Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxslijoch — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxslijoch — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxslijoch
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.17K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ምንማማርበት :መዝሙር: ስብከቶች ይተላለፋል !

መንፈሳዊ ትምህርቶች : መንፈሳዊ ጥያቄዎች : ስብከት : መዝሙር : ይቀርብበታል #ጉዞው ገዳማት #ሰማህታት ታሪክ ይቀርባል!
FacebookGroup : ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ይቀላቀሉ ::

#shear

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-01 06:45:25 # አዋጅ አዋጅ አዋጅ
ፆመ_ሐዋርያት ( # ሰኔ_ፆም )
መቼ_ይገባል?ለምንስ_ይፆማል

2015'ዓ'ም ግንቦት 28 ሰኞ ይጀመራል። ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታቸንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት ፆም ነው።

የሰኔ ፆም :- ይህ ፆም የሀዋርያት ፆም በመባል ይታወቃል ስለ ምን የሐዋርያት ፆም ተባለ ቢሉ በበአለ ጴራቅሪጦስ ሀዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በዉሀላ የፆሙት ፆም ስለሆነ ነው።
የሰኔ ዖም የሚፆምበት ጊዜያት
የሰኔ ፆም ቢያንስ 15 ቢበዛ 45 ቀናት ያህል ይፆማል የሰኔ ፆምን እስከ 9 ሰአት እንድንፆም ቤተክርስቲያን አውጃለች ።

የሚገባበት ቀን በየአመቱ የተለያየ ቢሆንም የፆሙ ማብቂያ ዕለት ግን ሐምሌ 5 ድረስ ነው ። ሐምሌ 5 ሁለቱ ሀዋርያት ጴጥሮስ እና ጳዉሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉበት እለት ነው ።

ቅዱሳን ሐዋርያት የአምላካቸውን የመምህራቸውን አርአያ ተከትለው እርሱ ወደ ማዳን ሥራው ማለትም ህሙማነ ሥጋን በተዓምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት ከማዳን አስቀድሞ የስራውን መጀመሪያ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊት እንደ ጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው (ተከፈፍለው) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያን ጾምን አድርገዋል፡፡

ሐዋርያትም ይህንን ጾም እንደሚጾሙ ጌታችን አስቀድሞ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው በጠየቁት ጊዜ ተናግሮ ነበር፡፡ ‹‹ እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው
ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለምንድን ነው? አሉት ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ›› ማቴ 9፥15-16

