Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxslijoch — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxslijoch — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxslijoch
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.17K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ምንማማርበት :መዝሙር: ስብከቶች ይተላለፋል !

መንፈሳዊ ትምህርቶች : መንፈሳዊ ጥያቄዎች : ስብከት : መዝሙር : ይቀርብበታል #ጉዞው ገዳማት #ሰማህታት ታሪክ ይቀርባል!
FacebookGroup : ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ይቀላቀሉ ::

#shear

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 22

2022-09-11 06:13:09 እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመን ሉቃስ
በሰላም አሸጋገረን
2015
ዘረኝነት----የሚጠፋበት
የተራበ---የሚጠግበት .
የታስረ----የሚፈታበት
የተጠማ---የሚረካበት
የተከፋ--- የሚደሰትበት
ስደት፣--- የሚቆምበት

ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም የሚድፍንበት የፍቅርና የደስታ ዘመን ያድርግልን መልካም አዲስ አመት
2.7K views03:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 19:06:57 ​​ አበባዮሽ

እሰይ /ደስ ደስ ይበለን/(2)
አዲሱ አመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን

ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
ጌቶች አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
እሜቴ አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
ዘመን መጣ ብለን

አበባዮሽ ለምለም(2)
ባልንጀሮቼ ለምለም
ግቡ በተራ ለምለም
በእግዚአብሔር መቅደስ ለምለም
በዚያች ተራራ ለምለም
እንድታደንቁ ለምለም
የአምላክን ሥራ ለምለም
ህይወት ያገኛል ለምለም
እርሱን የጠራ ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም (2)
ክረምት አለፈ ለምለም
ጨለማው ጠፋ ለምለም
የመስቀሉ ቃል ለምለም
ሆነልን ደስታ ለምለም
እናገልግለው ለምለም
ቤቱ ገብተን ለምለም
ትንሽ ትልቁ ለምለም
ተሰልፈን ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም(2)
ያንን ኩነኔ ለምለም
ዘመነ ፍዳ ለምለም
የሞቱ በራፍ ለምለም
ያ ምድረበዳ ለምለም
ልክ አንደ ክረምት ለምለም
ሄደ ተገፎ ለምለም
ፀሐይ ወጣልን ለምለም
ጨለማው አልፎ ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም(2)
ይኸው መስከረም ለምለም
ይኸው ፀሐይ ለምለም
ንጉሡ ወርዶ ለምለም
ከላይ ሰማይ ለምለም
አውደ ዓመት ሆነ ለምለም
ደስታ ሰላም ለምለም
ፍቅር ሲገለጥ ለምለም
በአርያም ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም(2)
ይኸው አበባ ለምለም
ለምለም ቄጤማ ለምለም
አዲሱ ዘመን ለምለም
አምጥቷልና ለምለም
በሩን ክፈቱ ለምለም
መኳንንቶቹ ለምለም
የክብር ንጉሥ ለምለም
ይግባ ቤታችሁ ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም(2)
ቤታችሁ ይሙላ ለምለም
ሰላም ደስታ ለምለም
ሰጥቷችሁ እርሱ ለምለም
የሁሉ ጌታ ለምለም
ከዘመን ዘመን ለምለም
ያሸጋግራችሁ ለምለም
የሽበትን ዘር ለምለም
ይሸልማችሁ ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ

ይሸታል ዶሮ የእማምዬ ጓሮ
ይሸታል ጠጅ ጠጅ የአባብዬ ደጅ

አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ
እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰዎት ብዬ

ከብረው ይቆዩን ከብረው
የክብርን ወንጌል ሰምተው
የበጉን ሥጋ በልተው
የአምላክን ፊቱን አይተው
ከብረው ይቆዩን ከብረው
Join @ortodoxslijoch
3.7K views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 15:33:01 ንጉሥ ፈርኦን ለ ያዕቆብ ሐበሻ በጣም የሚጠላውን ጥያቄ ጠየቀው:: "ዕድሜህ ስንት ነው?"

