Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxslijoch — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxslijoch — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxslijoch
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.17K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ምንማማርበት :መዝሙር: ስብከቶች ይተላለፋል !

መንፈሳዊ ትምህርቶች : መንፈሳዊ ጥያቄዎች : ስብከት : መዝሙር : ይቀርብበታል #ጉዞው ገዳማት #ሰማህታት ታሪክ ይቀርባል!
FacebookGroup : ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ይቀላቀሉ ::

#shear

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-01-23 18:11:56 ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

ከየአቅጣጫው የምትገፋ
ከየአቅጣጫው የሚሴርባት
ከየአቅጣጫው የምትሰደብ
ከየአቅጣጫው የምትንገላታ

ነገር ግን

ከየአቅጣጫው ትክክል የሆነች
ከየአቅጣጫው እንከን የማይወጣላት
ከየአቅጣጫው ውበቷ የበዛ
ቅድስት ርትዕት ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ !!!

ኦርቶዶክስ ያደረከኝ አምላክ ክብር እና ምስጋና አምልኮት እና ውዳሴ ላንተ ይሁን!
አሜን
7.8K views15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 20:10:49 #የጋብቻ_ሕግጋት_ ~~~ #ሼርርርርርርርር

1.ከተጋቡ በኅላ አንድ አካል ናቸው። (ማቴ 19:4-6
2.መፋታት ክልክል ነው። (ሚል2:14)
3.አንድ ወንድ ለአንድ ሴት ። 1ኛ ቆሮ 7:2
4.የሚገባቸውን ሁሉ ማድረግ።
5.ባልም ለሚስትም በራሳቸሁ ሥልጣን የላቸሁም። 1ኛ ቆሮ 7:4
6.ኃላፊነትን መወጣት። ኤፌ5:20-23 ቆላ 3:18
7.ለጾምና ለጸሎት ካልሆነ አለመለያየት 1ኛ ቆሮ7:5
8.ሥጋዊ ጌጥ አለማብዛት ።1ኛ ጴጥ 3:1-4
9.ድንገተኛ ግጭት ቢከሰት ወዲያው መታረቅ።1ኛ ቆሮ 7:10-11
10.በሞት ካልሆነ አለመለያየት።1ኛ ቆሮ 7:39 እናሮሜ 7:2-3
ከሥጋዊ መንፈሳዊ የጋብቻ ዘመድ አለማግባት።ዘሌ 18:6-20 ዘሌ20:16-21፣ማር 6:17።

: #አታግባ
የህይወት ምንነት ሳታውቅ አታግባ
የትዳርን ምንነት ሳታውቅ አታግባ
የትዳር አጋርህን ሀቅ (መብት) ሳታዘጋጅ አታግባ
በችግር ሰዓት ህይወትን አብረህ ልትገፋ ምትችል ሴት ሳታገኝ አታግባ
ኃላፊነትህን እንዴት መወጣት እንዳለብህ ሳታቅ አታግባ
ለልጆችህ ተምሳሌት መሆን ሳትችል አታግባ

#ትዳር
ትዳር ማለት 1ወንድ አንድ ሴት
ትዳር ማለት 1እምነት አንድ እውነት
ትዳር ማለት 1እሳት አንድ ውሃ
ትዳር ማለት 1 ሙሉ አንድ ጎዶሎ
ትዳር ማለት 1መጥፎ አንድ ጥሩ
ትዳር ማለት 1 ጉልቻ አንድ ድስጥ
ትዳር ማለት 1ወንዝ አንድ ውሃ የሚቀዳ ቢሆንም
ካልተንከባክበውና ካልተቻቻልንበት ሊደርቅ የሚችል #ወራጅ

#ወንዝ ነው።
ደግ ሴትን ባሏ ያመሰግናታል፤
የሕይወት ዘመኑም እጥፍ ይሆናል።
ቅን ሴት ባሏን ደስ ታሰኘዋለች፤
ዘመኑንም በሰላም ይጨረሳል።
የደግ ሴት ዕድሏ ያማረ ነው፤
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውንም ወደ
ዕድሉ ታደረሰዋለች
መፀሐፈ ሲራክ 26:1~3

በፍቅር ያማረ ትዳር ሠላም ያለው እውነተኛ ፍቅር ፈጣሪ ይስጠን

አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
join @ortodoxslijoch
9.1K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 17:29:45 ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ ።

መግለጫውን የሰጡት # ብፁዕ_ወቅዱስ # አቡነ_ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት:

# ብፁዕ_አቡነ_አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አሥኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ : በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።

ቅዱስነታቸው ዛሬ ማለዳ በተሰማው ሕገ ወጥ "ሢመተ ጳጳሳት" ጉዳይ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ በሕገ ወጥነት የተከናወነ መሆኑን በመግለጽ :-

1. በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል።

2. መንግሥት ክስተቱ በሀገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ ሕጋዊ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

3. ምዕመናን ቤተክርስቲያንን ከመቸውም ጊዜ በላይ በንቃት እንዲጠብቁ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።
Join @ortodoxslijoch
7.5K viewsedited  14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 09:29:39 #ቤተ_ክርስቲያን_የመሳለም_ሥርዓት

ጠዋትና ማታ ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም መትጋት ያስፈልጋል። (ምሳ.8:34)
ወደ ቤተክርስቲያን ሲገባ ከቅፅረ ቤተክርስቲያን በር ላይ ሲደርሱ መሳለም ይገባል።

መዝ.28፥2፣ 95፥9፣ ኤር.26፥2፣ ሕዝ.46፥3፣ ፊልጵ 2፥9-10
ሁላችሁም አስተውሉ ስንሳለም እንደት ነው????

መጀመሪያ ቀኝ እጅን ላይ ዋ ጣታችንን ቀጥ እናደርጋለን
ከዛ እረጅም ወይም የመሀል ጣታችንን እጥፍ እናደርጋለን ከ ዋ ጣት ጋር ስናገናኘው መስቀል ይሰራል ከዋላ ያሉትን ሁለት ጣቶች እንዲመቸን አጠፍ አጠፍ እናደርጋቸዋለን።

#ምሳሌያቸው

በቀኝ እጅ መሳለማችን ገነትን በመሻት ወይም እግዚአብሔር በገነት ስለሆነ ያለው ገነትን ለማመልከት ነው።

መስቀል መስራችን ደግሞ መዳናችንን ለማመልከትና እንደተሰቀለ ለመመስከር ነው።

ስንሳለም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ማለት አለብን።
ትርጉሙም፥ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ነው ማለት ነው።

ስንሳለም፥ መጀመሪያ መስቀል እንደሰራን በቀኝ እጃችን ግንባራችን ላይ እናደርጋለን።

#ምሳሌው፥ እግዚአብሔር በሰማይ እንደሚኖር እንደማይመረመር ለመግለፅ ነው።

ከዛ፥ ወደ ታች እደረታችን እና ሆዳችን አካባቢ እናደርጋለን።

ምሳሌው፥ ጌታ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም መወለዱን ለመግለ ነው።

ከዛ፥ ወደ ግራ ጎንአችን ከጡታችን በላይ እናደርጋለን።

#ምሳሌው፥ አዳም አባታችን የሞትን ሞት እንደሞተ እና ሲኦል እንደ ገባ ለመግለፅ ነው።

በመጨረሻም፥ ወደ ቀኝ ጎናችን እናደርጋለን።

#ምሳሌው፥ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ከገነት ይዞ ጠላታችን ዲያቢሎስን አስፎ ወደ ገነት መግባቱን ለመግለፅ ነው።

ወደ ቤተክርስቲያን ሲገቡ ጫማን አውልቆ ወገብን ታጥቆ አደግድጎ መግባት ነው። ጫማ አድርጎ ቤተ ክርስቲያን መግባት ክልክል ነው።
ዘፀ 3፥5- ዮሐ.ሥ 7፥33
ኢያ 5፥ 15 ፍት፡መን፡12

ሃሳብን በመንፈሳዊ ነገር ወስኖ ወደ ውጪ ወደ አለማዊ ነገር እንዳይሄድ መግታትና መቆጣጠር ያስፈልጋል።
ከካህን ቀርቦ መስቀል መሳለምና በረከትም መቀበል ያሻል።

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተስለው የሚገኙትን የሥላሴን ፣ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ፣ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ፣ የመላእክትን ፣
የነቢያትን ፣ የፃድቃንን ፣ የሰማዕታትን ፣ የደጋጎች ቅዱሳንን ሥዕሎች እጅ መንሳትና የአክብሮት ስግደት መስገድ ይገባል።

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አስተውሉመሳቅ
ሥለ አለማዊ ሥራ መነጋገር ክልክል ነው።