እኛም ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመላበስ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ‹‹መሣሪያ›› አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ ነው። አንድ አንዶች እንደሚሉት የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምዕመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡
ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን በሰላም ያድርሰን!!!
6.1K views03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 08:27:12 የመጽሐፍ ቅዱስ ስሞች......"ለልጅዎ ስም
ማውጣት ይፈልጋሉ
ከዚህ ይመረጡ"
1. ዮሐንስ ፡- የእግዚአብሔር ፀጋ (ሀሴት፣ ፍስሀ)
2. ዳንኤል ፡- እግዚአብሔር ፈራጅ ነው
3. ኤልሳዕ ፡- እግዚአብሔር ደህንነት
4. አሞን ፡- የወገኔ ልጅ
5. እስራኤል ፡- የእግዚአብሔር ህዝቦች
6. ማርያም ፡- የእግዚአብሔር ስጦታ
7. ሀና ፡- ፀጋ
8. ሩሀማ ፡- ምህረት የሚገባት
9. ኢያሱ ፡- እግዚአብሔር አዳኝ ነው፣ መድሃኒት
10. ጌርሳም፡- ከሌላ ምድር ስደተኛ ነኝ
11. እዮሳፍጥ፡- እግዚአብሔር ፈርዷል
12. እዮአም ፡- አዳኝ
13. ኢዮሲያስ፡- ከፍ ከፍ አለ
14. ኤልሳቤጥ፡- እግዚአብሔር መሀላዬ ነው
15. አብርሃም ፡- የብዙሃን አባት
16. ኢሊዲያ (ይድድያ)፡- በእግዚአብሔር የተወደደ
17. ኤዶንያስ ፡- እግዚአብሔር ጌታዬ ነው
18. ኦዶኒራም ፡- ጌታየ ከፍ ያለ ነው አለ
19. ሆሴዕ፡- እግዚአብሔር መድኃኒት ነው
20. ሕዝቅያዝ ፡- እግዚአብሔር ሀይሌ ነው
21. ጴጥሮስ፡- መሰረት
22. ሴት ፡- ምትክ
23. ሙኤል ፡- እግዚአብሔርን ለምኜዋለው
24. አቤል ፡- የህይወት እስትንፋስ
25. ጎዶሊያስ ፡- እግዚአብሔር ታላቅ ነው
26. ስጥና ፡- ተዘጋ
27. ማቴዎስ ፡- ሞገስ
28. ፌቨን፡- የእግዚአብሔር አገልጋይ
29. ሚኪያስ ፡- እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን አለ
30. ይሁዳ፡- አማኝ (የአማኝ ልጅ)
31. ወንጌል ፡- የምስራች
32. ኤርሚያስ ፡- እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደርጋል
33. ህዝቅኤል ፡- እግዚአብሔር ብርታት ይሰጣል
34. ማራናታ፡- እግዚአብሔር ቶሎ ና
35. ሆሴዕ ፡- እግዚአብሔር ያድናል
36. አሞፅ ፡- ሀይል
37. ኤሴቅ ፡- የተጣላሁብሽ
38. ሚኪያስ ፡- እግዚአብሔር የሚመስል ማን ነው
39. ኢዮኤል፡- እግዚአብሔር አምላክነው
40. አብድዩ፡- የእግዚአብሔር አገልጋይ
41. ዮናስ ፡- ርግብ (የዋህ፣እሩሩህ)
42. እምባቆም ፡- እቅፍ
43. ሶፎኒያስ ፡- እግዚአብሔር ጠብቋል
44. ሀጌ፡- በሀላዊ ወይም በበዓል የተወለደ
45. ዘካርያስ ፡- እግዚአብሔር ያስታውሳል
46. ሚልክያስ ፡- መልክተኛዬ
47. ናታኔም ፡- የእግዚአብሔር ጠራጊ
48. አቤኔዘር ፡- ምስጋናዬን ለእግዚአብሔር አቀርባለው
join @ortodoxslijoch
5.2K views05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 15:55:28 ☞ ጠቃሚ ምክሮች
•••
1. ከአለስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች ራቅ።

“የጠብ መጀመሪያ እንደ ውኃ አፈሳሰስ ነው፤ ስለዚህ ጠብ ሳይበረታ አንተ ክርክርን ተው።”
— ምሳሌ 17፥14

2. ራስህን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች አርቅ። ምክንያቱም አንተን ራሱ ሳትፈልገዉ እንደነሱ እንድታስብ ትገደድ ይሆናል፡፡
“ልጄ ሆይ፥ በክፉ ሰዎች አትቅና፥ ከእነርሱ ጋርም መሆንን አትውደድ፤”
— ምሳሌ 24፥1
“በግፈኛ ሰው አትቅና፥ መንገዱንም ሁሉ አትምረጥ።”
— ምሳሌ 3፥31
“ክፉ ነገር ማድረግ ለሰነፍ ሰው ጨዋታ ነው፤ እንዲሁም ጥበብ ለአስተዋይ ነው።”
— ምሳሌ 10፥23
“ከሰነፍ ሰው ፊት ራቅ፥ በእርሱ ዘንድ የእውቀትን ከንፈር አታገኝምና።”
— ምሳሌ 14፥7
3. መቀበል የምትፈልገውን ስጥ።

4. ገንቢ ያለሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት ተቆጠብ።
“አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።”
— ምሳሌ 21፥23
“ፌዘኛን የሚገሥጽ ለራሱ ስድብን ይቀበላል፥ ኅጥአንም የሚዘልፍ ነውርን ያገኛል።”
— ምሳሌ 9፥7
“ፌዘኛን አትገሥጽ እንዳይጠላህ፤ ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል።”
— ምሳሌ 9፥8

5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑርህ።
“እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 13፥13

6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አትበል፥ የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና።

7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻው መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል....ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የኀላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ::
•••
__
☞ 🅢🅗🅐🅡🅔
               Join  @ortodoxslijoch
5.4K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 20:55:41 #ግንቦት_❷❶_
"እናቴ_ማሪያም_ደጓ_እናቴ"
◇ እንኳን_ለደብረ_ምጥማቅ_አመታዊ_የመገለጥ_በዓል_
በሰላም_በጤና_አደረሳችሁ_አደረሰን ◈።
◇ #ግንቦት_ ◇❷❶_
"እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም"➺በድብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ ወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአምስት (5) ቀን የታየችበት ነው።

◇ ጥንት ነገሩ እንዲህ ነው።
ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ስግደት ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮጵያ በተሰደደበት ጊዜ።

◈ ከድንግል እናቱ፣ ከዮሴፍ፣ ከሰሎሜ ጋር በደብረ ምጥማቅ ነበር።
◇ እመቤታችን ቦታውን ስለወደደችው።
ልጇ እንዲህ አላት ይህ ቦታ ወደ ፊት ያንቺ መገለጫ ያሆናል ብሎ ቃል ኪዳን ገባላት።

እመቤታችን በልጇ ፍቃድ ግንቦት 21 ቀን ከአእላፍ መላእክት፣ ፆድቃን፣ ሰማዕታት አስከትላ መታ ለአምስት ቀን ና ለክርስቲያኑና ለአሕዛቡ የተገለፀችበት ቀን ነው።

◈➺ ይህም በዓል ከ33ቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚህ ቀን ግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን እመቤታችን ጻድቃንን መልአክትን አስከትላ ትገለጽላቸው ነበር።
እስላምም ክርስቲያንም በግልጽ ይመለከቷት ነበር።

◈ ከየአገሩ ያሉ ሰዎች ይሰበሰባሉ ድንኳን ተክለው ሰቀላ ሰርተው አጎበር ጥለው ይከትማሉ ፤ ድንግልም ከግንቦት 21 ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሳታቋርጥ ትገለጽላቸው ነበር፤

◇ ህዝቡ የተለያየ ጥያቄ ይጠይቃታል አዳም አባታችንን አሳይን? ይሏታል
◈ ገሚሱ ነብዩ ዳዊትን
◈ ገሚሱ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሳይን ይሏታል?
◈ አንዳንዱም ከዚህ ቀደም የሞተ ዘመዱን እንድታሳየው ይጠይቃታል?

◇ እርሷም ለሁሉም ፍቃዳቸውን ትፈጽምላቸው ነበር፤
አዳምን ስትጠራው ከሔዋን ጋር
ዳዊትን ስትጠራው ከበገናው ጋር ቅዱስ ጊዮርጊስን ስትጠራው ከጸአዳ ፈረሱ ጋር ነው።

◇ ወይ ግሩም ታዲያ ይህ በዚያ ደጉ ዘመን ነበር፤
◇ አሁን ግን ኃጢያታችን ሲበዛ በረድኤት ወይም ለበቁ ካልሆነ
በገሃድስ ተገልጻ አትታይም።

➺ ለእናቱ ለቅዱስተ ቅዱሳን ለንፅህተ ንፁሀን
◈ ለአዛኝቷ ድንግል እመቤቴ ለቅድሳን እናታቸው
◈ ለነቢያት ትንቢታቸው
◈ ለሰማእታት እክሊላቸው ለሆነች ለእናቱሲል ይማረን። ኣሜን፫

➺◇በቃቹህ ይበለን ከመጣብን ከዚህ ክፉ የዘር በሽታ በቃችሁ ይበለን።ኣሜን ፫
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅሯ በልባችን ጣዕሟ በአንደበታችን ይደርብን። ኣሜን፫
➺ወስብሐት ለእግዚአብሔር
➺ወለወላዲቱ ድንግል
➺ወለመስቀሉ ክብር
     Join @ortodoxslijoch
7.3K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 06:09:10 #የሰንበትን_ቀን_ትቀድሰው_ዘንድ_አስብ

‹‹ስድስት ቀን ስራ፣ተግባርህም ሁሉ አድርግ በሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፡፡እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን አርፏልና ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታል፡፡ ›› (ዘጸ 20፡10-11)

#ሰንበት_ማለት_ምን_ማለት_ነው ?

