2023-04-14 07:25:46
ሚስጥረ እለተ አርብ ( ስቅለት )
እለተ አርብ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የሚታሰብበት ቀን ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ ያያቸው ስቃይና መከራ ለዓይን የሚዘግንኑ ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ከባድ ቀንን ለእኔና ለእናንተ ፍቅር ሲል አሳልፏል፡፡
" ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ
እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። " ኢሳ. 53 : 7
13ቱ ህማማተ መስቀል
➊ እራሱን በዘንግ ተመታ ፦ ተፉበትም መቃውንም ይዘው
እራሱን መቱት ።《ማቴ 27÷30》
➋ በጥፊ ተመታ ፦ በጥፊም ይመቱት ነበር።《የሀ 19÷4》
➌ ምራቅ ተፉበት ፦ ተፉበትም መቃውንም ይዘው እራሱን
መቱት።《 ማቴ 27÷30》
➍ የሾክ አክሊል ጎንጉነው በእራሱላይ አቀዳጁት 《ማቴ.27፥29 》
➎ መራራ ሀሞት አጠጡት ፦ በሀሞት የተደባለቀ የወይን
ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም ።《ማቴ 27÷34 》
➏ ጀርባውን መገረፉ ፦ በዚያን ጊዜም ጲላጦስ እየሱስን ይዞ
ገረፈው ። 《ዩሀ 19÷1》
➐ ጎኑን በጦር መውጋት፦ ነገር ግን ከጭፈራዎቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው ወድያውም ደምና ውሃ ወጣ።《የሀ 19÷34 》
➑ ወደ ኃላ መታሰሩ ፦ የሾለቃውና ጭፍሮቹ የአይሁድም ሌሎችም እየሱስን ይዘው አሰሩት። 《ዩሀ.18÷12 》
➒ ሳዶር
➓ አላዶር
➊➊ ዳናት
➊➋ አዴራ
➊➌ ሮዳስ
5ቱ #ቅንዋተ #መስቀል ችንክሮች ሳዶር ፣ አላዶር ፣ ዳናት ፣ አዴራ እና ሮዳስ ይባላሉ።
➊ #ሳዶር ፦ ማለት ቀኝ እጁ የተቸነከረበት
➋ #አላዶር፦ ማለት ግራ እጁ የተቸነከረበት
➌ #ዳናት ፦ ማለት እግሮቹ የተቸነከረበት
➍ #አዴራ ፦ ማለት ደረቱን የተቸነከረበት
➎ #ሮዳስ ፦ ማለት ከወገቡ (እብርቱ) አጣብቆ እንዲይዝ
የተቸነከረበት
መከራን ታገሰ
በህይዋንና በሙታን ላይ የሚፈርድ እርሱን እንደበደለኛ
ተፈረደበት
አለምን ሁሉ በቅፅበት የፈጠረ እርሱ በስጋው ሞተ በመለኮት ህያው ሆነ
ጌታችን_መድኃኒታችን_እየሱስ_ክርስቶስ ከ6-9 ስአት በመስቀል ላይ ሳለ የተናገራቸው 7ቱ የፍቅር ቃላት
ኤሉሄ ኤሉሄ ለማስበቅታኒ (አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ ) ማቴ 27÷46
እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ።
ሉቃ.23÷43
አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ። ሉቃ 23÷43
አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው። ሉቃ.23÷34
እናትህ እንኃት እንሆ ልጅሽ:: ዩሀ 19÷26-27
ተጠማሁ። ዩሀ 19÷28
ተፈፀመ። ዩሀ 19÷30
#ጌታችን_መድኃኒታችን_እየሱስ_ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ
የተፈፀሙ 7ቱ ታአምራት
ፅሀይ ጨለመች
ጨረቃ ደም ለበሰች
ከዋከብት ብርሃናቸውን ነሱ
የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከሁለት ተከፈለ
አለቶች ተሰነጣጠቁ
መቃብራን ተከፈቱ
የሞቱት ተነሱ
ክብርና ምስጋና አምልኮት ውዳሴ ስግደት ዝማሪ ይድረሰ ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን_ለእየሱስ_ክርስቶስ
አቤቱ አምላካችን ሆይ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ
አስበን አሜን ፫
መልካም ስግደት
Join @ortodoxslijoch
3.0K views04:25