ከገቡ በኋላ:ዝምታ:ፀጥታ
ፍርሃት የእግዚአብሔርን ምህረት በጥብዓተ ልብ መፈለግ አለብን።

ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን የመዘምራንን ማሕሌት፣ የቅዱሳን መላእክትን ምስጋና ፣ የነቢያትን ትንቢት ፣ የሐዋርያትን ስብከት መስሚያና የልዑል እግዚአብሔርን ነገር መማሪያ ቦታ ስለሆነች ነው።

ከዚህም በላይ የሥጋ ወደሙ ምስጢር የሚፈፀምበት ቦታ ስለሆነች ነው።
ዘሌ. 26፥2

#አስተውሉ
አጭርና ያደፈ ልብስ ለብሶ ወደ ቤተክርስቲያን መሔድ ክልክል ነው። ረዘም ያለ እና ንፁህ ልብስ ለብሶ መሔድ ያስፈልጋል።
ዘፀ. 19፥10-11

በተለይ #ሴቶች እራሳችንን ተከናንበን እንዲንፀልይ ታዘናል።

በመጨረሻም ወደ ቤተክርስቲያን ባዶ እጅ መሔድ አይገባም ። መባዕ፣ ምፅዋት ይዞ መሔድ ይገባል። ዘጸ.34፥20
ወሰብሐት ለእግዚአብሔር
shear አርጉት!
Join @ortodoxslijoch
7.8K views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 21:19:43 ቃና ዘገሊላ ምንድን ነው ?
ቃና ዘገሊላ በቀጥታ ትርጉም የገሊላዋ ቃና ማለት ነው ።

እንደ
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አስተምሮ በጥምቀት
በአል ማግስት ጥር12 ቀን የቃና ዘገሊላ በአል ይከበራል ።ይህ
በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በድምቀት የሚከበር
መፀሀፍ ቅዱሳዊ በዓል ነው ።በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ
ያገኘው ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስየገሊላ ሀገር ክፍል
በምትሆንቃና በተባለች ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት ነው ።

ቃና ዘገሊላ ምን ተፈፀመ ?
ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በምትሆን
በቃና በዶኪማስ ቤት ሠርግ ላይ ከእናቱ ከድንግል ማርያም
ጋርተገኝቶ ነበር ። "ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዙእ ኢየሱስ" የጌታ
የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች "እዳለ ቅዱስ ዮሐንስ 2፥1 ።
እመቤታችን ለሠርገኞቹ ዘመድ ነበረችና ከልጃ ከወዳጃ ከኢየሱስ
ክርስቶስ ጋር በሠርጉ ላይ ታድማ ነበር ።

እናትን ጠርቶ ልጅን
መተው ሥርአት ሥላልሆነ፤በተጨማሪም ደግሞደቀመዛሙርቱን
ከጌታ ጋር ታድመዋል ። ይህም መምህርን ጠርቶ ደቀ መዛሙርቱን
መተው ሥርአት ሥላልሆነ ነው ።
የሠርጉ ስነ ስርአት በሰመረ ባማረ ሁኔታ እየተከናወነ ሳለ ድንገት
የወይን ጠጅ አለቀ ።

አስተናባሪዎቹ በጭንቀት ባህር ስጥመው
ምን እንደሚያደርጉ ግራ በገባቸው በጠበባቸው ጊዜ የችግር ጊዜ
ደራሽ የሀዘን ጊዜ አፅናኝ የሆነችው የአምላክ እናት ድንግል
ማርያም ቅድስ ገብርኤል እንደተናገረ በፀጋ የተሞላች ናትና ሉቃ
1፥28 ማንም ሳይነግራት የልቦናቸውን ጭንቀት አይታ ጎዶላቸውን
ተመልክታ ወደ ልጃ ወዳጃ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወር ብላ "ወይንኬ
አልቦሙ " "ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል" አለችው ። እርሱም
መልሶ "አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም
"አላት ።እመቤታችንም ለአገልጋዮቹ "የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ "
አለቻቸው ።

ጌታም በቦታው የነበሩትን ስድስት ጋኖች ውሀ
ሞልተው እዲያመጡ አዘዛቸው ። ውሀውንም ወደ ወይን ለውጦ
ለሊቀ ምርፋቃት( ለአሳዳሪው) እዲሰጡት አዘዘ ። አሳዳሪውም
ወደ ወይን የተለወጠውን ውሀ በቀመሰ ጊዜ አደነቀ ።

ከወዴት
እደመጣ ስላላወቀ ሙሽራውን " ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን
የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኅላ መናኛውን ያቀርባል አንተ
ግን መልካሙን እሰከ አሁን አቆይተሀል"አለው ። ወይኑም በስው
እጅ ያይደል በሰማያዊው አባት የተዝዘጋጀ ሰለነበር ጣፋጭ እና
ልብን የሚያስደስት ነበር ።

"አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ?" ይህንን የጌታችንን ንግግር
ብዙዎች በዘመናችን ሣሣቱበት ይታያንል ። ክብር ይግባውና
አምላካችን ይህንን የተናገረው እናቱን ሊያቃልል ሽቶ አይደለም ።
ስለሆነም ከመፀሐፍ ቅዱስ አንፃር ይህንን አረፍተ ነገር መመልከቱ
በጣም ጠቃሚ ነው ። በተናጥል ስንመለከት "አንቺ ሴት " ሴት
የሚል ቃልየፆታ መጠሪያ ነውና በፆታዋ አክብሮ ሲጠራት ነው ።

በሌላ በኩል ደግሞ ሔዋን ከአዳም በተፈጠረች ጊዜ አዳም
እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር "ይህቺ አጥንት ከአጥንቴ ናት ስጋዋም
ከስጋዬ ናት እርሳም ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል "ዘፍ.2፥23
በመሆኑም ጌታችን አንቺ ሴት ማለቱ ከስጋዋ ስጋ ከነፍሳ ነፍስ
መንሳቱን ለማጠየቅ ነው ።

" ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ?"የሚለውን አረፍተ ነገር የንቀት
ሰለመስለን ብቻ የዳቦ መልክ የያዘ ድንጋይ ፤ ዳቦ ነው እደማይባል
የንቀት ንግግር ነው ልንል አይገባም ። ጌታም እዲህ ሲል
ውሀውን ወይን እድርግላቸው ብትይኝ አላደርግም እልሽ ዘንድ
ከአንቺ ጋር ምን ፀብ አለኝ ማለቱ ነው።

ድንግል ማርያም አማላጅነት በገሊላ ቃና ጌታችን መድሀኒታችን
ኢየ�ሱስ ክርስቶስ በሠርግ ቤት ሳለ የወይኑን ማለቅ
የማይመለከት ሆኖ አይደለም ። ነገር ግን የእናቱን የድንግል
ምርይምን አማላጅነት ሊገልጥ ስለ ወይኑ ማለቅ እስክትነግረው
ድረ�ስ አንዳች ነገር አላደረገም ። ኅላ ግን የጭንቅ አማላጅ
ድንግል ማርይም ስለ ወይኑ አስብች ልጃ ወዳጃን ለመነች ።

እር�ሱም የእናቱን ልመና ተቀብሎተአምራቱን ፈፀመ ።
እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሳይነግራት በልብ ያለውን
የምታቅ የምትመረምር እናት ናትና የሰርጉ አስተባባሪዎች ይህ
ጎደለ ሳይላት የልቦናቸውን ሀዘን ተመልክታ ከልጃ ከወዳጃ
አማልዳ የጎደላቸውን ሞልታለች ።

ያሰጨነቃቸውንም አርቃለች
በችግራቸውም ደርሳላቸዋለች ። ታዲያ ሳይነግራት የልቦናን አይታ
ከማለደች ስሟን ጠርተው ለሚለምኗትማ እንዴት አብልጣ
አታማልድ ?

ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤቷን
በረከቷንያሳድርብን አሜን !!!

join @ortodoxslijoch
1.3K viewsedited  18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 09:46:28 "ውኃ ሽቅብ አይፈስስም" የሚል አባባል አለ:: ዛሬ ግን ውኃ ሽቅብ ፈሰሰ:: ፈጣሪም በውኃ ተጠመቀ::

ዛሬ ውኃ በውኃ ተጠመቀ:: "የሕይወት ውኃ እኔ ነኝ" ያለው ጌታ በዮርዳኖስ ውኃ ተጠመቀ::

