Get Mystery Box with random crypto!

شـبـاب السـلـــفــــيــــيــن

የቴሌግራም ቻናል አርማ nuredinal_arebi — شـبـاب السـلـــفــــيــــيــن ش
የቴሌግራም ቻናል አርማ nuredinal_arebi — شـبـاب السـلـــفــــيــــيــن
የሰርጥ አድራሻ: @nuredinal_arebi
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.90K
የሰርጥ መግለጫ

#ሰለፍያ_ቀጥተኛ_የሀቅ_መንገድ_ብሎም_አይነኬ_ፅኑ_ተራራ_ነው
ለአስተያዬትና እርማት
@Nuredin_al_arebi_Bot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-23 15:15:44 የኔ ጥያቄ.....!!!?


ብዙ የዘነጋናችው ርዕሶች አሉ እናስታውስ

?????

ግን የሱና ሰወች ለምንድነው ስለ ሶሀቦች ወይም ስለታቢዒዮች ወይም ስለ ኢስላማዊ ታሪኮችን የረሳናቸው!?

በተለይ አንዳንዶቻችን ዘንድማ ኢስላማዊ ታሪኮችን መናገር ከመንሀጅ የሚያስወጣ በሚመስል መልኩ ተረስተዋል ለምን....!?

ሰለፍያ ማለት ኢስላም ኢስላም ማለት ሰለፍያ ማለት አይደለምን...!?

ሁለንተናዊ የሀይማኖታችንን መርሆች በተቻለን አቅም እንዳንቃኛቸው ያደረገን ነገር ምንድን ነው!?

ስለ ታሪካችን
ስለ ፀባያችን
ስለ ሶላታችን
ስለ እውነተኝነታችን

በተለይ ስለ ታሪክ የተደረገ ሙሀዶራ እኔ አላውቅም ለምን...!?

ስለ ነብያቶች ታሪክ
ስለ ሶሀቦች ታሪክ
ስለ ታቢዕዮች ታሪክ
ስለ ታቢዑ ታቢዒን ታሪክ
ስለ ሊቃውንቶቻችን ታሪክ
ስለ ሙጀዲዶች ታሪክ
ስለ ጀግኖቻችን ታራክ
ስለኢስላም ጀግኖች ታሪክ

ስለነዚህና መሰል ጉዳዮች ከመናገር ለምን ፈራን!?ነው ወይስ ታሪክ የመስራት ህልም የለንም!?

አወ ይመስላልኮ ምክንያቱም ታሪኩን የማያውቅ ትውልድ ታሪክ ለመስራት አልታደለም ።

ከተውሒድና ሱናችን ላይ ትኩረታችን እንዳለ ሆኖ ኢስላማዊ ጣፋጭ ታሪኮችን ባንዘነጋ መልካም ነው እላለሁ።

ታሪኮቻችን ላይ ብናተኩርኮ የብዙወቻችን ልዩነቶች መፍትሔ ባገኙ ነበር ግን ከታሪክ እውቀቶች የነፃ ትውልድ የፊትና መዘውር ነውና ያውና...........
ስህተታችን ሰፍቶ
➙ልዩነታችን በዝቶ
➙መጠላለፋችን ጎልቶ....እየታዬ ነው።



ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት ብንሰጥ እላለሁ ይህ ማለት ግን ከተውሒድና ሱናችን እንዘናጋ ማለት አይደለም ሲጀመርኮ ከባለታሪኮቹም የምንረዳው ተውሒድና ሱናን አይደል....!?