ከባሕላችን እጅግ ሊላቀቀን ያልቻለ ጥያቄ ቢኖር ዕድሜን መናገር መፍራት ነው:: "ኸረ ዕድሜዬን አልደብቅም" የምንል ሰዎች እንኳን ከመናገራችን በፊት "ዕድሜ ጸጋ ነው" የሚል ትንሽ የመግቢያ ንግግር እናደርጋለን:: በሰው ፊት ዕድሜ የጠየቁ ሕፃናትም “ዕድሜ አይጠየቅም እሺ ማሙሽዬ" የሚል ምክር ከትንሽ ቁንጥጫ ጋር ይቀምሳሉ::
ንጹሐኑ ሕፃናት ትምህርት ቤት "How old are you?”ን ሲያነቡ ስለሚውሉ ለምን እንደማይጠየቅ ግራ ግብት ይላቸዋል:: ብቻ በአጭሩ "ዕድሜህ ስንት ነው?" ተብለን ስንጠየቅ "ሰዓት ስንት ነው?" ስንባል በምንመልስበት ፍጥነት አንመልስም::

ያዕቆብ ግን ፈርኦን ሲጠይቀው የሐበሻ ደም የለበትምና "የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው" ብሎ ቀልጠፍ ብሎ መለሰ:: የሚገርመው በምድር ላይ የኖረበትን ዘመን "የእንግድነት ዘመን" አለው:: እውነትም ይህች ዓለም ሁላችንም ለጊዜው በእንግድነት የመጣንባት ናት እንጂ ሀገራችንስ በሰማይ ነው:: በእንግድነት መጥተን ዘላለም እንደሚኖር እንነካከሳለን እንጂ እንግዶች ነን:: እንደ ያዕቆብ ያሉ ቅዱሳን ግን "በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ" (ዕብ 11:13) ሁሉን ትተው የተከተሉት ሐዋርያቱም "በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ" ብለው አስተማሩ:: (1ኛ ጴጥ 1:17)

ያዕቆብ ዕድሜዬ 130 ነው ካለ በኁዋላ ጥቂትም ክፉም ሆነብኝ አለ:: እንግዲህ መቶ ሠላሳ አንሶት ነው:: እርግጥ ነው ሰው ዕድሜ አይጠግብም:: ማቱሳላንም ብንጠይቀው "ባጭር ተቀጨሁ" ማለቱ አይቀርም:: የተፈጠርነው ከዘላለማዊት ነፍስ ጋር ስለሆነ ለመኖር እንጂ ለመሞት መቼም ዝግጁ አንሆንም:: እንደ ያዕቆብ ያለ ብዙ ነገር ያየ ሰው ደግሞ ዕድሜህ ያንስብሃል:: ከእናትህ ሆድ ጀምረህ የሕይወት ትግል ከጀመርክ ለብኩርና ከተሽቀዳደምክ : ከፈጣሪህ ጋር ትግል ከገጠምክ : ድንጋይ ተንተርሰህ ሰማይ ድረስ ከተመለከትክ : ለራሔል ዓሥራ አራት ዓመት ደጅ ከጸናህ : በዮሴፍ ለዓመታት ካለቀስክ ዕድሜህ ቢያጥብርህ አይፈረድብህም::

ያልተኖረ ዕድሜ ግን ይሰለቻል:: ሰው ሥራ ሲኖረው ቀኑ እንዴት ይሮጣል? ይላል:: ሥራ የፈታ ደግሞ "ኸረ የዛሬው ቀን አልሔድ አለ እኮ" ይላል:: በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪካቸው ከተጻፈ ሰዎች የሚያሳዝኑት "ኖረ ሞተም" የተባለላቸው ሰዎች ናቸው:: መኖርህ ካልፈየደ መሞትህ አይጎዳም ከመባል በላይ ምን አስከፊ ነገር አለ::

ወዳጄ አንተ ወደዚህች ምድር የመጣ አንተን የሚመስል ብቸኛው ሰው ነህ:: የማያልቅበት ፈጣሪ የአንተን ዓይነት ሰው ፈጥሮ አያውቅም ድጋሚም አይፈጥርም:: ምድርም የአንተ ዓይነት ሰው አይታ አታውቅም:: ዕድሜ የተሠጠህ ለአንተ ብቻ የተሠጠህን ነገር አበርክተህ እንድትሔድ ነው:: በአንተ ብቻ የሚፈታ ችግር በአንተ ብቻ የሚፈጠር ብዙ መፍትሔ አለ::

