Get Mystery Box with random crypto!

#BuleHoraUniversity ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ፕሬዝዳንት አወዳድሮ ለመቅጠር የቅጥር | 43 All University

#BuleHoraUniversity

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ፕሬዝዳንት አወዳድሮ ለመቅጠር የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል።

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ ተቋሙን ለሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የሚመራ ኃላፊ ለማወዳደር ፍላጎቱን አሳውቋል፡፡

አመልካቾች የትምህርት ደረጃቸው ሁለተኛ ዲግሪ ከረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ጋር እና ከዚያ በላይ መሆን እንዳለበት ተገልጿል።

አመልካቾች በቀጣይ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፦

• Curriculum Vitae (CV)

• የትምህርት ደረጃን የሚገልጽ ሰርተፊኬት

• የአካዳሚክ ማዕረግ የሚገልጽ ደብዳቤ

• በዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ወይም በምርምር ተቋም በተመራማሪነት ያገለገሉበትን ጊዜ የሚገልጽ ደብዳቤ

• በዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉበትን የሚገልጽ ደብዳቤ

• በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትነት ቢመደቡ የዘርፉን ሥራ ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ከአስር ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂክ ዕቅድ

አመልካቾች ከነሐሴ 23/2014 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 04/2014 ዓ.ም በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ ወይም
በኢ-ሜይል አድራሻ bhu.info@bhu.edu.et ወይም dubacana19@gmail.com እና በዩኒቨርሲቲው ፖስታ ሳጥን ቁጥር 144 መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለተጨማሪ መረጃ፦

www.bhu.edu.et
0914315520
0941081619

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ባለፈው ሰኔ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት የነበሩትን ጫላ አዋታ (ዶ/ር) እና ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶች ከኃላፊነታቸው በማንሳት በምትካቸው አዲስ አመራሮች መመደቡ ይታወሳል።


@merejamnch
@merejamnch