ዮርዳኖስ የንዕማንን ለምፅ ያነፃ ወንዝ ነበር:: ዛሬ ሊጠመቅ ወደ እርሱ የወረደው ግን "ንጻ" ብሎ ለምፃምን በቃሉ የሚያነጻ ጌታ ነበር:: ለጌታም ጌታ አለው:: ዮርዳኖስ አፍ የላትም እንጂ ንጹሑ ጌታ ወደ እርስዋ ሲገባ እርስዋ ንዕማን ሆና "ጌታዬ ሆይ አንጻኝ" ልትል ምንም አልቀራት::

"አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽ፥ ምን ሆናችኋል?" መዝ 113:5 እንዳለ ነቢዩ ዛሬ የመጣባት እንግዳ እንደ ንዕማን የሚነጻ ሳይሆን ከዮርዳኖስ ውኃ ይልቅ ግን እርሱ ንጹሕ ነበር::

ዮርዳኖስ በኢያሱ ዘመን የሊቀ ካህናቱ እግር ሲረግጠው የተከፈለ ወንዝ ነበር:: በኤልያስና በኤልሳዕ መጎናጸፊያም ሁለት ጊዜ ተከፍሎ ነበር::

ዛሬ የሐዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት ክርስቶስ ወደ ዮርዳኖስ ሲወርድ የዮርዳኖስ ልብ በፍርሃት ተከፈለ:: በዕለተ ሰኑይ ውኃን ለሦስት ከፍሎ ሐኖስ ጠፈር ውቅያኖስ ያደረገው አምላክ ወደ እርስዋ ሲመጣ ትንሽዋ የዮርዳኖስ ወንዝ ተጨነቀች:: በውኃ ላይ ሰፍፎ የነበረው መንፈስ ቅዱስ በርግ አምሳል ሲመጣባት ዮርዳኖስ ይኼን ሁሉ መሸከም አትችልምና ተጨነቀች::

"አቤቱ፥ ውሆች አዩህ፥ ውሆችም አይተውህ ፈሩ፤ ጥልቆች ተነዋወጡ፥ ውኆችም ጮኹ" መዝ. 77:16

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥምቀት 2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
ፎቶ :- በዮርዳኖስ ወንዝ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! በኮሜንት መስጫው ሥር ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-

የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
የቴሌግራም ቻናል : https://t.me/deaconhenokhaile
የዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
1.0K views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 08:51:31 #የምወደው_ልጄ_ይህ_ነው!!

በጥምቀት በዓል በታላቅ ፍቅር ሲያመሰግኑ በነበሩት ወጣቶች አንጻር የሚከተለው #ተግሳጽ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ- "የምወደው ልጄ ይህ ነው!"
<< የምወደው ልጄ ይህ ነው! ባንተስ ደስ የምለኝ መቼ ነው?? >>
( በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ)

በእርግጥ ያንተን ያህል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ መውጣት አይችልም፤ ኦሪት ዘፍጥረት የቱ ጋር እንደሆነ, ዜና መዋእልም የት እንደሚገኝ አያውቅም። ምናልባት ከራእይ ዮሐንስ ሀይለ ቃል ለማንበብ መዝ.ዳዊት ላይ ገልጦ ይዳክር ይሆናል፤ ምንም ምስጥር አያውቅም፤ ለአንድምታው,ለትርጓመውም እንግዳ ይሆናል፤ መላእክት ጻድቃን ሰማዕታትን አይለይም።

ጊዮርጊስ ሰማዕቱን ከመላእክት አንዱ አድርጎ ያስበዋል፤ ለየትኛውም ሃይማኖታዊ ጥያቄ መልስ መስጠት አይችልም፤ ዛሬም የእርሱ ጥያቄ ዓሣ ፆም አለው ወይስ የለውም ? የምል ልሆን ይችላል፤ በማህሌት እና በሰዓታት በቅዳሴና በወረብ መካከል ያለው ልዩነት አይገባውም! ለእርሱ በቤ/ክን ውስጥ የሚሰማ ዜማ ሁሉ ቅዳሴ ነው፤ ስለ ስርዓተ ቤ/ክን ምንም አያውቅም በእርሱ አስተሳሰብ በፆም ቀን ፀበል መጠጣት ፆሙን አያፈርስም፤ የምያማትበውም አንተ በምታውቀውና በምታብራራው ሥርዓት ሳይሆን እጅን በማወዛወዝ ልሆን ይችላል፤ የሰንበት ት/ቤትን ተከታታይ ት/ት አልተማረም ፤ በጉባኤ አባልነትም አልተመዘገበም፤ በየትኛውም ምድብ አያገለግልም፤ ከየተኛው መንፈሳዊ ት/ቤት አልተመረቀም፤ ይሁንና የምወደው ልጄ ይህ ነው።

የሚዘምረው መዝሙርም ሥርዓተ ቤ/ክን ያልጠበቀ ነው፤ ሽብሸባውም እንዲሁ፤ አለባበሱም ብዙ ጉድለት አለበት፤ ነጠላውን እንደዋዛ ይጠመጥመዋል እንጅ በትምህርተ መስቀል አያደርግም፤ አረማመዱም የምንፈሳዊ ሰው አይደለም ፀጉሩን የተንጨባረረ እና የተጠቀለለ ነው፤ የምውልበት ሥፍራ መልካም ላይሆን ይችላል፤ በሰው ሁሉ የተጠላ የተተፋ፤ ይሁን ግን ልንገርህ -የምወደው ልጄ ይህ ነው።

አናንያ ሆይ < የሳኦልን ክፉ አትንገረኝ ፤ የእርሱን የቀደመ ጭካኔውንና በሰው ዘንድ ያለውን ክፉ ስም አትንገረኝ፤ ጌታ ሆይ መጥፎ ነው >እያልክ አትወትውተኝ ሁሉንም አውቀዋለሁ፤ ነገር ግን ካንተ ይልቅ የሚሰማኝ የምፈራኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው።

አንተ በቤቴ ኖረህ ሳትሰማኝ ቃሌንና ትእዛዜን ተለማምደህ ቸል ብለህ ስትኖር፣ የተናገርኩትን ትእዛዝ ቸል ሳይል የምፈፅም የእኔ ምርጥ እቃ- የምወደው ልጄ ይህ ነው።
አንተ የለመድከውን አንተ የተዳፈርከውን መቅደሴን በሩቅ እያየ የምፈራ የምንቀጠቅጥ ሳነሳው የምነሳ ሳስቀምጠው የምቀመጥ ምርጥ እቃዬ -የምወደው ልጄ ይህ ነው።

እርግጥ ነው ዜማ አያውቅም እኔን ግን ያውቀኛል፤ ምንም ጥቅስ አልያዘም ትህትናን ግን ይዙዋል፤ የቅዳሴን ተሰጦ አይመልስም እኔ ስጠራው ግን ይመልስልኛል: እኔ ግን ይፈራኛል: ስለ ስሜ ስተጋ አይታክትም፤ ስለ ክብሬ ሲንከራተት አልተማረረም፤ ያንተን ቸልተኛውን ትእዛዝና ተገሳፅ በትህትና ተቀበለ እንጅ እኔን አክብሮ አከበረህ እንጅ ለታቦት ማለፍያ መንገድ ስደለድል፤ ቆሻሻ ሲዝቅ አፈር ሲሸከም ካንተ ያገኘውን ጥቅስ በየመንገዱ ሲሰቅል ድንጋይ ሲሸከም በፊቱ ላይ ደስታን እንጅ አንዳች ምሬት አላየሁበትም። ስሜታዊ ሆኖ ነው: ስላልበሰለ ነው አትበለኝ የቤቴ ቅናት የምትበላው ለእኔ የታመነ የምወደው ልጄ ይህ ነው።

ስሜታዊ መሆንስ እንዳንተ ማንቀላፋት ነው፤ መብሰልስ ቸልተኝነት ነው ስምኦን ሆይ ስለሱ አንዳች ክፉ አትንገረኝ ኃጥአተኛ ነው እንድህ አድርጓል አትበለኝ አንተ ያልሠራሀውን አልሠራም እኔ ያየሁትን ክፋቱን አይደለም፤ በንስሐ በትህትና ማጎንበሱን ነው። ለክብሩ ሳይሳሳ በእንባ እግሮቼን አጥቧል ምንጣፍ አንጥፎ ሳር ጎዝጉዞ በአደባባይ ከፊቴ ስደፋ ያን ጊዜ ነው የልጄን ልብ ያየሁት:: ስለሱ አንዳች ክፉ አትንገረኝ - የምወደው ልጄ ይህ ነው።

