2023-04-20 18:29:36
ሰበር!
~
ሰዑዲያ ዒድ ነገ ጁመዐ እንደሆነ አውጃለች። [ምንጭ:- አሰዑዲያ የዜና ወኪል https://twitter.com/SaudiNews50/status/1649070246681104386?t=gjVElwU_nLMs-1Vy-cEDSg&s=19
]
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሐል አዕማል።
=
{ وَٱلۡقَمَرَ قَدَّرۡنَـٰهُ مَنَازِلَ حَتَّىٰ عَادَ كَٱلۡعُرۡجُونِ ٱلۡقَدِیمِ }
"ጨረቃንም የመስፈሪያዎች ባለቤት ሲሆን እንደ ዘንባባ አሮጌ ቀንዘል እስኪሆን ድረስ (መሄዱን) ለካነው።" [ያሲን፡ 39]
የጨረቃ መስፈሪያዎች የተባሉት በየ ወሩ ለ 28 ቀን የሚያልፍበት ቆይታ ነው። ቀጭን ሆና ጀምራ እያደገች ትሄድና ሙሉ ጨረቃ ትሆናለች። እንደገና እያነሰች ሄዳ ልክ እንደ ደጋን የጎበጠ የተምር ቀንዘል ጎብጣ ትቀጥናለች። በመጨረሻ ትጠፋለች።
ወሩ 30 ቀን ሲሆን ጨረቃ ለ 2 ሌሊቶች ትደበቃለች (አትታይም)። ወሩ 29 ቀን ሲሆን ደግሞ ለ 1 ሌሊት ትደበቃለች።
ኢስላማዊው የቀን መቁጠሪያ የጨረቃን እንቅስቃሴ መሰረት ያደረገ ነው። ስለሆነም ዘካ የሚወጣው፣ የልጆች ለአቅመ መጠን መድረስ የሚወሰነው በጨረቃ አቆጣጠር መሰረት ተሰልቶ ነው። በጨረቃው አቆጣጠር አንድ አመት 354 አካባቢ ቀናት ሲኖሩት የፀሐዩ አቆጣጠር ደግሞ 365 አካባቢ ቀናት አሉት። ስለዚህ የ 11 ቀን ልዩነት አለ ማለት ነው።
ማስታወሻ፦
አንዳንዶች የጨረቃን መውጣት ስንከታተል "ጨረቃን ታመልካላችሁ" እያሉ ይከስሳሉ። ለነዚህ አላዋቂዎች የምንላቸው እናንተ የፀሐይን እንቅስቃሴ መሰረት ያደረገውን መቁጠሪያ የምትጠቀሙት ፀሐይን ስለምታመልኩ ነው እንዴ? ለምን በራሳችሁ ላይ ትተኩሳላችሁ?
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
3.0K views15:29