2023-05-17 06:46:50
«በሚያልፍ ዓለም ውስጥ የማያልፈውን አምላክ_
*_ተስፋህም፣ መከታህም አድርገው_ !*
♡አቤቱ ጌታዬ ሆይ፥
፡
➊.በጥበቤ እንዳልመካ ጥበቤ ይዘነጋኛል፣
፡
➋.በጉልበቴ እንዳልመካ ጉልበቴ ይከዳኛል፣
፡
➌.በሀብቴ እንዳልመካ ሀብቴ እንደ በረዶ ይሟሟል፣
፡
➍.በዝናዬ እንዳልመካ ተረኛ ዝነኛ ይነጥቀኛል፣
፡
➎.በኃይሌ እንዳልመካ ኃይሌ ይዝልብኛል፣
፡
➏.በሰራዊት እንዳልመካ ይበተንብኛል፣
፡
➐.በውበቴ እንዳልመካ ውበቴ ይበላሽብኛል፣
፡
➑.በፍቅሬ እንዳልመካ ፍቅሬ በጥላቻ ይለወጣል፣
፡
➒.በአገልግሎቴ እንዳልመካ የገነባሁትን ላፈርሰው እችላለሁ፣
፡
➓.በወዳጅ እንዳልመካ ከስፍራው አጣዋለሁ፣
፡
➊➊.በትላንት እንዳልመካ አልፎ ተረት ይሆንብኛል፣
፡
➊➋.በዛሬ እንዳልመካ ባሰብሁበት መዋል ያቅተኛል፣
፡
➊➌.በነገ እንዳልመካ ቀን የሚያመጣውን ማወቅ ያቅተኛል፣
:
➊➍.በቅድስናዬ እንዳልመካ ,አንዱን ስደፍን አንዱ ያፈስብኛል።
፡
የምመካበት ያሳፈረኝን የምመካበትን የፈራሁትን፣ የምመካበት ያጣሁትን እኔን ልጅህን ትምክሕት የሆንከኝ ጌታዬ ሆይ ተመስገን።
♡አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ፥
፡
➊.ጽድቅ ለሌለኝ ጽድቅ ፣ ቅድስና ለሌለኝ ቅድስና ፣ ጥበብ ለሌለኝ ጥበብ
የሆንከኝ አንተ ነህ።
፡
➋.ቤዛ ማቅረብ ለማልችል ቤዛ የሆንከኝ ፣ ከሞትም ያዳንከኝ ፈጣሪዬ ሆይ ምስጋናዬ ይድረስህ።
፡
➌.ከሚያባርረኝ ጠላት ፣ ከሚያሳድድ ሕሊና የተማጸንሁብህ የደኅንነቴ ቀንድ አንተ ነህ።
፡
➍.የማትደፈር ምሽግ ሁነህ ከሁሉ የምታድነኝ አንተ ነህ።
፡
➎.የዘራሁት ሲመክን ፍሬን የምትሰጠኝ ፣ የሠራሁት ሲፈርስ አዲስ ገንብተህ የምታኖረኝ አንተ ነህ።
፡
➏.አንተ ትምክሕቴ ነህ። የደኅንነቴም ራስ ነህ። ለሚያልፈው ዓለም ብቻ ሳይሆን ለማያልፈው ዓለምም እሻሃለሁ።
፡
➐.አንተ ካላቅኸኝ የሚያሳንሰኝ ፣ አንተ ከወደድከኝ ከንቱ የሚለኝ ማንም የለም። ቢኖርም ሐሰተኛ ነው።
፡
ዛሬን ያየሁብህ ትምክሕቴ ሆይ ተመስገን።
:
♡አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ፥
፡
➊.በአንተ ላይ እደገፋለሁ፣ በአንተ ላይ እደላደላለሁ፣ የማትነቃነቅ ምሰሶዬ አንተ ነህ።
፡
➋.ከስፍራህ አትታጣም። ስደገፍህ የማትሰበር ምርኩዜ አንተ ነህ።
፡
➌.ስጠጋህ የማትሸሸኝ ወዳጄ አንተ ነህ።
፡
➍.ከፍ የምልብህ ደብሬ አንተ ነህ።
♡አቤቱ አምላኬ ሆይ፥
፡
ካንተ አግኝቻለሁና ከሰው አጣሁ ብዬ አላዝንም። ባንተ ተክሻለሁና ከሰርሁ ብዬ አላጉረመርምም።
:
➊.የቤቴ ብርሃን ፣ የትዳሬም ዘውድ አንተ ነህ።
፡
➋.በረታው ሲደክም፣ የተሾመው ሲሻር አንተ ግን በዘመናት ያው ሁነህ አይሃለሁ።
፡
➌.ያለመድኩት ጠባይህ፣ ይህ ብቻ ነው ብዬ ያልገለጥሁት ማንነትህ የተመሰገነ ይሁን።
:
♡አቤቱ ጌታዬ ሆይ፥
፡
አንተ ልዑል ስትሆን የምረገጥ ጭቃ የሆንሁት እኔ አመሰግንህ ዘንድ መፍቀድህ በእውነት በመደነቅ እንዳመሰግንህ ያደርገኛል።
፡
➊.የገዛ አቅሜ ሲከዳኝ በእርጅናዬ የማትጥለኝ ጓዴ አንተ ነህ።
፡
➋.እስከ ማታ ይቆያል ያሉት በጥዋቱ ሲያልቅ አንተ ግን እንደ በዛህ ትኖራለህ።
:
➌.በክፉ ቀን ይቆምልኛል የምለው ራሱ ክፉ ቀን ሲሆን አንተ ግን በፍቅር ቅላፄ ታናግረኛለህ።
:
➍.ያየኸው እንጂ የገላመጥኸው ማንም የለም። ፊትህን ስትመልስ እደነግጣለሁ ፣ ስምህን ስጠራ ወዲያው አይዞህ ትለኛለህ።
፡
➎.ደስታዬን ፈውሰህ ባንተ እንድደሰት ስለረዳኸኝ ፣ ነፍሴ ከእውቀት ተራቁታ እንዳታስቸግረኝ በብዙ ትምህርት የደገፍከኝ አንተ እንደሆንህ አውቃለሁ።
:
➏.በዚህ ዘመን ስላስነሣሃቸው አባቶችና ካህናት ምስጋና አቀርብልሃለሁ።
Join @ortodoxslijoch
1.8K views03:46