Get Mystery Box with random crypto!

ሚያዚያ 23/8/2015 # ቅዱስ_ጊዮርጊስ ለሰማዕቱ # ቅዱስ_ጊዮርጊስ አመታዊ የእረፍት መታሠቢያ | ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች

ሚያዚያ 23/8/2015 # ቅዱስ_ጊዮርጊስ

ለሰማዕቱ # ቅዱስ_ጊዮርጊስ አመታዊ የእረፍት መታሠቢያ ክብረ በዓል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን
ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቱ የፍልስጤም መኮንን ዞሮንቶስ (እንስጣቴዎስ) እናቱ ደግሞ (አቅሌሲያ) ቴዎብስታ ትባላለች በፍልስጤም ልዳ ጥር 20 በ277 ዓ.ም ተወለደ ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ ብሩህ ሀረገ ወይን ፀሐይ ዘልዳ ማለት ነው

ቅዱስ ጊዮርጊሰ በፋርስ በኢራን ዱድያኖስ የተባለ ንጉሥ ነገስታቱን ሰብስቦ ሰባ ጣኦታትን ሲያሰግድ ተመለከተ በዚህን ጊዜም ቤተ መንግስት ድረስ በመገስገሰሰ ተቃውሞውን በማሰማት ክርስቲያን መሆኑን መስክሯል ከዚህም በኋላ በተለያዩ ነገስታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰው ህሊና ሊታሰቡ የማይቻላቸው አስራ ዘጠኝ መከራዎች ደርሰውበታል ቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስት ጊዜ ሞቶ ሶስት ጊዜ ተነስቷል የእግዚአብሔር ተአምር በተደጋጋሚ ተገልፆለታል

የቅዱስ ጊዮርጊስ መከራ በጥቂቱ፦ክርስቲያን በመሆኑ ብቻ ወደ እስር ቤት ተወረወረ፤እጆቹና እግሮቹ ታስሮ ተገረፈ ፤የብረት ጫማ አጥልቀው አስኬዱት፤ከብረት አልጋ ላይ አስተኝተው እሳት አነደዱበት፤እጆቹን የኋሊት አሰሩት፤በመጋዝ ለሁለት ሰነጠቁት

የጋለ ሳህን ከጭንቅላቱ ላይ አስቀመጡበት፤ሰውነቱን በጩቤ ፈተፈቱት፤ችቦ እና እሳት አንድደው በግራና በቀኝ አቃጠሉት
ምላሱን በቢላዋ ቆረጡት፤በአፍንጫው ቀዳዳዎች በሚስማር መተው ቸነከሩት፤በመጥረቢያ ፈለጡት፤ቅጥራን አፍልተው በጭንቅላቱ ላይ ደፉበት፤በበሬ አስረው ጎተቱት፤ጥርሶቹን በጉጥ አስረው ነቃቀሉት፤ከብረት ድስት ውስጥ ጨምረው ቀቀሉት፤አስጎንብሰው አሸዋ ጫኑበት፤ከእንጨት ላይ አንጠልጥለው በእሳት አጋዩት፤በወፍጮ ፈጩት

በዚህ እለት ደሞ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስለ ቤተ ክርስቲያን ፍቅር ሲል በሰይፍ ተቀልቶ በመንኮራኩር ተፈጭቶ ወደ እቶን እሳት ተወርውሮ ለአእምሮ በሚከብድ መልኩ ብዙ መከራን ተቀብሎ በ 27 አመቱ ሚያዚያ 23 ቀን መከራን ተቀብሎ በሰማዕትነት አርፏል

እግዚአብሔር ሰማዕታትን በደም ቅዱሳንን በተጋድሎ ያፀናል አምላክ እኛንም በሀይማኖት በምግባር እንድንፀና የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን "አሜን"