ሌሎች ከአንተ በሀብት በእውቀት በሥልጣን ወዘተ በልጠው ልታይ ትችላለህ:: ሕይወት ፍትሐዊ አይደለችም:: ፈጣሪ ያደላል ወይ ልትል ትችላለህ::
ከሀብታሙም ከአዋቂውም ከኃያሉም እኩል ለአንተ የተሠጠህ ፍትሐዊ ሥጦታ ግን ጊዜ ነው:: ለሁሉም ሰው ቀንና ሌሊቱ ሃያ አራት ሰዓት ነው:: በብራቸው ሰዓት ያስጨመሩ የሉም:: አጠቃቀምህ ነው እንጂ ጊዜ ለአንተም በእኩልነት ተሠጥቶሃል::

ዐዲስ ዓመት ሊገባ ነው:: ፀሐይ እያየችን ስታልፍ ሌላ አንድ ዓመት ሆናት:: 2012 አይቻልም እንጂ በድንጋይ ፈንክተን ብንሸኘው ደስ የሚለን ዓይነት ከባድ ዓመት ነበር:: አሁን ደግሞ ፈጣሪ በቸርነቱ ሌላ ዘመንን አቀዳጀን:: ፈጣሪ የሠጠን ያልተጻፈበት አዲስ ደብተር ነው:: ብዕሩ እጃችን ላይ ነው:: ምን እንጽፍበት ይሆን? ካለፈው ደብተር የቀጠለ ታሪክ እንጽፍ ይሆን? ወይስ አዲስ ነገር?

መልካም አዲስ ዓመት

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጳጉሜን 5 2012 ዓ ም
2.8K views12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 06:19:23 እንኳን ለ2015 ለዘመነ ሉቃስ ዓመተ ምህረት በሠላም አደረሳችሁ >>

መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን _
#የዘመን መለወጫ
#ዘመን መለወጫ ምንድ ነው.?
#እንቁጣጣሽ ምንድነው..?
#አዲስ አመት ለምን ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል...?

ኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያ መስከረም ነው፡፡ ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ ስለ አዲስ ዓመት በተለያየ ስም የመጠራቱ ታሪካዊ አመጣጥና ስያሜ መነሻ አሳቡ ምን እንደሆነ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

*ዘመን መለወጫ*
ዘመን መለወጫ መስከረም ወር የሆነበት ምክንያት “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር ይተካከላል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ቢቆጥሩ 366 ቀናት ይሆናል፡፡

“ሌሊቱም ከቀኑ ጋራ ይተካከላል፡፡ ዓመቱም ጠንቅቆ ቢቆጥሩት ሦስት መቶ ስልሳ አራት ቀን ይሆናል፡፡ /ሄኖክ.26፥44/ “ዘመናችንን እንደ
ቀድሞ አድሱ” /ሰ.ኤር.5፥21/ከቆየ እንዲል፡፡ በዘመነ ኖኅ ዓለምን ንፍር ውኃ አጥለቅልቆት በኋላ
ዳግመኛ ውኃው የጎደለበት በመሆኑ /ኩፋሌ 7፥1/
“በመጀመሪያው ወር መባቻም ምድር ታየች” እንዲል፡፡

*ዕንቁጣጣሽ*
ዕንቁጣጣሽ የተባለበት ምክንያት አንደኛ “ዕንቁ - ዕፅ አመጣሽ” ብሎ የአበባውንአህጉራትን መፈንዳት ያመለክታል፡፡ ሁለተኛ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ በእጣ ሲያካፍላቸው አፍሪካ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪካ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኀ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡

