Get Mystery Box with random crypto!

43 All University

የቴሌግራም ቻናል አርማ merejamnch — 43  All University 4
የቴሌግራም ቻናል አርማ merejamnch — 43  All University
የሰርጥ አድራሻ: @merejamnch
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.11K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በአዲስ የተከፈተ ከ43ቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት እና ሌሎች የዩኒቨርስቲ ሀላፊዎች ጋር በመነጋገር ፈጣን የሆነ መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ነው።
እንዲሁም በተጨማሪ መረጃወችን በመሰብሰብ በሁሉም የ ት/ት ደረጃ ተማሪን የሚመለከት መረጃ በፍጥነት እናደርሳለን።
ለCross ፦
👇👇👇
👍 @Gashushu
👍 @Gashtiman25
❤Join❤
👇👇👇
@merejamnch

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-29 14:52:18
የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ምንይችል ግታውን (ዶ/ር) የኢንስቲትዩቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አድርጎ ሾሟል።

ተሿሚው ለቀጣይ ሦሥት ዓመታት ኢንስቲትዩቱን እንደሚመሩ ተገልጿል።

ምንይችል ግታው (ዶ/ር) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዲን በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
1.0K views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:53:30
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፍ የሕግ መውጫ ፈተና ከወሰዱ 58 ተማሪዎቹ 52ቱ የመውጫ ፈተናውን ማለፋቸውን አሳውቋል።

10 ሴት እና 42 ወንድ በድምሩ 52 ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን በከፍተኛ ውጤት ማለፋቸውን የዩኒቨርሲቲው የሕግ ትምህርት ቤት ዲን ምንዳ ግርማ ገልጸዋል፡፡

ውጤቱ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ደረጃ ተማሪዎቻቸውን ካሳለፉ የትምህርት ተቋማት ውስጥ አንዱ መሆኑን ዲኑ ጠቁመዋል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
948 views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:58:57
የጤና ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተናን ዛሬ መሰጠት ይጀምራል።

በዚህም የፋርማሲ፣ አንስቴዥያ እና ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ዛሬ የምዘና ፈተናውን ይወስዳሉ።

ለአምስት ቀናት በሚቆየው የብቃት ምዘና የነርሲንግ ባለሙያዎች ነሐሴ 24/2014 ዓ.ም፣ የህክምና እና ጤና መኮንን ባለሙያዎች ነሐሴ 25/2014 ዓ.ም፣ የሚድዋይፈሪ፣ ዴንታል ሜዲስን እና ኢንቫይሮመንታል ሄልዝ ባለሙያዎች ነሐሴ 26/2014 ዓ.ም እንዲሁም የሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ፣ ፔዲያትሪክ ነርሲንግ እና ሳይካትሪ ነርሲንግ ባለሙያዎች ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም የምዘና ፈተናው ይወስዳሉ።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
993 views05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:57:43
#AmharaEducationBureau

በአማራ ክልል የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23/2014 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 04/2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት እንደሚካሄድ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ወላጆች እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናትን ለትምህርት እንዲያስመዝግቡ ቢሮው አሳስቧል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
953 views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 13:49:49
#BuleHoraUniversity

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ፕሬዝዳንት አወዳድሮ ለመቅጠር የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል።

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ ተቋሙን ለሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የሚመራ ኃላፊ ለማወዳደር ፍላጎቱን አሳውቋል፡፡

አመልካቾች የትምህርት ደረጃቸው ሁለተኛ ዲግሪ ከረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ጋር እና ከዚያ በላይ መሆን እንዳለበት ተገልጿል።

አመልካቾች በቀጣይ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፦

• Curriculum Vitae (CV)

• የትምህርት ደረጃን የሚገልጽ ሰርተፊኬት

• የአካዳሚክ ማዕረግ የሚገልጽ ደብዳቤ

• በዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ወይም በምርምር ተቋም በተመራማሪነት ያገለገሉበትን ጊዜ የሚገልጽ ደብዳቤ

• በዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉበትን የሚገልጽ ደብዳቤ

• በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትነት ቢመደቡ የዘርፉን ሥራ ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ከአስር ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂክ ዕቅድ