እና ብናስብበት ለማለት ያክል ብቻ ነው።


...... ኑር ነኝ የፋሩቅ አባት


https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
2.7K views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 10:47:38 አድስ ደርስ ተጀምሯል።
~
በሸይኽ አቡ ዐማር አወል ቢን አሕመድ አል ኸሚሴ ሲሰጥ የነበረው የዑምደቱል አህካም ደርስ በመጠናቀቁ በቦታው የቡሉጝ አል_መራም ደርስ ተጀምሯል።
የደርስ ስዓት 3:00_3:30 ድረስ

የደርስ ቦታ መርከዝ ቢን ዐብ'ባስ።

ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ለተማሪዎች በጣም ምቹ እንድል ነውና ተጠቀሙበት።
2.3K views07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 09:15:44 قال ابن الجوزي رحمه الله :

‏وإنَّ قلوب الناس لتعرف حال الشخص ، وتُحبه أو تأباه ، وتذمَّه أو تمدحه ، وفق ما يتحقَّق بينه وبين الله ، فإنه يكفيه كل همٍّ ويدفع عنه كل شرٍّ .

وما أصلح عبد ما بينه وبين الخلق دون أن ينظر إلى الحق ، إلا انعكس مقصوده ، وعاد حامده ذامًا .

صيد الخاطر ( ١٠٨ )

https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
2.8K views06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 07:57:15 ﴿ رَبَّنا وَلا تُحَمِّلنا ما لا طاقَةَ لَنا بِهِ وَاعفُ عَنّا وَاغفِر لَنا وَارحَمنا﴾
2.7K views04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 22:46:27 ይድረስ ለራያ አለማጣ ሰለፍዮች!!