አንተ መዘመር ሰልችቶሃል ፤ ማጨብጨብም ደክሞሃል፤ እርሱ ግን ስያመሰግን ብውል ብያድር አይጠግብም። ምናልባት ጀማሪ ስለሆነ ነው ትል ይሆናል፤ አንተ ፈፃሚ ስለሆንክ ነው የተሰላቸህው? አንተ መዝሙር ምታጠናው ከበሮ ለመምታት ብቻ ይሆናል ፤እርሱ ግን በባዶ እጁ በማመስገኑ ደስተኛ ነው። አንተ እንዴት እንደምሸበሸብ እያወክ ታበላሸዋለህ ፤ እርሱ ግን ላገኘው ሁሉ እንዲህ ነው የሚሸበሸበው እያለ ይጨነቃል፤ ልክ ነህ ጀማሪ ነው፥ ስሜታዊ ነው፤ ያልበሰለ ነው ፤ ነገር ግን የምወደው ልጄ ይህ ነው። ባንተ ደስ አልተሰኘሁም፤ በተማርኸው መጠን አልኖርክም በዘራሀው መጠን አላፈራህም፤ ስለ ቅናቱ በእርሱ ደስ የምለኝ - የምወደው ልጄ ይህ ነው። ባንተስ ደስ የምለኝ መቼ ነው????????????

ይህን የእግዚአብሔር ተግሳጽ ከመቀበል ጋር አንድ መልእክት ይቀራል:: እነዚህ ወጣቶች ቀድሞም በቃለ እግዚአብሔር ተኮትኩቶው አላደጉም:: ምንም በጥሩ ምግባር ባይታወቁም በልባቸው ግን እንደ እሳት የሚንቀለቀል ሃይማኖት አላቸው:: ፈሪሃ እግዚአብሔር አላቸው::

እኛ ወደ እነርሱ ባንሄድ እነሱ ግን ወደኛ መጥተዋል:: ሌላ ምን እንላለን:: ነብዩ <መንፈሱ ሰብስባቸዋልና ከነዚህ አንድ አትጠፋም > እንዳለ ያለ ቀሽቃሽ የሰበሰባቸው የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲጠብቃቸው እንዲያጸናቸው እንመኛለን:: በጎች ኑረው በረት ጠበባ አይባልምና ቤተ ክርስቲያንም መዋቅሯን አጠናክራ እንደምትቀበላቸው ተስፋ እናደርጋለን::

ለወጣቶቹ ግን < ምንነው ለጥምቀት ብቻ > ከሚል ምክር ጋር አንድ ቃለ ሐዋርያ እንጥቀስ::
" እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለም። " ዕብራውያን 6፥10

ወጣት ሆይ! አንብበህ ስታበቃ ተገሳፁ ላንተ እንደሆነ አስተውል!! "እኛስ ለታቦት ሥራ አለብን" ብለው እራሳቸውን ዝቅ ያደረጉ ወንድሞችህ "የምወደው ልጄ ይህ ነው" ተብለዋል። አንተም ከእነርሱ ተማርና የምወደው ልጄ አንተ ነህ ለመባል ያብቃህ!
[ጸሐፊ :- ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የምወደው ልጄ ይህነው !
1.5K views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 10:43:37 ረቡዕ ጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም

#ጾመ_ገሃድ /ጾመ ድራር ጥምቀት/
ገሃድ ማለት የቃሉ ትርጉም መግለጫ፣ ግልጥ፣ ልዋጭ፣ ይፋዊ በገሃደ የሚታወቅ ነገር ማለት ነው።

የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መገለጥን የምናስብበት ነው። አንድም ጋድ ተብሎም ይጠራል፤ ጥምቀት ረቡዕ፣ ዓርብ ቢውል በዚያ ለውጥ ማግሰኞና ሐሙስ ይጾማልና።

ጋድ /ጾመ ድራር ጥምቀት/፦ ይህ ጾም የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት በማሰብ የጥምቀትን ዋዜማ ከምግብ መከልከል ነው። የሚቆርብ ሰው አክፍሎ የሚያድር ስለሆነ የጥምቀት ድራር /ዋዜማ/ ጾም ነው።

የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ዕለት በሚውልበት ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ ማግሰኞንና ሐሙስን በመጾማችን ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል። በዚህም የጾምና የበዓል ማክበር ይከናወንልናል።

የጥምቀት ዋዜማ ሰኞ፣ ማግሰኞ፣ ሐሙስ ከሆነ ጾም ነው፤ በአጋጣሚ ደግሞ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ከጥሉላት ምግቦች ብቻ ይጾማል።

