2023-01-31 06:08:12
ትምህርት ሃይማኖት (የሃይማኖት ትምህርት)
በሁለት ይከፈላል፡፡
ይኸውም፦
1ኛ፡- ዶግማ
2ኛ፡- ቀኖና በሚል ነው፡፡
#ዶግማ ፡- ቃሉ የግሪክ ሲሆን ፍችውም እምነት ማለት ነው፡፡
#ቀኖና ፡- ደግሞ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ሥርዓት ማለት ነው፡፡
#ዶግማ ወይም እምነት ስንል ምንም ነገር አይጨመርበትም ፤ አይቀነስበትም፤
አይሻሻልም፤ ችግርና ፈተናም ቢመጣ እስከ ሞት ድረስ አጥብቀን የምንይዘው
ነው፡፡
#ለምሳሌ
ያህል ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረ፤ ቢመረምር እንጂ
የማይመረመር ሁሉን
ቻይ አምላክ፤ የሚሳነው ነገር የሌለ ፈጣሪ፤ የሰማይና የምድር ባለቤት
የሠራዊትጌታ ሕያው #እግዚአብሔር ነው፡፡ #እግዚአብሔር (ፈጣሪ) የአካል
ሦስትነት አለው፡፡
በመለኮት፣
በመፍጠር፣
በሥልጣን፣
በአገዛዝ፣ በፈቃድ ግን አንድ ነው፡፡
#በሦስትነቱ
አብ፤
ወልድ፤
መንፈስ
ቅዱስ ሲባል
#በአንድነቱ አንድ # መለኮት አንድ እግዚአብሔር ይባላል፡፡
በአዳም ምክንያት ከመጣው የዘለዓለም ሞትና ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ
የወጣነው ከሦስቱ አካላት በአንደኛው አካል ማለትም በወልድ በኢየሱስ
ክርስቶስ ነው፡፡ ይህ #ዶግማ ወይም እምነት ይባላል፡፡
#ቀኖና ግን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ያደጉ ክርስቲያኖች
የሚመሩበት ሥርዓት ስለሆነ፤ በሃይማኖት #አባቶች ወይም # በቅዱስ
#ሲኖዶስ አማካኝነት እንደጊዜው ሁኔታ #የሚሻሻል በመሆኑ የሚጨመርበት፤
የሚቀነስለት ነው፡፡
#ለምሳሌ
1ያህል እኛ ኦርቶዶክሳውያን የምንጠመቀው ሴት በሰማንያ ወንድ በአርባ
ቀናችን ነው፡፡
የተወለዱ ሕጻናት ሴቷ ሰማንያ ወንዱም አርባ ቀን ሳይሞላቸው
#ቢታመሙና በሽታው አስጊ ከሆነ በ10፣ በ20፣ በ30…ቀናቸው #መጠመቅ
#ይችላሉ ቀኖና ነውና፡፡
2በቤተ ክርስቲያናችን የቀዳስያን ብዛት መነሻው አምስት ነው፡፡ ምናልባት
ከአምስቱ አንዱ፤ ሁለቱ፤ ሦስቱ ቢታጡና ሌላም ተፈልጎ እስከ መጨረሻ
የማይገኝ ከሆነ ከአቅም በላይም የሆነ ችግር ከገጠመ ሁለቱ ወይም አንዱ ብቻ
ቀድሰው ማቁረብ ይችላሉ፡፡ #ቀኖና ነውና፡፡
3በቤተ ክርስቲያናችን
ታቦት ሲከብር ቤተ ክርስቲያኑን የሚዞረው ሦስት ጊዜ ነው ችግር ካለ አንድ
ጊዜ ብቻ ዑደት ተፈጽሞ ሊገባ ይችላል። #ቀኖና ነውና።
#ስለቀኖና ( # ስለሥርዐት )
#ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ እንዲህ ሲል ጽፏል።
፩. ‹‹ነገር ግን ሁሉን በአግባብና በሥርዐት አድርጉ፡፡›› 1ኛ ቆሮ. 14፥40፡፡
፪. ‹‹ወንድሞች ሆይ በሠራንላቸው ሥርዐት ሳይሆን በተንኮል ከሚሄዱት
ወንድሞች ሁሉ ትለዩ ዘንድ #በጌታችን #በኢየሱስ # ክርስቶስ ስም
እናዝዛችኋለን፡፡
#እኛን ልትመስሉ እንደሚገባችሁ እኛም በእናንተ መካከል ያለ ሥራ እንዳልኖርን
ራሳችሁ ታውቃላችሁ›› 2ኛተሰ. 3፥6-7››
#ቀኖና (ሥርዐት) የሚወሰነው በሃይማኖት አባቶች እንደሆነና
#ወንጌልን
የሚስተምር ሰው ለሚያስተምራቸው ክርስቲያኖች በሃይማኖት አባቶች የተወሰነ
ቀኖና ማስተማርና መሰጠት እንዳለበት #መጽሐፍ #ቅዱስ እንዲህ ሲል
ያስረዳል፡፡
በየከተማውም ሲሄዱ፥ ሐዋርያትና ቀሳውስት በኢየሩሳሌም ያዘዙትን /
የወሰኑትን/ ሥርዐት አስተማሯቸው፡፡
#አብያተ ክርስቲያናትም በሃይማኖት ጸኑ ዕለት ዕለትም ቁጥራቸው ይበዛ
ነበር፡፡›› ይላል የሐዋ. 16፥4-5፡፡
በዚህ #የእግዚአብሔር ቃል መሠረት ቅዱስ #ጳውሎስ ደርቤንና ልስጥራን
በተባሉ ቦታዎች ለነበሩ ክርስቲያኖች ወንጌልን ከሰበከ በኋላ #ሐዋርያት
የወሰኑትን #ቀኖና (ሥርዐት) እነደሰጣቸው እንረዳለን፡፡
ስለዚህ ቀኖና ወይም ሥርዐት ቤተክርስቲያንን ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም፡፡
በመሆኑም #ዶግማንና #ቀኖናን ወይም እምነትንና ሥርዓትን ጎን ለጎን ይዞ
መጓዝ ሐዋር
Join @ortodoxslijoch
4.3K views03:08