Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxslijoch — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxslijoch — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxslijoch
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.17K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ምንማማርበት :መዝሙር: ስብከቶች ይተላለፋል !

መንፈሳዊ ትምህርቶች : መንፈሳዊ ጥያቄዎች : ስብከት : መዝሙር : ይቀርብበታል #ጉዞው ገዳማት #ሰማህታት ታሪክ ይቀርባል!
FacebookGroup : ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ይቀላቀሉ ::

#shear

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 27

2022-06-16 07:11:31
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቀም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው።

ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።

በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ - መንፈሳዊው መንገድ መጽሐፍ አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)

የሕይወት ፡ እናቱ ፡ ሆይ፤ ተቀዳሚ ፡ ተከታይ ፡ በሌለው ፡ በአንድ ፡ ልጅሽና ፡ በእኛ ፡ መካከል ፡ አስታርቂን።

Join @ortodoxslijoch
9.1K views04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 07:55:33 #ምንም__የለኝም_ደሃ_ነኝ_አትበሉ !
፦አንብቡት
---------------------
፨አንድ ደሃ ወደ አንድ ገዳም ሄዶ በዚያ ያገኛቸውን መነኩሴ አባት ለምን በጣም ደሃ ሆንኩ ብሎ? ጠየቃቸው።

እሳቸውም የምትሰጠው ብዙ አለህ እኮ ግን አላወቅከውምን? ብለው በጥያቄ መለሱለት። ደሃውም የምሰጠው ምንም ነገር የለኝም አላቸው። እኚህ አባትም ከማንም የማያንስ የምትሰጠው ብዙ ነገር አለህ ተመልከት፦

#ፊትህ፦ ይስቃል፥ ይደሰታል ለደስተኞች ፈገግታህን ትሰጣለህ ታካፍላለህ!
#አፍህ፦ ውብ የሆኑ ቃላትን ትናገርበታለህ፥ ታመሰግንበታለህ፥ ሰዎችን ታበረታታለህ፥ ትመክራለህ፥ ታፅናናበታለህ!!
#ልብህ፦ ለመልካምነት ፥ ለእውነትና እና ለትህትናን ልብህ ክፍት ነው!

#ዓይንህ፦ ዓይንህ ጎስቋላና ችግረኞችን በፍቅርና በደግነት ትመለከታለች!! በሀዘን ለተዋጠው ዕንባን ትሰጣለች!
#ሰውነትህ ፦ አቅም ያነሳቸውንና ጉልበት የሌላቸውን ታግዛቸዋለች።
ተመልከት ይሄን ሁሉ መስጠት ከቻልክ አንተ ደሃ አይደለህም..!!

#ተወዳጆች ያለንን ብናውቅ እግዚአብሔር ያስቀረብን አንዳች የለም ከሁሉም በላይ አንድያ ልጁን ሰጥቷል ከዚህ በላይ ደግነት የለም!! ስለዚህ እናንተ ደሃ አይደላችሁም እግዚአብሔር ያላችሁ ባለጠጎች እንጂ!

፨ እውነት ነው አምላኬ ሆይ ለኔ የሰጠህኝ እጅግ ብዙ ነውና በጣም አድርጌ አመሰግንሀለሁ
ክብርና ምስጋና አምልኮና ውዳሴ ለአንተ ለሀያሉ ለልዑል እግዚአብሔር ይሁን አሜን
የአብ ፀጋ
የወልድ ፍቅር
የመንፍስ ቅዱስ ህብርትና ቸርነት ከሁላችንም ጋር ይሁን

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የመላእክት ተራዳኤነት የቅዱሳን በርከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን
Join @ortodoxslijoch
9.0K views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