Get Mystery Box with random crypto!

شـبـاب السـلـــفــــيــــيــن

የቴሌግራም ቻናል አርማ nuredinal_arebi — شـبـاب السـلـــفــــيــــيــن ش
የቴሌግራም ቻናል አርማ nuredinal_arebi — شـبـاب السـلـــفــــيــــيــن
የሰርጥ አድራሻ: @nuredinal_arebi
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.90K
የሰርጥ መግለጫ

#ሰለፍያ_ቀጥተኛ_የሀቅ_መንገድ_ብሎም_አይነኬ_ፅኑ_ተራራ_ነው
ለአስተያዬትና እርማት
@Nuredin_al_arebi_Bot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-23 08:47:19
2.5K views05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 08:47:00 ታላቅ የደዕዋ ፕሮግራም በገጠር ....
--------------------------------------------

በሩቁ የነገርኳችሁ ሁላችሁም እንድትሰማሙ ነው አደራ እየደወላችሁ ህዝባችንን ቀስቅሱልን ለደዕዋው....!!

በኩታበር ወረዳ 018 ቀበሌ አራጢት ላይ የፊታችን ጁሙዐ ሚያዚያ 20 ይካሔዳል።

በመሆኑም በዚህ ቦታ ያላችሁ ሙስሊሞች በተለያዩ መገናኛ ብዙሀኖችም ጭምር እየተሰማማችሁ ሚያዚያ 20 ጁሙዐ አራጢት ላይ አዲሱ የሱና ወጣቶች መስጂድ እንገናኝ አደራ እንላለን።

በዚህ ፕሮግራም ላይ የተለያዩ የሱፍያ ጦሪቃ ተከታዮች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ታዳሚወቹ ለዚያራ የሚሔዱት የሱና ጀመዐወች

➊የጥቅሳ ሱና ወዳድ ወጣት ጀመዓ
❷የአርሰስ-አንባ ሱና ወዳድ ወጣት ጀመዓ
❸የዳሻ የሱና ወንድሞቻችን በፕሮግራሙ ይገኛሉ ብለን እናስባለን።


ፕሮግራሙ ለየት ባለ መልኩ ስለሚካሔድ ሁላችንም በቦታው በመገኘት የደዕዋው ተቋዳሽ እንሁን ባረከሏሁ ፊኩም።

ፕሮግራሙ የሚጀመረው ከጧቱ ❸:00 ላይ በመሆኑ ሁላችንም ቀድመን በመገኘት ለድናችን ያለንን ክብር እንግለፅ።

በስደት ያላችሁ የነዚህ አካባቢ ተወላጅ እህት ወንድሞች ለቤተሰቦቻችሁ ንገሩልን በማለት በአሏህ ስም እንጠይቃለን።

አዘጋጆቹ እና አስተናጋጆቹ ደግሞ...

➊ የአራጢት ወጣቶች
❷የአርሰስ አንምባ ወጣቶች
❸የችፍርጎ ወጣቶች
❹ከጥቅሳ ወጣቶች ጋር በመመካከር ነው።

ተውሒድን ለገጠሩ ህዝባችን እናድርስ ትግላችንን በድል ለማጠናቀቅ በተውሒድ እንቅስቃሴ ላይ ማተኮር ምርጫ ሳይሆን ግደታ ነው።

ከዳውዶ እስከ ሰጎዳ ድረስ ተጋብዛችኋል።

በኑረዲን አል አረቢ(➊❹❹❹)
ሽርክ እስካልጠፋ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል።

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
2.6K viewsedited  05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 08:35:56
ዋጋህን በሰወች ፊት አትተምነው በሀቅ ላይ ፅና!!

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
2.5K viewsedited  05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 18:12:54
ጭንብልህን አውልቅ አታስመስል...!!

በሌለህ ነገር ከመወደድ ይልቅ ባለህ ነገር መጠላት በላጭ ነው።

አታስመስል...!!

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
1.2K viewsedited  15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 17:20:27
ዝምድናን አትቁረጡ...!!

