ ወደፊት የምንኖርባት #የእግዚአብሔር ሀገር በተስፋ ዓይኖቻችን ልንመለከት እንጂ ይሁን ሁካታና ግርግር የበዛበት ዓለም ልንመለከት አይገባም።

ለእኛ በጣም አስቸጋሪ መስሎ የሚታየን ችግር #በእግዚአብሔር ዘንድ መፍትሔ አሉትም። ማንኛውም የተዘጋ በር ለመክፈት በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ቁልፍ አንድ ብቻ ሳሆን ብዙ ቁልፎች ናቸው። በእንደዚህ ዓይነት መንገድ የተከፈተውን ማንም ሊዘጋው አይችልም ፡፡ ራዕ 3፥7።

ተስፋ ፍርሀትን ጭንቀትን ግራ መጋባትን በመከላከል ዕረፍትን ይሰጣል።ተስፋ ዕረፍትን ከመጠቱ በላይ በተስፋ ደስ እንዲለን ተነግሮናል። ሮሜ 12፡2

መጥፎውን ወደ በጎ መቀየር የሚቻለውን #የእግዚአብሔር አሠራር ሳትይዝ ወደ ችግሮችህ ብቻ አትመልከት።

#እግዚአብሔር ሁሉም አጋጣሚዎች እርሱ በወደድው መንገድ ማስኬድ ይቻለዋል።

በሰዎች ድካም ሊደረግ የማይቻለው ሁሉ #በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ይቻላል። የሰዎች ጥበብ ሊወጣው ያልቻለውንም #የእግዚአብሔር ጥበብ ያመጣዋል።

ምንጊዜም በመለከታዊ ዕርዳታ የተከበብክ ስለሆንህ ብቻህን ላለመሆንህ እርግጠኛ ሁን፡፡
የሰማያት ወዳጆቻችንና ቅዱሳን ሁሉ በአንተ ዙርያ ሁነው ስለ አንተ እንደሚማልዱም እወቅ።

join @ortodoxslijoch
8.0K viewsedited  09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 14:26:31 "ሰው ባልመረጠው ዘሩ ተመርጦ እንዴት ይገደላል?"

"ኢትዮጵያዊ የተራበ ወገኑን ስብስቦ ሲያበላ እንጂ፣ ስብስቦ ሲበላ ታይቶ አይታወቅም።እንዴት ሰው በገንዛ አገሩ ላይ ወጥቶ ለመግባት ዋስትና ያጣል??እንዴት በራሱ ወንድም ይታረዳል?? እንዴት ሰው ፈልጎና መርጦ ባልተወለደው፣በዘሩ ምክንያት የጅምላ ጭፍጨፋ ይደረግበታል??

ኸረ ለመሆኑ እንዴት ብንከፋ ነው ባልኖርንበት ዘመን የኃሊት ሄደን የምንቀየመው???ቆይ ግን መቼ ነው?ይሄ ነገር የሚያበቃው??ማነውስ ለሰው ልጅ የመኖር ዋስትና የሚሰጠው?? እስከመቼስ ነው አንዱ አሳዳጅ ሌላው ተሳዳጅ ፣ አንዱ ታራጅ ሌላው ግን አራጅ ሆኖ የሚቀጥለው??

በእውነት ፍትህን ከመንግሥት ፍርድን ከእግዚአብሔር እንጠብቃለን።የምድር ነገሥታት አይተው ዝም ቢሉ።አይቶ ዝም የማይለው በግፍ የፈሰሰውን የናቡቴን ደም የተበቀለ እግዚአብሔር፣ከሳሽ እንኳን ባይኖር ለራሱ ከሶ ለራሱ መፍረዱ አቀርም።"

Join @ortodoxslijoch
7.5K views11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 06:29:48 ​​​​ሰኔ 12 #የቅዱስ_ሚካኤል ዓመታዊ በዓል!

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ እጅ ያዳነበት ፣ እናታችን ቅድስት አፎሚያ እረፍቷ ነው ።እግዚአብሔር ከቅዱሱ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ፣ ከእናታችን ቅድስት አፎሚያ በረከት ተካፋይ ያድርገን ።

በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራ የአስተራኒቆስ ሚስት የሆነች የቅድስት አፎምያን ታሪክ በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡

ቅድስት አፎምያ በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል፡፡

ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡

ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡

ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡

በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡

ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና “የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡

ለጊዜው “በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ድረስልኝ” እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡

ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ ምንም እንኳን ኃጢአት ባይሆንባትም በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ፡፡

ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው በጽናት ተጋድላ ነው፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በጸሎቷ ይማረን፤ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
Join @ortodoxslijoch
14.7K views03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