አመልካቾች ከነሐሴ 23/2014 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 04/2014 ዓ.ም በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ ወይም
በኢ-ሜይል አድራሻ bhu.info@bhu.edu.et ወይም dubacana19@gmail.com እና በዩኒቨርሲቲው ፖስታ ሳጥን ቁጥር 144 መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለተጨማሪ መረጃ፦

www.bhu.edu.et
0914315520
0941081619

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ባለፈው ሰኔ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት የነበሩትን ጫላ አዋታ (ዶ/ር) እና ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶች ከኃላፊነታቸው በማንሳት በምትካቸው አዲስ አመራሮች መመደቡ ይታወሳል።


@merejamnch
@merejamnch
1.2K views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 11:24:29
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጎባ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በጤና የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 356 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተማሪዎቹ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

በፋርማሲ፣ በነርሲንግ፣ በሚድዋይፈሪ፣ በህክምና ዶክትሬት በመጀመሪያ እና በሁለኛ ዲግሪ ከተመረቁት መካከል 36 ተማሪዎች ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የጤና ሳይንስ ኮሌጁ እስካሁን በድምሩ 2 ሺህ 350 ተማሪዎችን ማስመረቅ መቻሉ ተመላክቷል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
1.0K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 11:14:21
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንድቀጥል ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ
****
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከሃገር አቀፍ ፈተናዎች አገልግሎት የሥራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ገልፀው፤ ውጤታማነቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

በመድረኩ ላይ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና አሰጣጥ ዝግጅት፣ የዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና አሰጣጥ፣ የትምህርት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ተቋማዊ ሪፎርም፣ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ (autonomous) ለማድረግ ስለተያዘው ዕቅድ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዋናነት ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድን ከመገንባት አኳያ በትምህርት ሚኒስቴር የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራና ተስፋ ሰጪ ጅምሮች ስለመኖራቸውም ተብራርቷል።
ቋሚ ኮሚቴው የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናን በሚመለከት ከወላጆች የሚነሱ ስጋቶችን እና ጥያቄዎችን እንዲሁም፤ ከየክልሉ ትምህርት ቢሮዎች ያሰባሰባቸውን መረጃዎች መሰረት ላነሳቸው ጥያቄዎች ፤ በስራ ኃላፊዎቹ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡

ምንጭ :- ኢ.አ.ድ/MoE

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
1.0K views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:16:51
የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በ2015 ዓ.ም ይጀምራል።

የሙከራ ትግበራው በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚጀመር የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ሥርዓተ ትምህርቱ ሀገር በቀል እውቀት፣ ግብረ ገብ እንዲሁም ሳይንስና ቴክኖሎጂን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

በሙከራ ትግበራው የሚገኙ አስተያየቶች ተካተው ሥርዓተ ትምህርቱ በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ ይሸጋገራል ተብሏል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
1.2K views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 02:43:20
#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጥናቸውን ከ6 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ነገ ያስመርቃል።

ከተመራቂዎቹ ውስጥ 69 በሦሥተኛ ዲግሪ፣ 1,597 በሁለተኛ ዲግሪ፣ 98 በስፔሻሊቲ፣ 3,910 በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

መርከበኞች እና የከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም (HDP) ሰልጣኝ መምህራን ነገ ከሚመረቁት ውስጥ እንደሚገኙ ከዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር እና አልሙናይ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 40 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።

(የሚመረቁ ተማሪዎች ሙሉ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
1.3K views23:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:42:21 በ2014 በጀት ዓመት የተለያዩ የህግ ጥሰት ፈፅመዋል ከተባሉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል 222 ያህሉ ተማሪዎቻቸውንም እንዲበትኑ ውሳኔ ተላለፎባቸዋል ተባለ፡፡

በትምህርት ተቋማቱ ይማሩ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች እጣ ፋንታ ምን ይሆን?

ሸገር ሬድዮ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣንን አነጋግሯል የድምፅ ፋይሉን ያዳምጡ

#የትምህርትና_ስልጠና_ባለስልጣን

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
1.3K views11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