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
1.4K viewsedited  14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 17:01:40
ፂማችሁን አሳድጉ ወንዶች...

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
1.5K viewsedited  14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 10:21:07 ➤ ❝ግጥም

በከላላ መስጂደ-ሰላም ላይ የቀረበ!!

❝ቦረና” ይለያል❞,,,,,,።

ሐጃዊራን ያንጫጫው ግጥም


በኑረዲን አል አረቢ

t.me/nuredinal_arebi/16051
t.me/nuredinal_arebi/16051
2.0K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 08:51:39 ይለቀማል እንጂ በመላ በዘዴ፡
ለእንክርዳድ ተብሎ አይደፋም ስንዴ..
2.0K views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 07:33:04 የሸዋል ስድስት ቀናትን ፆም የሚመለከቱ ነጥቦች
~
1. ከሸዋል ስድስት ቀናትን መፆም ፋይዳው ምንድነው?
መልስ፦ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ كَانَ كَصِيَامِ الدَّهْرِ
“ረመዷንን ፁሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ያስከተለው አመት እንደመፆም ነው።” [ሙስሊም፡ 1164]
ስለዚህ ስድስት ቀናትን በሸዋል ወር ውስጥ መፆም አጅሩ ከረመዷን ወር ፆም ጋር የሚቆራኝ ነው ማለት ነው።

2. ከሸዋል ስድስት ቀናትን መፆም የሚጠቁመው ሐዲሥ ሰነዱ አስተማማኝ ነውን?
መልስ፦ ሐዲሡ ሚዛን በሚደፋ አቋም ለማስረጃነት በቂ ነው። ዝርዝር የፈለገ ይህንን ሊንክ ተከትሎ ይመልከት፦ https://tinyurl.com/mucfx3ny

3. ከሸዋል ውጭ ባሉ ወራት ውስጥ ስድስት ቀናት ቢፆም የሸዋልን ፆም ይተካልን?
መልስ፦ ማስረጃ የመጣው ሸዋልን በተመለከተ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ለማለት የሚያስችል መረጃ የለም።

4. አከታትሎ ነው ወይስ አፈራርቆ ነው የሚፆሙት?
መልስ፦ በሸዋል ወር ውስጥ እስከሆነ ድረስ አከታትሎም ይሁን አፈራርቆ፣ ቀጥታ ከዒድ በኋላም ይሁን አዘግይቶ በፈለገው መልኩ መፆም ይችላል።

5. ፆሙን ከሸዋል አንድ መጀመር ይቻላል?
መልስ፦ ሸዋል አንድ ዒድ ነው። በዒድ ቀን መፆም ደግሞ አይፈቀድም።

6. ቀዷእ ያለበት ሰው ሸዋልን መፆም ይችላል?
መልስ፦ ከፊል ዓሊሞች አይቻልም ይላሉ። የአብዛኞቹ ዓሊሞች አቋም ግን ይቻላል የሚል ነው። ጠንካራውም አቋም ይሄ ነው። ይህንን ከሚጠቁሙ መረጃዎች ውስጥ፦