ሰንበት ማለት አቆመ፣አረፈ ማለት ነው፡፡ይህ ቀን የጌታ ዕረፍት የተባረከም ቀን ነው፡፡ከማንኛውም ሥጋዊ ሥራ ተቆጥበን የእግዚአብሔርን ውለታ የምናስብበት ቀን ነው፡፡ ሰው እረፍት ያስፈልገዋል፡፡ የሰንበት ቀንም የተፈጠረው ለዚህ ነው፡፡ (ዘዳ 5፡14)፣(ማር 2፡38)
ከሳምንቱ ሰባት ቀናት መካከል ለእረፍት የተቀደሰው የተባረከው ዕለት ሰንበት ብቻ ነው፡፡ ስለሌሎች ቀናት የተነገረው ‹‹ ያ መልካም እንደሆነ አየ››የተባለው ብቻ ነው፡፡ ሰንበትን ግን ባርኮታል ቀድሶታል፡፡ (ዘፍ 1፡12፣ 18፡20፣ 25፡31)

በሐዲስ ኪዳን ለክርስቲያን ሁለት ሰንበት አለ ቀዳሚት ሰንበት(ቅዳሜ) እና ሰንበተ ክርስቲያን(እሑድ)
ቀዳሚት ሰንበት (ቅዳሜ)
ጌታ ያረፈባት ለእስራኤል ዘሥጋ የታዘዘው ሰንበት ነው፡፡ ይህ ቀን እስራኤላውያንን እግዚአብሔር አምላክ ከግብፅ ባርነት ወደ እረፍት እንዳወጣቸው ያመለክታል፡፡ዘዳ5-2-16 በእግዚአብሔር እና በህዝቡ መካከል ምልክት ነበረ ሰንበትን አለማክበር ግን ከባድ ቅጣት ያስከትል ነበር፡፡ (ዘጸ 3፡17) ፣ (ሕዝ 20፡12) ፣ (ዘኁ 15፡32-36)
ፈሪሳውያን በነበራቸው የተሳሳተ አመለካከት በሰንበት ቀን እንኳን መልካም ሥራን አይሰሩም ነበር፡፡ስለዚህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተወቅሰዋል፡፡ (ማቴ 12፡14) ፣ (ሉቃ 4፡16)

#ሰንበተ_ክርስቲያን_(እሑድ)

ይህች ቀን ለሳምንቱ መጀመሪያ፣ጌታችን ሥነ ፍጥረትን መፍጠር የጀመረበት ጌታ የተነሣበት፣መንፈስ ቅዱስ የወረደበት እንዲሁም ጌታችን ዳግመኛ በክብር የሚመጣበት ዕለት ስለሆነ ሰንበተ ክርስቲያን እንለዋለን፡፡ በሰንበተ ክርስቲያን (በጌታ ቀን) የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ልዩ ትኩረት በመስጠት ይሰባሰቡ ነበር፡፡ (ሐዋ 20፡7) ፣ገንዘብ ያዋጡበት ነበር (1ኛቆሮ 16፡2) ፣ በሥርዓተ ዓምልኮ የሚተጉበት፣የጌታችን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን የሚቀበሉበት ዕለት ነበር፡፡ (ዮሐ 20፡1-24) ፣ (ሐዋ 2፡11-14)

በቤተክርስቲያን ታሪክ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ሰንበት ናት በማለት ሥራ እንዳይሰራባት አዋጅ አስነግሮ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ይህቺ ዕለት በሐዲስ ኪዳን መከበር የጀመረ ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ከፋሲካ በፊት የሰንበት (የቀዳሚት) ማግስት በመባል በኩራት እና ቀዳሚያት የሚያቀርቡበት ቀን ነበር፡፡ (ራዕ 1፡10)

በቀዳሚት ሰንበት ቅዱስ እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ አርፎ ሥጋዊ እረፍትን ለሰው እንዳስተማረ በዚህች ቀን (በሰንበተ ክርስቲያን) በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን የዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍት የምናስብበት ነው፡፡ (ዕብ 4፡1-10)