ሦስተኛው /1ነገ.10፥1-10/ ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሣባ /መንሻ አዜብ የንጉሡን ጥበብ ከመስማት ማየትን መርጣ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ከብዙ ሠራዊቶቿ ጋር የእጅ በመያዝ ሄደች፡፡ ንጉሡም በደስታ ተቀብሎ እርሱም “እንቁ ለጣትሽወርኀ
ጌጥ ይሁንሽ” በማለት አራት አይነት ቀለም የሚታይበት በቀንና በሌሊት የምታበራ ቀለበት ሰጥቷታል፡፡ ወሩም መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ ወጥቷል፡፡

*ቅዱስ ዮሐንስ*
ሦስተኛው የአዲስ ዘመን ስያሜ ቅዱስ ዮሐንስ ነው፡፡ የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን እንዲከበር አባቶች ወስነዋል፡፡ /ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 1-3/ መጽሐፈ ስንክሳር “የመስከረም ወር የተባረከ ነው፡፡ እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች
መጀመሪያ ነው፡፡

በአጠቃላይ ዘመን መለወጫ ከላይ ባየናቸው የተለያየ ስያሜ ይጠራ እንጂ ዘመኑ አዲስ እየተባለ ቢጠራም አዲስ መሆን ያለበት ወርና ወቅቱ ብቻ ሳይሆን የእኛ የክርስቲያኖች ሥርዓት ነው፡፡

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነታችሁን አታርክሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነውና እያለ
በመዋዕለ ሥጋዌው ያስተምር ነበር፡፡

አዲስ ዓመት ሲመጣ በኀጥያት፣ በተንኮል፣ በክፋት የቆሸሸው ሰውነታችን በንስሓ፣ በቅዱስ ቊርባን፣ በመልካም ተግባር አዲስ ልናደርገው ይገባናል፡፡
*መልካም አዲስ አመት*
Join @ortodoxslijoch
4.6K viewsedited  03:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 07:05:15 ጳጉሜ ➌
እንኳን ለሊቀ መላእኩ ቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!

ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ #ሩፋኤል ነኝ
(ጦቢያ ፲፪÷፲፭)
የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል የስሙ ትርጉም

#እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው ማለት ነው
...የዋህ የምህረት የረድኤት መልእክ ቅዱስ ሩፋኤል ከስራዎቹ እንፃር በተለያየ ስም ይጠራል ለአብነት ያክል
#ፈታሄ ማህጸን ይባላል እናቶች ሲወልዱ ምጥ እንዳይበዛባቸው የሚረዳ መልእክ ስለሆነ አያሌ ክርስቲያኖች ማርገዛቸውን ካወቁ ጀምሮ ድርሳኑን በማንበብ መልኩን በመድገም ጠበሉን በመጠመቅ ይለምኑታል እንደ እምነታቸው ጽናት ይደረገላቸዋል፡፡

#ዐቃቤ ኖኀቱ ለአምላክ ይባላል፡- ሰማያውያን መዛግብት በእጁ የሚጠበቅ በመሆኑ
#መራሔ ፍኖት ይባላል ፡- ጦቢትን በቀና መንገድ መርቶታልና
#መልአከ ክብካብ ይባላል፡- ጦቢያና ሣራን ያጋባ ጋብቻቸውን የባረከ በመሆኑ፡፡
ቁጥሩ የሰው ልጅችን ጸሎት ከሚያሳርጉት ሰባቱ መላእክት አንዱ እንደሆነ በመጽሐፍ ጦቢት ላይ ራሱ መልአኩ ሲናገር እናነባለን፡፡
( ጦቢ 12÷15)

ጻድቁ ሄኖክም በበሽታ ሁሉ ላይ በሰው ልጆች ቁስል ላይ የተሾመ መልአክ እንደሆነ ጽፏል ( ሄኖ 10÷13)

...ዓይነ ስውር የነበረውን ጦቢያ የዓሳ ሐሞት ዓይኑን እንዲቀባው ልጁ ጦቢትን በመምከር ብልዙን ከብሌኑ ላይ አንሥቶ ዓይኑን ያበራለት መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡

...ሌላው ጽንስ በማኀጸን ከተቋጠረ ከአርባኛው ቀን ጀመሮ ቅዱስ ሩፋኤል በጥበቃው የማይለየው ሲሆን አንዲት ሴትም የመውለጃዋ ቀን ደርሶ ምጥ በያዛት ጊዜ ሕመሙን የሚያቀልላትና ማኀጸኗን የሚፈታው ይኸው መልአክ ነው፡፡ ከዚህም ሥርአት የተነሳ ፈታሔ ማኀጸን በመባል ይጠራል፡፡

የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል እረድኤት በረከትና ጠበቃው እንዳይለየን የዛሬ አመት በሰላም፣በፍቅርና በጤና ያድርሰን አሜን፡፡
1.2K views04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 06:35:06
​​"ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ።"
ጦቢት፲፪፥፲፭

የዋህ የምህረትና የረድኤት መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከስራዎቹ አንፃር በተለያየ ስም ይጠራል ለአብነት ያክል፦

"ፈታሄ ማህጸን"ይባላል። እናቶች ሲወልዱ ምጥ እንዳይበዛባቸዉ የሚራዳ መልአክ ስለሆነ አያሌ ክርስቲያኖች ማርገዛቸዉን ካወቁ ጀምሮ ድርሳኑን በማንበብ መልኩን በመድገም ጠበሉን በመጠጣት ሰዉነታቸዉን በመቀባት ይለምኑታል፡፡እንደ እምነታቸዉ ጽናት ይደረገላቸዋል፡፡

"ዐቃቤ ኖኀቱ ለአምላክ"ይባላል፡፡ ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠበቅ በመሆኑ ።

"መራሔ ፍኖት"ይባላል፡፡ ጦቢትን በቀና መንገድ መርቶታልና፡፡

"መልአከ ክብካብ"ይባላል፡፡ ጦቢያና ሣራን ያጋባ ጋብቻቸዉን የባረከ በመሆኑ፡፡

"የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።" መዝ፴፬፥፯

Join @ortodoxslijoch
1.3K views03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 15:21:16 ጠቃሚ ምክሮች
•••
1. ከአለስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች ራቅ

“የጠብ መጀመሪያ እንደ ውኃ አፈሳሰስ ነው፤ ስለዚህ ጠብ ሳይበረታ አንተ ክርክርን ተው።”
— ምሳሌ 17፥14

2. ራስህን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች አርቅ። ምክንያቱም አንተን ራሱ ሳትፈልገዉ እንደነሱ እንድታስብ ትገደድ ይሆናል፡፡
“ልጄ ሆይ፥ በክፉ ሰዎች አትቅና፥ ከእነርሱ ጋርም መሆንን አትውደድ፤”
— ምሳሌ 24፥1
“በግፈኛ ሰው አትቅና፥ መንገዱንም ሁሉ አትምረጥ።”
— ምሳሌ 3፥31
“ክፉ ነገር ማድረግ ለሰነፍ ሰው ጨዋታ ነው፤ እንዲሁም ጥበብ ለአስተዋይ ነው።”
— ምሳሌ 10፥23
“ከሰነፍ ሰው ፊት ራቅ፥ በእርሱ ዘንድ የእውቀትን ከንፈር አታገኝምና።”
— ምሳሌ 14፥7
3. መቀበል የምትፈልገውን ስጥ።

4. ገንቢ ያለሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት ተቆጠብ።
“አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።”
— ምሳሌ 21፥23
“ፌዘኛን የሚገሥጽ ለራሱ ስድብን ይቀበላል፥ ኅጥአንም የሚዘልፍ ነውርን ያገኛል።”
— ምሳሌ 9፥7
“ፌዘኛን አትገሥጽ እንዳይጠላህ፤ ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል።”
— ምሳሌ 9፥8

5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑርህ።
“እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 13፥13

6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አትበል፥ የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና።

7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻው መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል....ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የኀላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ::
•••
Join @ortodoxslijoch
2.0K viewsedited  12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 15:14:53 የ ግዕዝ ቁጥር ከ 1 እስከ 1ቢሊዮን
*
አንተ
ወጣት እንካ ተቀበለኝ ንብረትህን እርስትህን እወቅ
እንዳትሆን መናፍቅ!
አልቦ 0
፩ አሐዱ 1
፪ ክልኤቱ 2
፫ ሠለስቱ 3
፬ አርባዕቱ 4
፭ ሐምስቱ 5
፮ ስድስቱ 6
፯ ስብዓቱ 7
፰ ስመንቱ 8
፱ ተሰዓቱ............. 9
፲ አሠርቱ .............10
፲፩ አሠርቱ ወአሐዱ 11
፲፪ አሠርቱ ወክልኤቱ 12
፲፫ አሠርቱ ወሠለስቱ 13
፲፬ አሠርቱ ወአርባዕቱ 14
፲፭ አሠርቱ ወሐምስቱ 15
፲፮ አሠርቱ ወስድስቱ 16
፲፯ አሠርቱ ወሰብዓቱ 17
፲፰ አሠርቱ ወስመንቱ 18
፲፱ አሠርቱ ወተሰዓቱ 19
፳ እስራ 20
፳፩ እስራ ወአሐዱ 21
፳፪ እስራ ወክልኤቱ 22
፳፫ እስራ ወሠለስቱ 23
፳፬ እስራ ወአርባዕቱ 24
፳፭ እስራ ወሐምስቱ 25
፳፮ እስራ ወስድስቱ 26
፳፯ እስራ ወሰብዓቱ 27
፳፰ እስራ ወሰመንቱ 28
፳፱ እስራ ወተሰዓቱ 29
፴ ሠላሳ 30
፴፩ ሠላሳ ወአሐዱ 31
፴፪ ሠላሳ ወክልኤቱ 32
፴፫ ሠላሳ ወሠለስቱ 33
፴፬ ሠላሳ ወአርባዕቱ 34
፴፭ ሠላሳ ወሐምስቱ 35
፴፮ ሠላሳ ወስድስቱ 36
፴፯ ሠላሳ ወሰብዓቱ 37
፴፰ ሠላሳ ወሰመንቱ 38
፴፱ ሠላሳ ወተሰዓቱ 39
፵ አርብዓ 40
፶ ሃምሳ 50
፷ ስድሳ 60
፸ ሰብዓ 70
፹ ሰማንያ 80
፺ ተሰዓ 90
፻ ምዕት 100
፻፩ ምዕት ወአሐዱ 101
፻፪ ምዕት ወክልኤቱ 102
፻፫ ምዕት ወሠለስቱ 103
፻፬ ምዕት ወአርባዕቱ 104
፻፭ መዕት ወሐምስቱ 105
፻፮ ምዕት ወስድስቱ 106
፻፯ ምዕት ወሰብዓቱ 107
፻፰ ምዕት ወስመንቱ 108
፻፱ ምዕት ወተሰዓቱ 109
፻፲ ምዕት ወአሠርቱ 110
፻፲ወ፩ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 111
፻፲ወ፪ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 112
፻፲ወ፫ ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ 113
፻፲ወ፬ ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ 114
፻፲ወ፭ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 115
፻፲ወ፮ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 116
፻፲ወ፯ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 117
፻፲ወ፰ ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ 118
፻፲ወ፱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 119
፻፳ ምዕት ወእስራ 120
፻፴ ምዕት ወሠላሳ 130
፻፵ ምዕት ወአርብዓ 140
፻፶ ምዕት ወሃምሳ 150
፻፷ ምዕት ወስድሳ 160
፻፸ ምዕት ወሰብዓ 170
፻፹ ምዕት ወሰማንያ 180
፻፺ ምዕት ወተሰዓ 190
፪፻ ክልኤቱ ምዕት 200
፪፻ወ፩ ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ 201
፪፻ወ፪ ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ 202
፪፻ወ፫ ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ 203
፪፻ወ፬ ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ 204
፪፻ወ፭ ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ 205
፪፻ወ፮ ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ 206
፪፻ወ፯ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ 207
፪፻ወ፰ ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ 208
፪፻ወ፱ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ 209
፪፻ወ፲ ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ 210
፪፻፲ወ፩ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 211
፪፻፲ወ፪ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 212
፪፻፲ወ፫ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ 213
፪፻፲ወ፬ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ 214
፪፻፲ወ፭ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 215
፪፻፲ወ፮ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 216
፪፻፲ወ፯ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 217
፪፻፲ወ፰ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ 218
፪፻፲ወ፱ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 219
፪፻፳ ክልኤቱ ምዕት ወእስራ 220
፪፻፴ ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ 230
፪፻፵ ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ 240
፪፻፶ ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ 250
፪፻፷ ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ 260
፪፻፸ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ 270
፪፻፹ ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ 280
፪፻፺ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ 290
፫፻ ሠለስቱ ምዕት 300
፬፻ አርባዕቱ ምዕት 400
፭፻ ሐምስቱ ምዕት 500
፮፻ ስድስቱ ምዕት 600
፯፻ ስብዓቱ ምዕት 700
፰፻ ስመንቱ ምዕት 800
፱፻ ተሰዓቱ ምዕት 900
፲፻ አሠርቱ ምዕት 1000
፳፻ እስራ ምዕት 2000
፴፻ ሠላሳ ምዕት 3000
፵፻ አርብዓ ምዕት 4000
፶፻ ሃምሳ ምዕት 5000
፷፻ ሳድስ ምዕት 6000
፸፻ ሰብዓ ምዕት 7000
፹፻ ሰማንያ ምዕት 8000
፺፻ ተሰዓ ምዕት 9000
፻፻ እልፍ 10,000
፪፻፻ ክልኤቱ እልፍ 20,000
፫፻፻ ሠለስቱ እልፍ 30,000
፬፻፻ አርባዕቱ እልፍ 40,000
፭፻፻ ሐምስቱ እልፍ 50,000
፮፻፻ ስድስቱ እልፍ 60,000
፯፻፻ ሰብዓቱ እልፍ 70,000
፰፻፻ ስመንቱ እልፍ 80,000
፱፻፻ ተሰዓቱ እልፍ 90,000
፲፻፻ አሠርቱ እልፍ 100,000
፳፻፻ እስራ እልፍ 200,000
፴፻፻ ሠላሳ እልፍ 300,000
፵፻፻ አርብዓ እልፍ 400,000
፶፻፻ ሃምሳ እልፍ 500,000
፷፻፻ ስድሳ እልፍ 600,000
፸፻፻ ሰብዓ እልፍ 700,000
፹፻፻ ሰማንያ እልፍ 800,000
፺፻፻ ተሰዓ እልፍ 900,000
፻፻፻ አእላፋት 1,000,000
፲፻፻፻ ትእልፊት 10,000,000
፻፻፻፻ ትልፊታት 100,000,000
፲፻፻፻፻ ምእልፊት 1,000,000,000