[ማስረጃ አንድ]፦

እናታችን ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብላለች፦
كانَ يَكونُ عَلَيَّ الصَّوْمُ مِن رَمَضَانَ ، فَما أسْتَطِيعُ أنْ أقْضِيَ إلَّا في شَعْبَانَ
ከረመዷን (ያልፆምኩት) ፆም ይኖርብኝ ነበር። በሸዕባን እንጂ ቀዷኡን ማውጣት አልችልም ነበር።” [ቡኻሪ፡ 1149] [ሙስሊም፡ 1849]
ልብ በሉ! ሸዕባን በኢስላማዊው አቆጣጠር ከረመዷን በፊት ያለው ወር ነው። የረመዷንን ቀዷእ ሳታወጣ ቀጣዩ ረመዷን ሲቃረብ ነበር የምትፆመው። በዚህ መሃል ላይ ትልልቅ አጅር ያላቸው የዐረፋ ፆም፣ የዐሹራእ ፆም፣... አሉ። ዓኢሻ ይህን ሁሉ አትፆምም ነበር፣ ከአመት እስካመት ሱና ፆም አትፆምም ነበር ብሎ ማሰብ ይከብዳል።
“አይ ለሳቸው ስትል ነበርኮ የረመዷንን ቀዷእ የምታዘገየው” ከተባለ “አዎ። ነብያችን ﷺ ሸዕባንን አብዛኛውን ይፆሙት ስለነበር ሸዕባን ላይ ቀዷእ ለማውጣት ሰፊ ጊዜ ይኖራታል። ግና እሳቸውኮ
* ዐረፋና ዐሹራእ ይፆሙ ነበር።
* በሌሎችም ወራት “አያፈጥሩም እስከምንል ድረስ ይፆሙ ነበር” ብላለች ዓኢሻ። [ቡኻሪ፡ 1969]
* ከየወሩ ሶስት ቀን ይፆሙ ነበር። [አቡ ዳውድ፡ 507]
* በየ ሳምንቱም ሰኞና ሐሙስም ይፆሙ ነበር። [ቲርሚዚይ፡ 745]
* በተጨማሪም “ከረመዷን ቀጥሎ በላጩ ፆም የሙሐረም ወር ፆም ነው”ብለዋል። [1163]
* በየወሩ “አያመል ቢድ” ማለትም 13ኛ፣ 14ኛ እና 15ኛ ቀናትን መፆምንም አዘዋል። [ነሳኢ፡ 7/222] [ቲርሚዚይ፡ 761]
ይህ ሁሉ ከመሆኑ ጋር የረመዷንን ቀዷእ እስከ ሸዕባን ድረስ የምታዘገይበት አንዱ ምክንያት ቀጣይ ረመዷን እስካልገባ ድረስ ማዘግየት ስለሚቻል ነው። እንጂ በዚህ ሁሉ መሃልም መፆም ትችል ነበር።

[ማስረጃ ሁለት]፦

የረመዷንን ቀዷእ ወሩ እንዳለቀ ወዲያውኑ አከታትሎ መፆም ግዴታ አይደለም። ይሄ የብዙሃን ዑለማእ አቋም ነው። ቀጣይ ረመዷን እስካልገባ ድረስ ማዘግየት ይቻላል። ወዲያውና አከታትሎ መፈፀም ግዴታ ካልሆነ ደግሞ መሃል ግዴታ ያልሆኑ ፆሞችን መፈፀም የተከለከለ አይሆንም። ይህ እንግዲህ ቀዷእ ላለበት ሰው በላጩ አፈፃፀም ቀድሞ ቀዷኡን መፆም፣ ከዚያም የሸዋልን ስድስት ማስከተል ከመሆኑ ጋር ነው።
ነገር ግን በወር አበባ ወይም በሌላ ምክንያት በርከት ያለ ቀዷእ ያለ ከሆነ ሸዋልን ለመፆም በቂ ጊዜ ላይኖር ይችላል። ወይም የፆሙ ጊዜ በመደራረቡ ሊከብድ ይችላል። በዚህና መሰል ሁኔታ ላይ ላለ አካል ሸዋልን የመፆም አጅር እንዳያልፈው ቢያስቀድምና ቀዷኡን አረፍ ብሎ ቆይቶ ቢፆም የሚከለክለው ግልፅ ማስረጃ የለም።

ብዥታዎች፦
-
የግዴታ ፆምን ቀዷእ ሳይፆሙ ሱና ፆም መፆም አይቻልም የሚሉ ዓሊሞች እንዳሉ ገልጫለሁ። ከሚጠቅሷቸው ማስረጃዎች ውስጥ፦

[አንዱ]

