Get Mystery Box with random crypto!

43 All University

የቴሌግራም ቻናል አርማ merejamnch — 43  All University 4
የቴሌግራም ቻናል አርማ merejamnch — 43  All University
የሰርጥ አድራሻ: @merejamnch
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.11K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በአዲስ የተከፈተ ከ43ቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት እና ሌሎች የዩኒቨርስቲ ሀላፊዎች ጋር በመነጋገር ፈጣን የሆነ መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ነው።
እንዲሁም በተጨማሪ መረጃወችን በመሰብሰብ በሁሉም የ ት/ት ደረጃ ተማሪን የሚመለከት መረጃ በፍጥነት እናደርሳለን።
ለCross ፦
👇👇👇
👍 @Gashushu
👍 @Gashtiman25
❤Join❤
👇👇👇
@merejamnch

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 09:14:52
#Addis_Ababa_Education_Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ ያዘጋጀው የሬዲዮ ትምህርት የስክሪፕት ቀረጻን እያከናወነ ነው።

ቀረጻው በቅርቡ ተጠናቆ ለመማር ማስተማር ሥራ ዝግጁ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች 900 ስክሪፕቶች ተዘጋጅተው በቀረጻ ላይ እንደሚገኙ የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሬክተር በለጠ ንጉሴ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ ለ2015 የትምህርት ዘመን አንደኛ መንፈቅ ዓመት የሚያገለግሉ 450 የሚሆኑ ስክሪፕቶች ቀረጻ ላይ እንደሚገኙ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

75 የሬዲዮ ትምህርት ቀረጻ ፕሮግራም አዘጋጆች፣ ቴክኒሺያኖች እና ተማሪዎች በቀረጻው እየተሳተፉ እንደሚገኙ ቢሮው ገልጿል።

አዲሱ የአንደኛ ደረጃ ስርዓተ ትምህርት (ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል) በ2014 ዓ.ም የሙከራ ትግበራ ተካሂዶ በ2015 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይታወቃል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
625 views06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:14:40
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በሳምንቱ መጨረሻ መርሃ ግብሮች በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለመማር ላመለከቱ የመግቢያ ፈተና ቅዳሜ ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ፈተናው በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ፣ በጎዴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ በደጋህቡር ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ እንዲሁም በፊቅ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ተፈታኞች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

ለፈተናው የተመረጡ አመልካቾችን በተከታዩ ሊንክ መመልከት ትችላላችሁ፦

https://www.facebook.com/614590095253065/posts/pfbid02vdXcet51zSByjSyGbknWGK1WPZUDPdJexQEopi1VyFUc1eaWGPmuWoZH2Bx8z2qhl/?extid=a&mibextid=e8qoej

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
517 views06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 00:40:42
በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ በኢንተርኔት ላይ ማየት እንደሚችሉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በክልሉ ለፈተና ከተመዘገቡ 451 ሺህ 21 ተማሪዎች
ውስጥ 98 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት ፈተናውን መውሰዳቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ግርማ ባይሳ ተናግረዋል።

በዚህም የማለፊያ ውጤት ለወንዶች 50 በመቶ፤ ለሴቶች 47 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ አርብቶ አደሩ አካባቢዎች ማለፊያ ውጤት ለወንዶች 47 በመቶ፤ ለሴቶች 44 በመቶ ሲሆን ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ደግሞ ለወንዶች 44 በመቶ፤ ለሴቶች 41 በመቶ መሆኑ ተገልጿል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በተከታዩ ሊንክ መመልከት ይችላሉ፦

https://oromia.ministry.et/#/home

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
666 views21:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 18:19:28
#WachemoUniversity

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስቴር ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡

የ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁለት ዙር ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ የሚሰጠውን ፈተና አስመልክቶ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) ከሁሉም ምክትል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ከኮሌጅ እና የትምህርት ቤት ዲኖች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ፣ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ እና በንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮምፕሬንስቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ20 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ሁሉም የኮሌጅ እና የትምህርት ቤት ዲኖች የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የፈተና አስፈፃሚዎች ምልመላ መነሻ መስፈርት መሰረት የፈታኝ መምህራን ምልመላ እንዲያደርጉ ፕሬዝዳንቱ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ሚኒስቴሩ ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17/2015 ዓ.ም በሁሉም የዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምንም አይነት መደበኛ ተማሪ እንዳይገኝ ማለቱ ይታወሳል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
853 views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 16:05:23
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ካምፓስ ከአካባቢው ለተውጣጡ ተማሪዎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስልጠና እየሰጠ ነው።

በቴፒ ከተማ ከሚገኙ አምስት የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የሳይንስ ትምህርቶች የፈጠራ አቅም ያላቸው ተማሪዎች በስልጠናው እየተሳተፉ ነው።

ስልጠናው ተማሪዎቹ ያላቸውን የፈጠራ አቅም የሚያሳድግና በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን እውቀት በተግባር የሚሞክሩበት መሆኑ ተገልጿል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
801 views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 09:32:48
#AmharaEducationBureau

በ2015 የትምህርት ዘመን በአማራ ክልልበሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተማሪ መመዝገቢያ ክፍያ ጭማሪ ማድረግ #እንደማይፈቀድ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

"የተወሰኑ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የመመዝገቢያ ክፍያ ጭማሪ ማድረጋቸውን አረጋግጠናል" ያሉት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ማተብ ታፈረ (ዶ/ር)፤ ተግባሩ ህገ-ወጥ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመሆኑም ማንኛውም በክልሉ የሚገኝ የመንግስት ትምህርት ቤት ከባለፈው ዓመት የተለየ ምንም አይነት የመመዝገቢያ ክፍያ ጭማሪ ማድረግ ያልተፈቀደለት መሆኑን ኃላፊው አሳስበዋል።

በአማራ ክልል የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23/2014 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 04/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን መገለጹ ይታወሳል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
950 views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 09:17:41
#DebreMarkosUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት የፈጠራ ሥራዎች ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የግልጋሎት ሞዴል ሰርተፊኬት ተሰጥቶታል።

ከእንሰት የሚዘጋጅ ጠላ እና አረቄ እንዲሁም የአዘገጃጀት ዘዴዎቹ ባለስልጣኑ ለዩኒቨርሲቲው የእውቅና ሰርተፊኬት የሰጠባቸው ፈጠራዎች ናቸው።

ፈጠራዎቹ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ በሆኑት ባዎቀ ጥሩነህ መገኘታቸውን
ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በዩኒቨርሲቲው ሥም የተመዘገቡትን ፈጠራዎች እውን ለማድረግ ተቋሙ ሙሉ የምርምር ወጪዎችን መሸፈኑ ተገልጿል።

ፈጠራው ሙሉ ለሙሉ መተግበር ሲጀምር በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል ያልተለመደውን የእንሰት ምርት እና ጥቅም በሰፊው እንደሚያሳድገው ተመላክቷል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
909 views06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:21:27
#University_Of_Gondar

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም ይከናወናል፡፡

ትምህርታቸውን በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከታትለው ያጠናቀቁ ከ5 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን በዕለቱ እንደሚያስመርቅ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ተመራቂዎቹ በቅድመ ምረቃ እና በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
683 views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:05:35
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ ግብር ከተቋሙ በከፍተኛ ውጤት ለተመረቁ 18 ተማሪዎች በ2015 የትምህርት ዘመን ነጻ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል አወዳደሮ መስጠት እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡

የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ተማሪዎች በ2014 ዓ.ም በመደበኛ መርሃ ግብር የተመረቁና ለወንድ 3.5 እና ከዚያ በላይ፤ ለሴት 3.25 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

በመሆኑም የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን የምትፈልጉ መስከረም እና ሰኔ/2014 ዓ.ም ከዩኒቨርሲቲው የተመረቃችሁ እስከ አርብ ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎች፡-

• ሙሉ የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ሁለት ኮፒ
• ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ
• የድጋፍ ደብዳቤ
• በተማሪ አደረጃጀቶች አገልግሎት የተሰጠበት የምስክር ወረቀት

የማመልከቻ ቦታ፡- በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

ለፈተና ያለፉ አመልካቾች በውስጥ ማስታወቂያ ከጳጌሜን 01 እስከ 03/2014 ዓ.ም ይገለጻል።

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- መስከረም 05/2015 ዓ.ም።

ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡- በዩኒቨርሲቲው አምስት ካምፓሶች/ኮሌጆች

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
782 views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:33:24
#WoldiaUniversity

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በፀጥታ ስጋት ምክንያት ተቋሙን ለቀው የወጡ ተማሪዎችን በተመለከት ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም የመደበኛ መርሃ ግብር ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ በቀጣይ ዓመት ጥሪ በሚደረግበት ወቅት እንደሆነ ተገልጿል።

የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች በሙሉ የተጀመረውን ትምህርት እና ፈተና ለማጠናቀቅ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ መስከረም 03/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
1.1K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