#የሰንበት_ቀን_መሰጠት_ዓላማ

የሰው ልጅ ባሕርይ ደካማ ነውና እግዚአብሔር ሰንበትን ሰራለት፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ደካማ ባህሪያችንን ስለሚያውቅ ከሳምንቱ ዕለታት አንዱ ሰንበት እድርጎ ለዕረፍት ሰጠን፡፡ ከድካማችን የተነሳ በዕለቱ መስራት አንችልምና ሰንበት ለሥጋችን ጠቃሚ ነው፡፡ ነገር ግን ሰንበት የተሰጠበት ምክንያት ሰው በዚህ ዓለም ሲደክም ስጋውን ብቻ ሲያገለግል እንዳይኖር የአምላኩን ውለታ እያሰበ በመንፈሳዊ አገልግሎት ፀንቶ እንዲኖር ነው፡፡ ዘጸ 5-14-15

ለምልክት

አምላካችን እግዚአብሔር እንደተናገረው ሁሉ ሰንበት የዘላለማዊ እና የመንፈሳዊ ዕረፍታት ምልክት ሆኖ የተሰጠ ጸጋ ነው፡፡ ዘጸ 31-13 ሰንበት ለሚመጣው ዘላለማዊ ዕረፍት ምሳሌ ሆኖ የተሰጠ የብሉይ ኪዳን ሕግ ነው፡፡ በህጉ መሰረት በሰንበት ዕረፍተ ሥጋ ይደረጋል፡፡ይህም ለኋላው ዘመን ለድኅነተ ነፍስ ምሳሌ ነው፡፡ በሐዲ ኪዳንም የተገለጠው የክርስቶስ ትንሳኤ በሰንበተ ክርስቲያን ተፈፅሟል፤ ሰንበተ ክርስቲያንም የሰው ልጆች ለዘለዓለም አርፈው ከእግዚአብሔር ጋር በደስታ የሚኖሩበት ምስጢረ ትንሣኤ የተገለጠባት የድኅነት ቀን ናት፡፡

#ሰንበትን_እንዴት_ማክበር_ይገባል?

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰንበት ለመንፈሳዊ ሥራዎች(አገልግሎቶች) የተሰጠች መሆኗን ለማስተማር በሰንበት ድውያንን ይፈውስ፣ በምኩራብ እየተገኘም ያስተምር ነበር፡፡ (ዮሐ 5፡2-11 ፣9-14)፣(ሉቃ 14፡1-6)
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመፍቅረ ሰንበት አይሁድ ስለሰንበት አከባበር ሲያስተምራቸው ‹‹ከእናንተ አንድ በግ ያለው በሰንበትም በጉ በጉድጓድ ቢወድቅበት ይዞ የማያወጣው ማን ነው? እንግዲህ ሰው ከበግ እንደምን አይበልጥም? ስለዚህ በሰንበት መልካም ሥራን መሥራት ተፈቅዷል›› ብሏል።

ማቴ12-10-13 ክርስቲያን ሰንበትን ሲያከብር እንደጌታችን ትምህርት መንፈሳዊ ሥራን በመሥራት ይገባል እንጂ ልክ እንደ አይሁድ ያጠፈውን ሳይዘረጋ የዘረጋውን ሳያጥፍ ሊያሳልፍ አይገባም፤ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሯል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር!!!
    Join @ortodoxslijoch
5.6K views03:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 05:54:25 #እኔ_በእግዚአብሔር_ፊት_የምቆመው_ገብርኤል_ነኝ (ሉቃ 1፥19)
#ይህ_ገብርኤል_ነው
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤ የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ዳንኤልን ከአነብስት ያዳነው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ወደ ዘካሪያስ የተላከ የዮሐንስ ልደት ያበሰረ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ቂርቆስና ኤናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ሰብአ ሰገልነረ በኮከብ ምልክት የመራቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ድንግል ማርያሜና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
የብርሃን ወርቅ የተቀዳጀ
#ገብርኤል_ነወ ።
የአሸናፊና የኀኃይል መልአክ
#ገብርኤል_ነው ።
ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ
#ገብርኤል_ነው ።
#የመልአኩ_የቅዱስ_ገብርኤል_ጥበቃና_ረድኤት_አይለየን
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
      Join @ortodoxslijoch
7.9K views02:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 18:16:16 ሐይቅ እጢፋኖስ የመጀመሪያው መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ የነበረ እጅግ ጥንታዊ ና ታሪካዊ ሥፍራ ነው:: በቅዱስ አባ ኢየሱስ ሞዓ አባትነት አእላፋትን የወለደው ይህ የቤተ ክርስቲያናችንና የሀገራችን ኩራት የሆነ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫንና አቡነ ተክለ ሃይማኖትን የመሳሰሉ ቅድስናን ከሊቅነት ያስተባበሩ መምህራንን ያፈራ የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ሥነ ጽሑፍ ከፍታ ላይ ለመድረሱ መነሻ የሆነ ቦታ ነው::

ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ በዕድሜ ዘጠና ዓመት ያለፋቸው በጵጵስና ለብዙ ዓመታት ያገለገሉ ዕብራይስጥና ዐረቢኛን ጠንቅቀው የሚያውቁ በረከታቸው የሚያሳሳ ለቤተ ክርስቲያን የዋሉት ውለታ እጅግ ብዙ የሆነ አባት ናቸው::

"ልሔድ ክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ" የሚሉት እኚህ ሐዋርያዊ አባት ከማለፌ በፊት ይህንን ትምህርት ቤት ፈጽሜ እንድሔድ አግዙኝ ብለው ትልቅ የበረከት ጥሪን ለሁላችን አስተላልፈዋል:: እንኳን ሐይቅን ያህል ታሪካዊ ሥፍራ ላይ ቀርቶ በበረሃ ላይም ሕንፃ እንጀምር ቢሉን የብፁዕ አባታችንን ቡራኬ ለመቀበል የማይሻማ የለም:: የኤልያስን በረከት ለመቀበል ኤልሳዕ የሮጠውን ሩጫ ሁላችንም ይህንን ትምህርት ቤት በመፈጸም እንሮጣለን::

ነገው ዕለት "ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት" የተሰኘውን ድንቅ መጽሐፋቸውን ከቀኑ 7:00 ጀምሮ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አዳራሽ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ዶ/ር አንዱዓለም ዳግማዊ የመጽሐፋቸውን ሽያጭ የሚገኘውን ትርፍና በዕለቱ የሚገኘውን ገቢ ለሐይቅ እስጢፋኖስ የትምህርት ቤት ሕንፃ ግንባታ እንዲውል አድርገዋል:: ነገ በቅድስት ሥላሴ ተገኝተን በረከቱን እንካፈል::

ከሩቅ ያለንም በዚህ አካውንት የተቻለንን እናስገባ:: 1000520883097
https://fb.watch/kMs74TMFIK/?mibextid=CDWPTG
4.9K views15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-24 18:14:42 እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ ዕርገተ እግዚእ "

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ዕርገትን 2 ጊዜ ታከብራለች::

አንዱ "ጥንተ በዓል": ሁለተኛው ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል:: ጥንተ በዓል ማለት ጌታችን በትክክል ያረገበትን ቀን ያመለክታል::

+የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በኪነ ጥበቡ (በሕማሙ: በሞቱ) ዓለምን አድኖ: 40 ቀን ለሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን አስተምሯቸዋል::

+በ40ኛው ቀን 120ውን ቤተሰብ ይዟቸው ወደ ቢታንያ ወጣ:: በዚያም እስከ ሊቀ ዽዽስና ድረስ ሾሟቸው: ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡም አዟቸው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ጠብቁ ብሏቸዋል:: እየባረካቸው በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑ አርጉዋል::

+ሰማያት: ምድር: ደመናት: ነፋሳት: መባርቅትና መላእክት: ፍጥረት በሙሉ አመስግኗል:: አይሁድ መናፍቃን እርገቱን ምትሐት ነው እንዳይሉ: ጌታችን ትንሳኤውን አማናዊ እንደሆነ ለማስረዳት በ40ኛው ቀን ዐረገ::