ሆኖም ጥምቀት በየትኛውም ዕለት ቢውል በየዓመቱ ሁልጊዜ የጥምቀትን ዋዜማ እስከ ዕርበተ ፀሐይ እንጾም ዘንድ አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብንና ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ይሆን ዘንድ ሥርዓትን ሠርተውልናል።

ስለሆነም በ2015 ዓ.ም የጌታችን በዓለ ጥምቀት ጥር 11 ቀን በዕለተ ሐሙስ ስለሆነ ጾመ ጋድ /ገሃድ/ ጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም በዕለተ ረቡዕ ይሆናል ማለት ነው። ዕለተ ረቡዕ ራሱን የቻለ የጾመ ድኅነት ቀን ሲሆን በዚህ ዓመት ጾመ ገሃድ በዚህ ዕለት ውሏልና ዕለቱ ጾመ ድኅነትና ጾመ ገሃድ የተገጣጠሙበት ዕለት ሆኗል።

“መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም’’ 1ኛ ቆሮ. 8፥8
በሰላም በጤና አድርሶ ጾሙን ጾመን የጌታችንን በዓለ ጥምቀት እናከብር ዘንድ የእርሱ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፤ አሜን።
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር፤ አሜን።

ምንጭ፡ ሰባቱ አጽዋማትና ታሪኮቻቸው በመ/ር ኃ/ሚካኤል ተፈራ
ጥር 8 ቀን 2015 ዓ.ም
Join @ortodoxslijoch
2.3K viewsedited  07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 08:43:48 ከተራ ምንድን ነው?

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በዋዜማው የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል
Join @ortodoxslijoch
647 views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 07:02:53 የቀጠለ

ውድ የተዋህዶ ልጆች እንኳን ለጌታችን ለመድሃንታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት ዋዜማ የከተራ በዓል በሰላም አድራሳችሁ ።ጥምቀት ማለት ምን ማለት ነው?

ጥምቀት በግእዝ ልሳን(አጥመቀ አጠመቀ ነከረ) ካለው ግስ የተገኘ ነው ። ትርጉሙ መላ ሰውነትን በውሃ ውስጥ መንከር ወይም ማጥመቅ ማለት ነው።

2 ጥምቀትን የጀመረው ማነው?
እውነተኛዋን ጥምቀት የጀመረው ወይም የመሰረተው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

3 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛዋን ጥምቀት የመሠረተው መቼ ነው?
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ከድንግል ማርያም በድንግልና ተፀንሶ በድንግልና ተወልዶ እድሜው 30 ዓመት ያህል ሲሆነው በፈለገ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ መሠረተው(ሉቃስ 3፥21-23)።

የጌታችን ጥምቀት ታሪክ በአጭሩ እንዲህ ነው፦
"ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ዮሐንስ ግን እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተ ግን ወደ እኔ ትመጣለህ? ብሎ ከለከለው ኢየሱስም መልሶ አሁንስ ተው እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈፀም ይገባልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃ ወጣ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሄር መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱም ላይ ሲቀመጥ አየ እነሆም ድምፅ ከሰማይ መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ" (ማቴ 3፥13-17) ማር 1፥9 ሉቃ3፥21 ዮሐ 1፥32።
5 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን በዮርዳኖስ ተጠመቀ?
ቅዱስ ዳዊት የተናገረው ትንቢት ይፈፀም ዘንድ(መዝ 113፥3)።
~ዮርዳኖስ ለጥምቀት ታሪካዊ ምሳሌ ያለው በመሆኑ።
~ዮርዳኖስ ለምስጢረ ሥላሴ ምስጢራዊ መሳሌ ያለው በመሆኑ።
~ዲያቢሎስ በዮርዳኖስ የደበቀውን የአዳምንና የሄዋንን የእዳ የባርነት ደብዳቤ ይደመስስ ዘንድ(መፅሐፈ ቀሌምንጦስ)።

የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በጌታችን የጥምቀት እለት የምንጠመቀው ከጌታ ጥምቀት እረድኤት በረከት እናገኝ ዘንድ ነው።

እግዚአብሔር አምላካችን በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስፋጽማን ዘንድ ቅዱስ ፍቃዱ ይሁንልን ።
በዓሉ የሰላም የፍቅር የአንድነት በአል ያድርግልን አምላክ አሜን።

Join @ortodoxslijoch
1.0K views04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