Join @ortodoxslijoch
2.0K viewsedited  12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 19:51:42 #ባህረ_ሀሳብ ትውስታ

#የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት
1. አዲሱ ዓመት በየትኛው ወንጌላዊ እንደሚሰየም
ዘመኑ:
ዘመነ ማቴዎስ፣
ዘመነ ማርቆስ፣
ዘመነ ሉቃስ፣
ዘመነ ዮሐንስ
መሆኑን ለማወቅ በመጀመሪያ ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረውን 5500 ዘመንን እና ከክርስቶስ ልደት በኋላ ለማስላት (ለማወቅ) የምንፈልገውን ዓመተ ምህረት እንደምራለን።
ከዚያ ድምሩን ለ4 እናካፍላለን።
ወይም
በቀላሉ ከክርስቶስ ልደት በኋላ የምንፈልገውን ዓመተ ምህረት ለ4 አካፍለን ቀሪው ፦
1 ከሆነ ዘመነ ማቴዎስ፣
2 ከሆነ ዘመነ ማርቆስ፣
3 ከሆነ ዘመነ ሉቃስ፣
4 ከሆነ ዘመነ ዮሐንስ ይባላል።

ምሳሌ፦
2015ን ብንወስድ
5500+2015= 7515 ይሆናል። ለ4 ስናካፍለው 7515 ÷ 4 = 1878 ደርሶ ቀሪ 3 ይሆናል።

ወይም በቀላሉ መንገድ
2015 ÷ 4 = 503 ደርሶ ቀሪ 3 ይሆናል። ስለዚህ በ2015 ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ ነው።