+አንድም ራስ ባለበት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊኖሩ ይገባልና ጌታችን ዕርገቱን በገሃድ አደረገው:: "ዐርገ እግዚእ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን" እንዲል::
<<ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ::
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን::
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ:: >> (መዝ. 46:6)
=>ከበረከተ ዕርገቱ ይክፈለን::

+"+ እስከ ቢታንያም አወጣቸው:: እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው:: ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ:: ወደ ሰማይም ዐረገ:: እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ:: +"+ (ሉቃ. 24:50-53)
<<< ስብሐትለእግዚአብሔር >>>
8.0K views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-24 06:39:30 ኪዳነ ምህረት

ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃልኪዳን ማለት ነው፡፡በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው፡፡


  እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ ክርስቶስ መካነ መቃብር ጎለጎታ እየወረደች ትፀልይ ነበር፡፡ ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችው ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ የምህረት ቃል ኪዳን ገባለት ፡፡


እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ፣ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ ቃልኪዳን አደረገ፡፡
« ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ። … » መዝ, 89 : 3 እንዲል መፅሐፉ፡፡

ስሟን ለሚጠሩ፣ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት ቃልኪዳን ሰጥቷታል ፡፡

ታላቁ መፅሐፍ እንዲህ ይላል፦
". . . ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ። " ኦሪት ዘፍ. 9 : 16

በዚህም መሠረት ቃልኪዳኗን ምክንያት በማድረግ ኪዳነ-ምህረት እያልን እንጠራታለ

እንኳን ለ«ኪዳነምህረት» አደረሳችሁ። የእመቤታችን ምህረት እና ረድዔት፤በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!!!
         @ortodoxslijoch
         @ortodoxslijoch
6.7K views03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-22 17:59:16 ቅዱስ ሲኖዶስ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ ወሰነ፤
*ዕጩዎች ለሰኔ 30 ቀርበው፣ ሐምሌ 9 ቀን ይሾማሉ፣

የቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ አከራካሪውን የኤጲስ ቆጶሳት ሢመት በተመለከተ፣ ዛሬ ሰኞ፣ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በነበረው የቀትር በኋላ ውሎ ከስምምነት ላይ ደርሶ፣ ተከታዩን ውሳኔ አሳልፏል፤
ከዐማራ ክልል አህጉረ ስብከት በቀር፣ ለኦሮሚያ እና ለሌሎች አህጉረ ስብከት የሚሾሙ ዘጠኝ ዕጩዎች ተለይተው እንዲዘጋጁ ወስኗል፤ (በዚህ መሠረት ለኦሮሚያ አህጉረ ስብከት ሰባት ኤጲስ ቆጶሳት ለደቡብ ደግሞ 2 ኤጲስ ቆሳት፤ በድምሩ ዘጠኝ ይሾማሉ)

- ከኦሮሚያ አህጉረ ስብከት በተጨማሪ ደቡብ፣ ሶማሌ፣ አሶሳ እና ድሬዳዋ አህጉረ ስብከት ነው የአሁኑ ሹመት የሚካሔደው። የዐማራ ለቀጣይ ጥቅምት ምልዓተ ጉባኤ ተጠንቶ እንዲመጣ ነው የወሰነው።

- አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአባልነት የሚገኙበት የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ሠይሟል፤ እነርሱም፦ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ(ሰሜን ወሎ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ)፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ(የሐዲያ ከምባታ እና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ) እና ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ(የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ምሥራቅ አፍሪቃ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ) ይገኙበታል፤

- አስመራጭ ኮሚቴው እስከ መጪው ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ዕጩዎቹን ለይቶ ያቀርባል፤
- ዕጩዎቹ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተገምግመው እንዲሽሙ ከተወሰነ በኋላ በዓለ ሢመቱ ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅዱስ ፓትርያርኩ አንብሮተ እድ ኤጲሴ ቆስነት ሢመቱ ይፈጸማል።

- በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ምልዓተ ጉባኤ ደግሞ፣ የዐማራ ክልልን ጨምሮ ለሶማሌ፣ ድሬዳዋ፣ ቄለም ወለጋ እና አሶሳ አህጉረ ስብከት ለመሳሰሉት ተጨማሪ የኤጲስ ቆጶሳት ሢመት እንደሚኖር ተመልክቷል።
6.9K views14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