Get Mystery Box with random crypto!

43 All University

የቴሌግራም ቻናል አርማ merejamnch — 43  All University 4
የቴሌግራም ቻናል አርማ merejamnch — 43  All University
የሰርጥ አድራሻ: @merejamnch
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.11K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በአዲስ የተከፈተ ከ43ቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት እና ሌሎች የዩኒቨርስቲ ሀላፊዎች ጋር በመነጋገር ፈጣን የሆነ መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ነው።
እንዲሁም በተጨማሪ መረጃወችን በመሰብሰብ በሁሉም የ ት/ት ደረጃ ተማሪን የሚመለከት መረጃ በፍጥነት እናደርሳለን።
ለCross ፦
👇👇👇
👍 @Gashushu
👍 @Gashtiman25
❤Join❤
👇👇👇
@merejamnch

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-26 14:42:16
#JinkaUniversity

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጥናቸው ተማሪዎችን ነገ ያስመርቃል።

ዩኒቨርሲቲው በሳምንቱ መጨረሻ መርሃ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ያስተማራቸውን 202 ተማሪዎች ነገ ያስመርቃል። ከተመራቂዎቹ 58ቱ ሴት ተማሪዎች ናቸው።

በተመሳሳይ በከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም (HDP) የሰለጠኑ 69 መምህራን ነገ እንደሚመረቁ የዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ ሀይረዲን መሀመድ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25
1.1K views11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:41:41
የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በቀጣይ አመት እንደሚጀምር ተገለፀ።
-------//----------
የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት የሙከራ ትግበራ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በ2015 ዓ.ም ይጀምራል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ የሙከራ ትግበራ ከሚካሄድባቸው ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ መምህራን ስርዓተ ትምህርቱን የማስተዋወቅ የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

አዲሱ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት በርካታ ደረጃዎችን አልፎ ለሙከራ ትግበራ የደረሰ መሆኑን የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሸዋይርገጥ ገልፀዋል ።

በስርዓተ ትምህርት ዝግጅቱ ላይ የተመረጡ የመማር ማስተማር የልህቀት ማዕከላት ዩኒቨርሲቲዎች እና ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ በአማካሪነት እንደተሳተፉበት ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ስርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ ዛፏ አብርሃ በበኩላቸው ይህ ሥርዓተ ትምህርት ሀገር በቀል እውቀትን፣ ግብረ ገብነትን ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የተላበሰ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል ።

በመሆኑም በዚህ የሙከራ ትግበራ ወቅት ከመምህራንና ከባለድርሻ አካላት ብዙ ግብዓቶች እንደሚሰበሰቡ ጠቅሰው ወላጆችና ሌሎችም አስተያየት እዲሰጡበት በድረ ገፅ ይለቀቃል ብለዋል።

በሙከራ ትግበራው ወቅት የሚመጡ አስተያየቶች ተካተው በ2016 ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባም በመድረኩ ተገልጿል ።

የሚሰጠው ስልጠናም መምህራን የመምህሩን መምሪያና የተማሪውን መጽሐፉ እዲተዋወቁ ይረዳቸዋል ተብሏል ።

#MoE

Share&forward
Join

@merejamnch
1.0K views11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 12:18:26
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራን እና የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶችን የሥራ ደረጃ ማሻሻያ አድርጓል።

በዚህም የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳት ለመሆን ዝቅተኛው ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሆን ተወስኗል።

በሌላ በኩል የረዳት ፕሮፌሰር ማዕረግ ለማግኘት የሚያስፈልገው ዝቅተኛው ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ የሦሥተኛ ዲግሪ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ማሻሻያውን ገቢራዊ እንዲያደርጉ በሚኒስቴሩ የአስተዳደርና መሰረተ ልማት ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) የተፈረመ እና ለተቋማቱ የተላከ ደብዳቤ አሳስቧል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch
206 views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 20:38:47
ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኮአን ለኢድ-አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳቹህ ።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምትገኙና በዓሉን ከቤተሰቦቻችሁ ርቃችሁ ለምታከብሩ ተማሪዎች መልካም የኢድ-አል አድሃ አረፋ በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

Eid Mubarak!

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch
584 views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 20:38:39
#SalaleUniversity

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ነባር የክረምት ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 07 እና 08/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch
540 views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 20:38:35
#MekdelaAmbaUniversity

ስቴም ፓውር በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ትምህርቶች ቤተ ሙከራ/ስቴም ማዕከል አደራጅቷል።

ማዕከሉ የምህንድስና ትምህርት መርጃ መሳሪያዎች/Electronics Lab እና የ3-D ዲጂታል ማተሚያ መሳሪያዎች የተሟላለት ነው፡፡

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሂሳብ ትምህርቶች (STEM) ማዕከሉ፤ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች አገልግሎት እንዲሰጥ የተደራጀ መሆኑ ተገልጿል።

የማዕከሉ መምህራን ከቤተ ሙከራው መሳሪያዎቹ አሰራር ጋር የሚያስተዋውቅ ስልጠናም ተሰጧቸዋል።

ማዕከሉ በአካባቢው የሚገኙ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የሚማሩትን በተግባር እንዲሞክሩና ወደ ፈጠራ ሥራ እንዲቀይሩ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch
495 views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 14:22:47
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
-------------------------------------

በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ሲሰጥ የነበረው የ2014 ዓም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

በፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይም ምንም አይነት ችግር እንዳላጋጠመ የትምህርት ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ገልፀዋል።

ተማሪዎችም ፈተናውን በጨዋነት እና እርጋታ እንደወሰዱም ተናግረዋል።

የክልል እና ከተማ አስተዳደር ቢሮዎችም ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ስራ አስፈጻሚዋ ገልፀዋል።

የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 27/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

#MoE

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch
716 views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 14:21:22
#WolloUniversity

እንሰትን የማላመድ ሙከራ በወሎ ዩኒቨርሲቲ

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ድርቅን መቋቋም የሚችል የእንሰት ዝርያ ለማላመድ የሙከራ ምርምር ማካሄድ ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመተባበር የሙከራ ምርምሩን እያካሄደ ነው።

ለዚህም 6 የእንሰት ዝርያዎችን ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በማምጣት በአራት ወረዳዎች የማላመድ ሥራ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

የእንሰት ዝርያዎቹ በደሴ ቲሹ ካልቸር ቤተ-ሙከራ በማሳደግ ከ3 እስከ 4 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ ይደረጋል ተብሏል።

የእንሰት ዝርያዎቹ የምግብ እጥረትን ከመቅረፍ ባለፈ ለመድኃኒት፣ ለእንሰሳት መኖ፣ ለአካባቢ ጥበቃ እና ለቃጫ አገልግሎት እንደሚውሉ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ እና ተመራማሪ አያሌው ታለማ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch
591 views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 14:21:19
#MettuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ የነባር የክረምት ተማሪዎች ቲቶርያል ትምህርት ከሐምሌ 07 እስከ 09/2014 ዓ.ም እንደሚሰጥ አሳውቋል።

የ2014 ዓ.ም የክረምት ትምህርት በመቱ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ብቻ እንደሚሰጥ ተቋሙ ገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch
560 views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 10:24:32
#JinkaUniversity

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የነባርና አዲስ የክረምት ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን አራዝሟል።

በዚህም ምዝገባው ሐምሌ 18 እና 19/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል።

ትምህርት ሐምሌ 20/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch
678 views07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