«የአለማጣ ጀግኖች»
----------------------------------------
በተውሒድ በሱና የመጠቀ አእምሮ፡
ከቁርዐን ከሀዲስ መረጃን አጣምሮ፡
ነፍሱን የሸጠ ሰው ህልሙን አሳምሮ፡
መቼ ይጨነቃል ለዱንያ ማደሮ፡
ወኔ እየጨመረ ይበልጥ ይበረታል፡
በቢድዐ ጩኸት ሱና እንደት ይረታል!!
ጠንክር አንተ ጀግና ተነስ ወኔህ የታል!!?
----------------------------------------
ተውሒድን አስተምር ተነስ ተንቀሳቀስ፡
በአሏህ ተመካ ተራመድ ቀስ በቀስ፡
አናሳ ነኝ ብለህ ቁጥርህን አትናቀው፡
በብዛት አይደለም ጀግና እሚታወቀው፡
በዱር በገደሉ ህዝብህን አስተምር፡
በጌታህ ተመካ ተንቀሳቀስ የምር፡
------------------------------------------
በሞቀ ሞራል ላይ ቅዝቃዜ አትገሽር፡
እውቀት ላይ አተኩር አታብዛ ሽርሽር፡
ስልጣኔ መስሎህ አድስ ፊትና አትሞሽር፡
የነብያት ጥሪ ይህ መንሐጅ ነው አብሽር፡
ሽርክና ቢዲዐ በሚመራት ሀገር፡
ከወንድሞችህ ጋር ፀንተህ ተነጋገር፡
በስክነት ተወያይ በጥልቀት ተማከር፡
ለፊትና አካላቶች እንዳትሆን አሽከር፡
ተውሒድ ላይ አተኩር ሱና ላይ ተሽከርከር፡
------------------------------------------------
ተውሒድን ማስተማር ይሁን ያንተ አላማህ፡
በኢብራሒም ፈለግ ተውሒድ የተጠማህ፡
ከጠማማወች ጋር እንዳይገኝ ፊርማህ፡
የሽርክን ዲሪቶ የጥመትን ካስማ፡
ከማንም ከምንም ከሁሉም አትስማ፡
-------------------------------------------
ትንፋሽክን ሊዘጉት ቢያስቡም እንደ አስም፡
ለሀቁ ጥሪያችን በየዘመናቱ ቢያወጡለት ስም፡
ሒዝብያ ቢንጫጫም ደዕዋውን ሊያከስም፡
እኛ እያለንማ የነብያት ጥሪ ደዕዋችን አይፈርስም፡
እያለ ሳይሰለች ብቻውን ሲታገል፡
የአለማጣው ነብር ያ!የራያው ግልገል፡
የሽርክን ቁሳቁስ ሰበረው እንደ ገል፡
----------------------------------------
በርታ ጀግናዬ ሆይ......!!
ተናበብ በእምነትህ በሱና ተጣመር፡
አሶብያን ትተህ በደሊል ተመርመር፡
ሽርክና ቢዲያን በጋራ እንዋጋ፡
እናጥፋው ከሀገር ይህን ክፉ አደጋ፡
አንተም እኔን ናፍቀኝ እኔም አንተን ላስብ፡
ወደ ተውሒድ ጥሪ ህዝቡን እንሰብስብ፡
ከዚያም በምንችለው ለሱና እንከስብ፡
--------------------------------------------
ጠላቱ ቢበዛም ሁሉም ቢጠራራ፡
በተውሒዱ ቁሟል ገዝፎ እንደ ተራራ፡
ስር እየሰደደ ጫፉ እያንሰራራ፡
----------------------------------------
የጀግንነት መክሊት አንደበተ-ቆራጥ፡
ላመኑበት ጉዳይ ተሰኪ እንደ ሚዝራጥ፡
የአለማጣ ጀግኖች ሲሰማ ዝናቸው፡
እጅግ መንሀጅ ወዳድ#ሰለፍዮች ናቸው፡
------------------------------------------------
አክሱም ሙስሊሞች ላይ በሚደርሰው በደል፡
በኔና አንተ ድክመት በኛው ስራ እማይደል!?
እንጅማ ብንተጋ በጣምራ ብንቆም፡
አይደፍሩንም ነበር እንኳን ጣት መጠቆም፡
--------------------------------------------------
በርቱ የኔ አንበሶች ፅናት ላይ አሁንም፡
እኛ ኢስላምን ይዘን የበታች አንሆንም፡
ዛሬ ጠላታችን የተጫወተብን፡
አህባሽም በቀድሯ የምትደነፉብን፡
መስማማት ተሰኖን ስንናከስ ሲያዩን፡
ከመካከል ገቡ እጅግ ሊያለያዩን፡
-----------------------------------------
ስለዚህ ጀግናዬ የአለማጣ ወጣት፡
ሽርክና ቢዲዐን አትሸፋፍን ቅንጣት፡
በምላስ ተናገር በፅሁፍም ደስኩር፡
ተሽከርከር በፍጥነት እንደ መንኮራኩር፡
በአለማጣ ወጣት በብዙ ተስፋ አለኝ፡
ዛሬ አልዘረዝርም ለምን እንዳትለኝ!!
-----------------------------------------------
ሳላይ የወደድኩህ በተውሒድህ ጥራት፡
በአቂዳ የፀዳህ ጌታን ከማጋራት፡
አንተ ነህ ሱንዩ የጨለማው መብራት፡
ኢንሻ-አሏህ ደግሞ መጥተን ስናያችሁ፡
በተውሒድ በሱና እጂጉን ደምቃችሁ፡
የሱናውን ወጥመድ ለአህባሽ አጥምዳችሁ፡
በአሏህ እገዛ ድል አስመዝግባችሁ፡
በድምቀት በደስታ ታሳዩናላችሁ!?
------------------------------------------
በመንሀጀ-ሰለፍ ተጓዥ ክንውኖች፡
የተውሒድ ሰባኪ የምድር ድሮኖች፡
በርቱ ተበራቱ የአለማጣ ጀግኖች፡
------------------------------------------
ከደካማው ወንድማችሁ
ኑረዲን አል አረቢ የተጫረች
------------------------------------------
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
3.3K viewsedited  19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 19:58:12 ግን ለምን በዚህ መጠን?
~
ሰው ግን ወላሂ በጣም የሚገርም ሆኗል። ቁም ነገር ላይ የመጨረሻ ዳተኛ ነው። የሌሎችን አጀንዳ ለመቀበል፣ እንቶ ፈንቶ ለማራገብ ግን አንደኛ!
* ወደ ተውሒድ የሚጣሩ፣ ከሺርክና ቢድዐ የሚያስጠነቅቁ ስራዎች ገበያ የላቸውም።
* ሰዎችን ከአክ 'ፍሮተ- ኃይሎች ለማትረፍ ያቅማቸውን ተፍ ተፍ የሚሉ ዱዓት ስራዎች ይሄ ነው የሚባል የሚያሰራጫቸው የለም።
* ስለ ኢስላማዊ አደቦች የሚሰጡ ትምህርቶች ቦታ የሚሰጣቸው የለም።
* ሌላው ቀርቶ የቤተሰብ የአፋልጉኝ ጥሪ እንኳ ሰሚ አጥቷልኮ። አላህን ማሰብ የለ! በሰው ጭንቀት መጨነቅ የለ! ነግ በኔ የለ! ምን አይነት ድንዛዜ ላይ ነው የደረስነው? እንዲያው ልጅ፣ መኪና፣... ጠፍቶባችሁ ተጨንቃችሁ "አፋልጉን" ያላችሁ እንኳ ጭንቀቱን አይታችሁታል። ምናለ እናንተ እንኳ ለየት ብትሉ?!

ከእንዲህ አይነቶቹ አሳሳቢ ጉዳዮች ይልቅ

- የሆኑ ዱዓቶች ላይ ፀያፍ ነገር ሲታይ ወይም ሲሰማ ያለ ምንም ጥንቃቄ ሁሉንም በጅምላ ለማጠልሸት የሚታየው ርብርብ የሚገርም ነው።
- ኦሮሞ ተሰደብ፣ አማራ ተወገዘ፣ ትግሬ ተነካ፣ ... ሲባል እጁንም ምላሱንም እሾህ አድርጎ ሁሉን በጅምላ ሊወጋ የሚዘምተው እልፍ ነው። አስመሳይ የዘር ነጋዴዎች!
- የወንዙ፣ የመንደሩ ወሬ ሲነሳለት ለእስክሳ የሚነሳውም ለጉድ ነው። ሐራም ነገር ሁሉ በዘር በብሄራችን ስም ሲቀርብ ልናወግዘው ቀርቶ ደጋፊ ሆነን እንሰለፋለን።
- በማይረቡ ጉዳዮች የአጀንዳ ፍርፋሪ ሲወረወርለት የሚያራግበውም መዓት ነው።

ብቻ ያሳዝናል!

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
2.2K views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 19:55:43 https://t.me/durusuabihizam?livestream
3.2K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 18:03:17 ይህ የነጮች አባባል ዛሬ ነው የገባኝ!!

"Dont be available be valuable "
3.4K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 22:41:53 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

ወደ መርከዝ አቢ አዩብ የቁርዐን ሂፍዝና መሰረታዊ የሸሪአ እውቀቶች ማዕከል ገብታችሁ ለመማር የተመዘገባቹህ ተማሪዎች በመዘግየታችን አውፍታን እየጠየቅን

በአዳሪ የተመዘገባቹህ መግቢያ ቀን ሀሙስ እንደሆን ለመግለፅ እንወዳለን

በተመላላሽ የተመዘገባቹህ ትምህርት የምንጀምረው ቅዳሜ መሆኑን አውቃችሁ በፕሮግራማችሁ እንድተገኙ

ማሳሰቢያ:

ከነገ (ቅዳሜ) ጀምሮ በስልክ የተመዘገባቹሁም ለመመዝገብ ፍላጎቱ ያላችሁም የሚያስፈልጉ ነገራቶችን በሟሟላት ከነገ ጀምሮ መመዝገብ ትችላላችሁ ።

ኮንቦልቻ በርበሬ ወንዝ አዲሱ ድልድይን ተሻግሮ ደዌይ ከአንሷር መስጅድ ዝቅ ብሎ

0925887118 /0712887118


https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
3.5K views19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 14:10:34 አትጠራጠር

➊ እውነት እና ዘይት ምንጊዜም ከላይ ይሆናሉ፡፡

➋ የእርጥብ ቅል ክብደቱ እስኪደርቅ ድረስ ነው።

https://t.me/nuredinal_arebi
4.3K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