አዲሱ ዓመት የሚውልበት ዕለት
ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ረቡዕ፣ ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜ፣ ወይም እሁድ መሆኑን ለማወቅ አሁንም በመጀመሪያ ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረውን 5500 ዘመንን እና ከክርስቶስ ልደት በኋላ ለማስላት (ለማወቅ) የምንፈልገውን ዓመተ ምህረት እንደምራለን።

ከዚያ ድምሩን ለ4 እናካፍልና ድርሻውን ከመጀመሪያው ድምር ላይ እንደምረዋለን።

ከዚያ ድምሩን ለ7 ስናካፍል ቀሪው (0 ከሆነ ሰኞ፣ 1 ከሆነ ማክሰኞ፣ 2 ከሆነ ረቡዕ፣ 3 ከሆነ ሐሙስ፣ 4 ከሆነ አርብ፣ 5 ከሆነ ቅዳሜ፣ 6 ከሆነ እሁድ) ዕለት መስከረም 1 ቀን ይሆናል።

ምሳሌ፦ 2015ን እንውሰድ 5500+2015=7515 ከዛም 7515÷4 = 1878 (ድርሻ ነው) ዕለቱን ለማወቅ 7515+1878=9391 ይህንን ለሰባት እናካፍለው 9391÷7=1341 ቀሪ 6 ነው።

ስለዚህ በ2015 ዘመኑ
#ዘመነ_ሉቃስ ዕለቱ ዕለተ እሁድ ይሆናል።
Join @ortodoxslijoch
1.7K viewsedited  16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 07:26:07 #ሰንበት_ክቡር_ነው
#ሰንበት_የእግዚአብሔር_ነው
#ስንበትእሁድ_ነው
#ከሰንበት_ረድኤት_በረከት_ይክፈለን
እኛንም ፍጡሮችህንም ሀገራችንንም አምላክ ሆይ ጠብቀን

መልካም እለተ ሰንበት

#ሰንበት ምንድን ነው?
“ #ሰንበት” የሚለው ቃል “ማረፍ፤ ማቆም” የሚል ትርጉም ካለው የዕብራይስጥ ቃል የመጣ ነው። ይህ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው ለጥንት እስራኤላውያን በተሰጠው ትእዛዝ ላይ ነው። (ዘፀአት 16:23) ለምሳሌ ያህል፣ የአሥርቱ ትእዛዛት አራተኛ ሕግ እንዲህ ይላል፦ “የሰንበትን ቀን ቅዱስ አድርገህ መጠበቅ እንዳለብህ አትርሳ። ሥራህንና የምታከናውናቸውን ነገሮች በሙሉ በስድስት ቀን ሠርተህ አጠናቅ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው። በዚህ ቀን . . . ምንም ሥራ አትሥሩ።” (ዘፀአት 20:8-10) የሰንበት ቀን የሚባለው ዓርብ ፀሐይ ከጠለቀችበት አንስቶ ቅዳሜ ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ድረስ ያለው ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ እስራኤላውያን ከሰፈራቸው ርቀው አይሄዱም፣ እሳት አያቀጣጥሉም፣ እንጨት አይሰበስቡም ወይም ምንም ዓይነት ሸክም አይሸከሙም። (ዘፀአት 16:29፤35:3፤ ዘኁልቁ 15:32-36፤ ኤርምያስ 17:21) የሰንበትን ሕግ መጣስ በሞት ያስቀጣል።—ዘፀአት 31:15
በአይሁዳውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት ሰባተኛውና ሃምሳኛው ዓመት እንዲሁም አንዳንድ ቀናት ሰንበት ተብለው ይጠሩ ነበር። በሰንበት ዓመት መሬቱ ሳይታረስ ይተው የነበረ ሲሆን ዕዳ ያለባቸው እስራኤላውያንም ዕዳቸው ይሰረዝላቸው ነበር።—ዘሌዋውያን 16:29-31፤ 23:6, 7, 32፤ 25:4, 11-14፤ ዘዳግም 15:1-3

ከሰንበት ረድኤት በረከት የክፈለን
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
በያላችሁበት መልካም እለተ ሰንበት
Join @ortodoxslijoch
366 views04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