መግቢያዬ ላይ የጠቀስኩትን “ረመዷንን ፁሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ያስከተለው አመት እንደመፆም ነው” የሚለውን ሐዲሥ ነው። ማስረጃ የሚያደርጉበት አግባብ የተጠቀሰው አጅር ሙሉ ረመዷንን ፁሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ያስከተለን ነው የሚል ነው።
ይሄ ግን አብዛኛው ሙስሊም ረመዷንን ሙሉውን ስለሚፆም በዚህ መልኩ ተገለፀ እንጂ በተጨባጭ ሸሪዐዊ ምክንያት ሙሉውን ያልፆመ ሰው ከተጠቀሰው አጅር ውጭ ይሆናል ማለት አይደለም። ለምሳሌ ያክል ነብያችን ﷺ “ረመዷንን አምኖና አጅሩን አስቦ የፆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል” ብለዋል። ይህ ማለት ግን በወር አበባ ምክንያት ሙሉውን ያልፆመች ሴት ይህንን አጅር አታገኝም ማለት አይደለም።

[ሁለተኛ] ማስረጃ የሚያደርጉት ተከታዩን ሐዲሥ ነው፦
من أدركَ رمضانَ وعليهِ من رمضانَ شيءٌ لم يقضهِ، لم يتقبَّل منهُ ومن صامَ تطوُّعًا وعليهِ من رمضانَ شيءٌ لم يقضهِ، فإنَّهُ لا يتقبَّلُ منهُ حتَّى يصومَهُ
“በሱ ላይ ቀዷእ ያላወጣው የረመዷን ፆም እያለበት ረመዷን የደረሰበት ሰው አላህ አይቀበለውም። በሱ ላይ ቀዷእ ያላወጣው የረመዷን ፆም እያለበት ግዴታ ያልሆነ ፆም የፆመ ሰው ቀዷኡን እስከሚፆም ድረስ ተቀባይነት አይቀበለውም።” [ሙስነድ አሕመድ፡ 8606]

መልስ፦ ዶዒፍ ነው። [አልዒለል፣ ኢብኑ አቢ ሓቲም፡ 768]

[ሶስተኛ] የሚጠቀሰው እንዲህ የሚል ነው፦
አንድ ሰው፡ “የረመዷን ቀዷእ አለብኝ። ከመሆኑም ጋር አስሩን ትርፍ ፆም ልፆም ፈልጌ ነበር” ሲል አቡ ሁረይራህ ረዲየላሁ ዐንሁ፡ “አይሆንም። ይልቁንም በአላህ ሐቅ ጀምር፣ እሱን ቀዷእ አውጣ። ከዚያ በኋላ የፈለግከውን ትርፍ ፆም ፁም” አሉ። [ሙሶነፍ ዐብዲረዛቅ፡ 7715]

መልስ፦ ግንዛቤው ላይ የተለያዩ ሃሳቦች ከመሰንዘራቸው ጋር ቀጥታውን ስንወስድ ከዓኢሻ ሐዲሥ ጋር የሚቃረን ነው። የዓኢሻ ሐዲሥ ደግሞ የነብዩ ﷺ ኢቅራር (ማፅደቅ) ያለበት ስለሆነ ቅድሚያ ይሰጠዋል።

[ማጠቃለያ]:-

ስለዚህ የረመዳን ፆም ቀዷ ያለበት ሰው
① ለቀዷው ሰፊ ጊዜ ስላለና
② የሸዋል ጊዜ አጭር ስለሆነ ሸዋልን አስቀድሞ መፆም ይችላል።

* ይህንን ነጥብ ዘለግ አድርጌ መዳሰስ የፈልግኩት ሸዋል ቢያልፍም እንኳ ቀዳኡን ሳይፆሙ የሸዋልን ስድስት ቀናት መፆም አይቻልም የሚሉ ዑለማዎችን ፈትዋ ነጥለው ትኩረት የሚሰጡ ስላሉ ነው። ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት መፆም ይቻላል የሚለው አቋም የብዙሃን ዑለማእ ምርጫ ነው። በሸይኽ ሙቅቢል ፈትዋ ፅሁፌን ላሳርግ:-
2.2K views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 07:33:04
1.9K views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