Get Mystery Box with random crypto!

#MoE የትምህርት ሚኒስቴር በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራን እና የአ | 43 All University

#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራን እና የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶችን የሥራ ደረጃ ማሻሻያ አድርጓል።

በዚህም የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳት ለመሆን ዝቅተኛው ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሆን ተወስኗል።

በሌላ በኩል የረዳት ፕሮፌሰር ማዕረግ ለማግኘት የሚያስፈልገው ዝቅተኛው ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ የሦሥተኛ ዲግሪ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ማሻሻያውን ገቢራዊ እንዲያደርጉ በሚኒስቴሩ የአስተዳደርና መሰረተ ልማት ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) የተፈረመ እና ለተቋማቱ የተላከ ደብዳቤ አሳስቧል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch